Get Mystery Box with random crypto!

ሙስሊም ሰባኪያን ክርስቶስን እናከብረዋለን እንወደዋለን የሚሉት ውሸታቸውን ነው፡፡ ነቢያቸው ሙሐመድ | የነፍሴ ጥያቄዎች

ሙስሊም ሰባኪያን ክርስቶስን እናከብረዋለን እንወደዋለን የሚሉት ውሸታቸውን ነው፡፡ ነቢያቸው ሙሐመድም ቢሆን ክርስቶስን በበጎ የጠቀሰው የራሱ “ነቢይነት” ተቀባይነት እንዲኖረው የነበረው ብቸኛ አማራጭ በመሆኑ ነው፡፡ ከክርስቶስ በኋላ “ነቢያት ነን” ብለው የተነሱት ግለሰቦች ሁሉ በተወሰነ መንገድ የራሳቸውን ተልእኮ ከእርሱ ጋር በማያያዝ በእርሱ ሥልጣን ተንተርሰው የራሳቸውን ነቢይነት ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ሲሞክሩ እንመለከታለን፡፡ የክርስቶስ ማንነት የሃቀኝነት፣ የቅድስናና የግብረ ገብነት ጣርያ በመሆኑ እርሱን መቃወም የአንድን ነቢይነ ነኝ ባይ ሐሰተኛነት ከመቅፅበት ገሃድ ያወጣል፡፡ ለዚህ ነው ሙሐመድን ጨምሮ ከክርስቶስ በኋላ የተነሱት ሐሰተኛ ነቢያት ተልእኳቸውን ከእርሱ ጋር በማያያዝ የእርሱን አጽዳቂነት (Validation) ሲፈልጉ የምንመለከተው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ሐሰተኛ ነቢያትም ሆኑ የእነርሱ ተከታዮች የክርስቶስ ሕይወትና ትምህርት በኃጢአት የተነከረውን ስብእናቸውን ስለሚኮንን ከክርስቶስ በላይ የሚጠሉት ምንም ነገር የለም፡፡ ለቅቡልነት ሲሉ በአንደበታቸው እንደሚያከብሩት ቢናገሩም በተግባራቸውና በተጠኑ ንግግሮቻቸው እርሱን ዝቅ ለማድረግና የእርሱን ሥልጣን ለማጣጣል ጥረት ሲያደርጉ ይታያሉ፡፡ ሙሐመድ ይህንን ሲያደርግ ነበር፡፡ የእርሱም ተከታዮች ዛሬ ይህንኑ ሲያደርጉ እንታዘባለን፡፡ ለአብነት ያህል በምስሉ ላይ እንደሚታየው አሕመዲን ጀበል የተሰኙ ግለሰብ የጻፉትን ተመልከቱ፡፡ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐሰተኛ ነቢያትም ሆነ ከተከታዮቻቸው ጋር ሕብረት የለውም፡፡ እነርሱ ዝቅ ሊያደርጉት ቢሞክሩም እርሱ ግን በአባቱ ዘንድ ከዘላለም እስከ ለዘላለም ከብሮ የሚኖር በቅዱሳኑ የሚመለክ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው!

እውነት ለሁሉ