Get Mystery Box with random crypto!

የነፍሴ ጥያቄዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ yenebsetiyakewoch — የነፍሴ ጥያቄዎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ yenebsetiyakewoch — የነፍሴ ጥያቄዎች
የሰርጥ አድራሻ: @yenebsetiyakewoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.30K
የሰርጥ መግለጫ

✋እንኩዋን ወደ ቻናላችን በሰላም መጡ
በዚ ቻናል ውስጥ ከእሰላም ወገኖቻችን የሚነሱ ጥያቄዎችን እንመልሳለን እንተነትናለን እባክዎን ልቦን ክፍት አድርገው ይከታተሉ👍
ለአስተያየት ለጥያቄ ለምክር @yenebsebot ይጠቀሙ
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
አስተያየት ካለ ያሳውቁን እንጂ Live ብለው ማግኘት ያለቦትን እንዳያጡ!!

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-07-29 13:15:27 እግዚአብሔር ምላጭ ተከራየ?

ኢሳይያስ 7:20 “በዚያን ቀን፤ እግዚአብሔር ከወንዝ ማዶ በተከራየው ምላጭ በአሦር ንጉሥ፤ የራሱንና የእግሩን ጠጉር ይላጨዋል፤ ምላጩም ጢሙን ደግሞ ይበላል” ይላል፡፡ አምላክ ምላጭ ይከራያልን? ሁሉን የፈጠረና ዓለሙ ሁሉ የርሱስ አይደለምን? ጸጉር ይላጫልን? ተራ የሰው ማህበራ ድርጊቶቹን ሁሉ የፈጣሪ እለታዊ ድርጊት እንደሆኑ አድርጎ መግለፅ ለፈጣሪ ያለንን እሳቤ በብዥታ የተሞላ አያደርግምን?

“ምላጭ” የተባለው የአሦር ንጉሥ መሆኑ በግልፅ እየታየ ይህ ጥያቄ መነሳቱ በራሱ በእጅጉ የሚያስገርም ነው፡፡ ይህ ቃል እግዚአብሔር እርሱን በማያቀውቀው፣ ጣዖት አምላኪ በሆነው የአሦር ንጉሥ ተጠቅሞ የይሁዳ ንጉሥ የአካዝ ጠላት የሆነውን ኤፍሬምን እንደሚያዋርድ የተነገረ ዘይቤያዊ ንግግር ነው፡፡ (መላጨት የኀዘንና የውርደት ምልክት ነው 2ሳሙኤል 10፡4፣ ኤርምያስ 41፡5፡፡) ይህ ነጥብ የሙግት ሐሳብ ሆኖ መቅረቡ በራሱ እጅግ አስቂኝ ነው፡፡ በሌላ ወገን ደግሞ ሙስሊም ወገኖች ይህንን ነጥብ “ከጠንካራ” ሙግቶቻቸው መካከል እንደ አንዱ በመቁጠር በተደጋጋሚ ማንሳታቸው በእጅጉ የሚያሳዝን ነው፡፡ ብዙ ሙስሊሞች አንዱ የጻፈውን በመያዝ በደመነፍስና በድርቅና ከመከራከር በዘለለ ክፍሉን አውጥቶ የማንበብ ልማድ የላቸውም፡፡

 እውነት ለሁሉ
share join sharw
@yenebsetiyakewoch
@yenebsetiyakewoch
21.1K views10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-27 08:31:28 (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕ. 1)
----------
3፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

4፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ስላመናችሁ በተሰጣችሁ በእግዚአብሔር ጸጋ ምክንያት ሁልጊዜ ስለ እናንተ አምላክን አመሰግናለሁ፤

5-6፤ ለክርስቶስ መመስከሬ በእናንተ ዘንድ እንደ ጸና፥ በነገር ሁሉ በቃልም ሁሉ በእውቀትም ሁሉ በእርሱ ባለ ጠጎች እንድትሆኑ ተደርጋችኋልና።

7፤ እንደዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ስትጠባበቁ አንድ የጸጋ ስጦታ እንኳ አይጎድልባችሁም፤

8፤ እርሱም ደግሞ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል።

9፤ ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።

10፤ ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልብና በአንድ አሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ።

መልካም ሰንበት
@yenebsetiyakewoch
20.1K views05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-25 17:33:31 ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ ነው ወይ?

ዳኒኤል vs ኢብኑ አጭር ልውውጥ

አድምጡትማ
share join share
@yenebsetiyakewoch
@yenebsetiyakewoch
12.8K viewsedited  14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-24 13:02:36 አላህ የፍጡር ስም

ሙስሊም ወገኖቻችን ኢየሱስ የሚለው ስም ለሰዎች መጠርያ ሆኖ ያገለገለባቸው አጋጣሚዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሚገኙ የፍጡር ስም ነው የሚል ሙግት እንደሚያቀርቡ ከላይ ተመልክተናል፤ ምላሻችንንም አስቀምጠናል፡፡ አሁን ደግሞ በዚህች አጭር ጽሑፍ የእነርሱኑ ሎጂክ ተጠቅመን አላህ የሚለው ስም የፍጡር ስም መሆኑን እናስረዳለን፡፡

ሙስሊም ወገኖቻችን ትክክለኛው የፈጣሪ ስም አላህ መሆኑን ለማስረዳት ከእብራይስጥና ከአራማይክ ጋር በማገናኘት ሲሞግቱ ይታያሉ፡፡ የተያዩ ምሑራዊ ምንጮችን ስንመለከትም አላህ የሚለው ቃል አል-ኢላህ የሚለው ቃል እጥርጥር መሆኑንና ሴማዊ ስረመሠረት ካላቸው ቃላት ጋር ተያያዥ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ቃሉም “አምላክ” ተብሎ የሚተረጎም እንጂ የተፀውዖ ስም አለመሆኑን እንረዳለን፡፡ ለምሳሌ ያህል የኢስላም ባሕረ ዕውቀት እንዲህ ይላል፡-

Allah is the Arabic equivalent of the English word God, and is the term employed not only among Arabic-speaking Muslims but by Christians and Jews and in Arabic translations of the Bible. A contraction of al-ilah, meaning “the god,” Allah is cognate with the generic pan-Semitic designation for “God” or “deity” (Israelite/Canaanite El, Akkadian ilu) and is particularly close to the common Hebrew term Elohim and the less frequent Eloah. It is thus, strictly speaking, not a proper name but a title. (Richard C. Martin, Encyclopedia of Islam and the Muslim World, p. 39)

ኤል፣ ኢሉ፣ ኤለሂም፣ ኤሎሃ፣ የሚሉት ሁሉ “አምላክ” የሚል ትርጉም ያላቸው የወል ስሞች አንጂ የተጸውዖ ስሞች አይደሉም፡፡ አላህ ወይም አል-ኢላህ የሚለው ቃል ተመሳሳይ ስረ መሠረት ያለው የወል ስም እንጂ የተጸውዖ ስም አይደም፡፡ ሙስሊም ወገኖቻችን ይህ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙት የእብራይስጥና አራማይክ ቃላት ጋር እንደሚገናኝ ዕውቅና መስጠታቸው ቃሉ በብቸኝነት እውነተኛውን አምላክ እንደሚጠቅስ መናገራቸው ስህተት መሆኑን ያሳይል፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት “አል-ኢላህ” ከሚለው ቃል ጋር አንድ ስረ መሠረት የሚጋሩት ቃላት እውነተኛውን አምላክ ብቻ ሳይሆን ሰብዓውያን ፈራጆችን፣ መላእክትንና ጣዖታትንም ጭምር ለማመልከት ጥቅም ላይ ውለዋልና፡፡

ቅድመ እስልምና የነበሩት አረቦች ቃሉን ከብዙ አማልክት (ኢላህ) መካከል አንዱና ትለቀኛው አድርገው ለሚያመልኩት አምላክ (አል-ኢላህ) ይጠቀሙት እንደነበረ ምሑራዊ ምንጮች ያሳያሉ፡-

Historical evidence indicates that Allah was the name of an ancient Arabian high god in a pantheon of other gods and goddesses like those found in other ancient Middle Eastern cultures. Worshipping him as the only real god may have started before the seventh century in Arabia, but it was in the Quranic revelations delivered by Muhammad as the prophet of Islam between 610 and 632 that the monotheistic ideal received its first clear expression among Arab peoples. (Campo, Encyclopedia of Islam, p. 34)

ቅድመ እስልምና አረብ ጣዖታውያን ትልቀኛው አምላክ አድርገው ያመልኩ የነበሩትና የካዕባ ትልቀኛው አምላክ ሁባል ነበር፡-

The religion of the pre-Islamic Bedouin was primarily animistic, while urban populations, such as the Meccans, worshiped a supreme God, al-Ilah, and its three daughters, al-Uzza, al-Lat, and Manat. Hubal was the chief deity of the Kaba. (Richard C. Martin, Encyclopedia of Islam and the Muslim World, p. 370)

ቅድመ አረብያ እስልምና አላህ የሚባለው አምላክ ሦስት ሴት ልጆች እንዳሉት ይታወቃል፤ እነዚህም አል-ላት፣ መናትና ኡዛ በመባል ይጠራሉ፡፡ “አል-ላት” “አል-ላህ” የሚለው ቃል ሴቴ ፆታ ሊሆን እንደሚችል ሊቃውንት ይናገራሉ፡-

The three most popular goddesses in preIslamic Arabia were al-Lat, Manat, and al-Uzza, sometimes called the daughters of Allah. Al-Lat (possibly the female counterpart of the Arabian high god Allah) was worshipped by Arab tribes in much of the peninsula. (Campo, Encyclopedia of Islam, p. 265)

ከዚህ ምን እንረዳለን? አላህ የሚለው ቃል እውነተኛውን አምላክ ብቻ ሳይሆን ሰዎችን፣ ጣዖታትንና መላእክትን ለማመልከት ጥቅም ላይ ከዋሉት ሴማዊ ቃላት ጋር አንድ ስረ መሠረት የሚጋራ ቃል ነው፡፡ አረብ ጣዖታውያንም ከሁሉም ትልቅ ብለው የሚያስቡትን ጣዖት ለመጥራት ይጠቀሙበት ነበር፡፡ ስለዚህ በሙስሊም ወገኖች ሎጂክ መሠረት አላህ የፈጣሪ ስም ብቻ ሳይሆን የፍጡራንም ስም ነው ማለት ነው፡፡

እውነት ለሁሉ
share join share
@yenebsetiyakewoch
@yenebsetiyakewoch
13.2K viewsedited  10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-24 09:15:21 ኢየሱስ የፍጡር ስም?

አብዱሎች ኢየሱስ በሚለው ስም የተጠሩ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሚገኙ ኢየሱስ የፍጡር ስም ነው ይሉናል:: ኢየሱስ የስሙ ትርጉም "ያሕዌ አዳኝ" ማለት በመሆኑ ምክንያት ለፈጣሪ ተገቢ የሆነውን ስም ለፈጣሪያቸው ክብር ፍጡራን ተሸከሙት እንጂ በትርጉም ደረጃ ወደ ፍጡራን የሚያመለክት ስም አይደለም:: ሰዎች በዚህ ስም ሲጠሩ ስሙ መታወቂያ ቢሆናቸውም የሚያስተላልፈው መልእክት ወይም ትርጉሙ ወደ ፈጣሪ እንጂ ወደ ፍጡራን አያመለክትም:: ነገር ግን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ስም ሲጠራ የስሙ ትርጉም ሙሉ በሙሉ እርሱን እንደሚያመለክት አምላክ እንጂ እንደ ፍጡር አይደለም:: ይህ መሆኑ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፏል:-

ማቴዎስ 1:21 "ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።"

ጌታችን ከኃጢአት ስለሚያድን ነው በዚህ ስም የተጠራው:: ከኃጢአት የሚያድን ደግሞ አምላክ ብቻ ነው:: ስለዚህ ኢየሱስ በዚህ ስም መጠራቱ እርሱ ከኃጢአት የሚያድን ያሕዌ መሆኑን ከማልከት አንጻር ሲሆን ሰዎች በዚህ ስም የተጠሩት ስሙ የተሸከመው ትርጉም ወደ ራሳቸው ሳይሆን ወደ ያሕዌ በሚያመለክት መንገድ ነው::

ከታች የሙስሊሞችን ተመሳሳይ ሎጂክ ተጠቅመን "አላህ የፍጡር ስም" በምትል አጭር ጽሑፍ እለቅላችዋለው::

እውነት ለሁሉ!!

share join share
@yenebsetiyakewoch
@yenebsetiyakewoch
9.3K views06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-23 08:17:08 ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል ዛሬም ነገም እስከለዘላለሙ አሜን!!

መልካም ቀን
@yenebsetiyakewoch
7.9K views05:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-23 07:38:42
ሙስሊም ሰባኪያን ክርስቶስን እናከብረዋለን እንወደዋለን የሚሉት ውሸታቸውን ነው፡፡ ነቢያቸው ሙሐመድም ቢሆን ክርስቶስን በበጎ የጠቀሰው የራሱ “ነቢይነት” ተቀባይነት እንዲኖረው የነበረው ብቸኛ አማራጭ በመሆኑ ነው፡፡ ከክርስቶስ በኋላ “ነቢያት ነን” ብለው የተነሱት ግለሰቦች ሁሉ በተወሰነ መንገድ የራሳቸውን ተልእኮ ከእርሱ ጋር በማያያዝ በእርሱ ሥልጣን ተንተርሰው የራሳቸውን ነቢይነት ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ሲሞክሩ እንመለከታለን፡፡ የክርስቶስ ማንነት የሃቀኝነት፣ የቅድስናና የግብረ ገብነት ጣርያ በመሆኑ እርሱን መቃወም የአንድን ነቢይነ ነኝ ባይ ሐሰተኛነት ከመቅፅበት ገሃድ ያወጣል፡፡ ለዚህ ነው ሙሐመድን ጨምሮ ከክርስቶስ በኋላ የተነሱት ሐሰተኛ ነቢያት ተልእኳቸውን ከእርሱ ጋር በማያያዝ የእርሱን አጽዳቂነት (Validation) ሲፈልጉ የምንመለከተው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ሐሰተኛ ነቢያትም ሆኑ የእነርሱ ተከታዮች የክርስቶስ ሕይወትና ትምህርት በኃጢአት የተነከረውን ስብእናቸውን ስለሚኮንን ከክርስቶስ በላይ የሚጠሉት ምንም ነገር የለም፡፡ ለቅቡልነት ሲሉ በአንደበታቸው እንደሚያከብሩት ቢናገሩም በተግባራቸውና በተጠኑ ንግግሮቻቸው እርሱን ዝቅ ለማድረግና የእርሱን ሥልጣን ለማጣጣል ጥረት ሲያደርጉ ይታያሉ፡፡ ሙሐመድ ይህንን ሲያደርግ ነበር፡፡ የእርሱም ተከታዮች ዛሬ ይህንኑ ሲያደርጉ እንታዘባለን፡፡ ለአብነት ያህል በምስሉ ላይ እንደሚታየው አሕመዲን ጀበል የተሰኙ ግለሰብ የጻፉትን ተመልከቱ፡፡ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐሰተኛ ነቢያትም ሆነ ከተከታዮቻቸው ጋር ሕብረት የለውም፡፡ እነርሱ ዝቅ ሊያደርጉት ቢሞክሩም እርሱ ግን በአባቱ ዘንድ ከዘላለም እስከ ለዘላለም ከብሮ የሚኖር በቅዱሳኑ የሚመለክ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው!

እውነት ለሁሉ
8.6K views04:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-22 18:36:07 ከህንፃ ቤተ ክርስትያን በላይ የሰዎች ነብስ ሊያሳስበን ይገባል
7.0K views15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-27 13:50:11 ሰላም ውድ የዚ ቻናል አባላት እንዴት ናችሁልኝ እንዴት እንደሆነ ባይገባኝም accounte እምቢ ብሎኝ ነበር።

ምንምም መፖሰት አልቻልኩም ነበር።እና የቻናሉ promoter የ prommotion ፖስት ከመፖሰት ውጪ ጠፍቼባችዋለው እና አሁን ተመልሻለው መርሀባ እውነትን እንመሰክራለን !
12.9K viewsedited  10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-12 14:04:17
እኔ ፖለቲካ አልወድም ስለ ብሄርም ስለ ፖለቲካም ስለ ቦታም ፅፌላችው አላውቅም።

ሁሌም ከብሄራችሁም ሆነ ከኢትዮጵያ ቤተክርስትያንን እና ክርስትናችሁን እንድታስቀድሙ ግን እመኛለው።

መቻቻል የሚባል ነገር አይገባኝም ስለመቻቻል እፅፋለው ጠብቁኝ ግን ግን መቻቻል በሚል ካባ ውሸት ለእውነት ስትመሰክር ማየት ያሳዝናል።

እኔ ኢትዮጵያዊ ለመባል መሰተር አለብኝ እንዴ ? እኔ ኢትዮጵያዊ ለመባል በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ያልተባረከ ምግብ መጎራረስ አለብኝ እንዴ?

እኔ ኢትዮጵያዊ ለመባል እስልምናን መሰበክ አለብኝ እንዴ?

ለማንኛውም ከኢትዮጵያዊነት ክርስትናን አስቀድማለው ኢትዮጵያዬም ከፍ ትበል ሰፋ አድርጌ እመለስበታለው በዚ ጉዳይ በደንብ እፅፋለው
@yenebsetiyakewoch
@yenebsetiyakewoch
14.1K viewsedited  11:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ