አልሀኪም፣ በሱዩጢና በሌሎችም ዑለማዎች ሶሂህ የተሰኘው ይህ ሀዲስ የሚከተሉትን ቁሞ ነገሮች ያስተምረናል፦ 1. የነብያችን صلى الله عليه وسلم ልቅና፤ 2. ነብዩ አደም በርሳቸው በረከት ሐጢአታቸው መማሩ፣ 3. በነብዩ صلى الله عليه وسلم ክብርና ልዕልና ተወሱል ማድረግ እንደሚበረታታ፤ 4. በዚህ ዓለም በህይወት በሌሉበት ዘመንና ሁኔታ ተወሱል በርሳቸው ማድረግ እንደሚወደድ፤ 5. ነብያችን صلى الله عليه وسلم ክብር ተወሱል ማድረግ የነብያት ሱና መሆኑ፤ 6. ነብያችን صلى الله عليه وسلم ለዓለም መፈጠር ሰበብ መሆናቸው፤ 7. ነብያችን صلى الله عليه وسلم ሳይፈጠሩ በፊት በላይኛው ዓለም ዝናቸው የገነነ እንደነበረ፤ 8. በርሳቸው ክብር አላህን መማጸን ያለው ትርፋት፤