Get Mystery Box with random crypto!

#አብዱልቃድር_ኻን_የፓኪስታን_የኑክሌር_አባት_የሰሜን_ኮሪያ_ባለውለታ ሙሉ ስሙ አብዱልቃድር አብዱ | حيات سحبا የምርጦች ትውልድ ታሪክ

#አብዱልቃድር_ኻን_የፓኪስታን_የኑክሌር_አባት_የሰሜን_ኮሪያ_ባለውለታ

ሙሉ ስሙ አብዱልቃድር አብዱልገፉር ኻን ይባላል ። ከአባቱ ከአብዱል ገፉርና ከእናቱ ከዙለይካ እ.ኤ.አ በ 1936 በዛሬዋ ህንድ ተወለደ ። ያኔ እርሱ ሲወለድ ባንግላድሽ ፣ ፓኪስታንና ህንድ አንድ ሃገር ሆነው በእንግሊዝ አገዛዝ ስር የነበሩበት ነበር ።

በ 1947 እንግሊዝ ከህንድ ክፍለአህጉር ለቃ ስትወጣ ትገዛቸው የነበሩት ህዝቦች በሀይማኖት ጦርነት ይተላለቁ ጀመር ። የአሁኗ ህንድ በሂንዱ ሃይማኖታዊ ብሔርተኝነት ስትመሰረት ፓኪስታንና ባንግላዴሽ ደግሞ በኢስላማዊ ብሔርተኝነት አንድ ሃገር ሆነው ተገነጠሉ ። የአሁኗ ፓኪስታን ምእራብ ፓኪስታን ትባል የነበረ ሲሆን ባንግላዴሽ ደግሞ ምስራቅ ፓኪስታን ተብላ አንድ ሃገር ነበሩ ። ምንም እንኳ ባንግላዴሽ ሗላ ላይ ከፓኪስታን ብትገነጠልም ።

የአብዱልድር ኻን ቤተሰቦች የሚገኙት በህንድ ግዛት ውስጥ ቢሆንም ጥብቅ የእስልምና አማኞች በመሆናቸው ከሚደርስባቸው ሃይማኖታዊ ጥቃት ለመሸሽና ወደ ኢስላማዊቷ ፓኪስታን ለመጠቃለል ወደ ፓኪስታን ተመሙ ። አብዱልቃድርም ህንድ ውስጥ የጀመረውን ትምህርት ትቶ ወደ ፓኪስታኗ ካራቺ ከተማ በመምጣት ትምህርቱን ቀጠለ ። በዚያም በካራቺ ዩኒቨርስቲ በፊዚክስ የመጀመሪያ ድግሪውን ያዘ ።

በዚያው በካራቺ እያለ አንድ ህይወቱን የሚቀር ነገር ተከሰተ ። አብዱልቃድር ኻን የምእራብ ጀርመንን ስኮላርሽፕ በማግኘት ወደ አውሮፓ አቀና ። ያኔ ጀርመን ለሁለት የተከፈለች ሲሆን ምእራብ ጀርመን እና ምስራቅ ጀርመን በመባል ትጠራም ነበር ። አብዱልቃድር ትምህርቱን በጀርመን እየተከታተለ ሳለ ከኔዘርላንድ ሌላ የትምህርት እድል አግኝቶ ወደ አምስተርዳም አቀና ። የአብዱልቃድር ብቻ ሳይሆን የፓኪስታንም ታሪክ የተለወጠው በዚህ በኔዘርላንድ ቆይታው ነው ።

በትምህርቱ ስኬታማ በስራውም ታማኝ የነበረው አብዱልቃድር ኻን በብረት ምህንድስናና በሌሎችም ሳይንሳዊ ምርምሮች ከፍተኛ እመርታ በማሳየቱ የእንግሊዝ ጀርመንና ኔዘርላንድ የጋራ የኑክሌር መመራመሪያ ማእከል የሆነው URENCO የተሰኘው ተቋም በኑክሌር ተመራማሪነት ቀጠረው ። በዚህም ከፍተኛ የኑክሌር እውቀቶችን ማካበት ቻለ ። በስራው የተቋሙን እምነት በትልቁ ማግኘት የቻለው ፓኪስታናዊው ሳይንቲስት ታላላቅ ሚስጥራዊ የኑክሌር ረቂቆችን ዶክመንቶችን እንዲተረጉም ሃላፊነት ተሰጠው ። በዚህ ጊዜ ያገኛቸውን እውቀቶች በሀገሩ ቋንቋ እየከተበ ለሀገሩ ውለታ ለመዋል ያዘጋጃቸው ጀመር ።

አብዱልቃድር ኻን ሀገሩን አብዝቶ የሚወድ ለእምነቱም ቀናኢ የነበረ ሰው በመሆኑ በነዚያ የአውሮፓ ታላላቅ ጊዜያቶቹ ለአንድት ቅፅበት እንኳ ሀገሩን አይዘነጋም ነበር ። እናም ተገቢውን የኑክሌር ሚስጢር ከሸከፈ እና ረቂቆቹን አዘጋጅቶ ከጨረሰ በሗላ ለሀገሩ መንግስት የኑክሌር ቦንብ ለመስራት የሚያስችለው ቀመር እንዳለውና ለዚህም ሁሉን ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን በደብዳቤ አሳወቀ ። ይሁን እንጅ ፓኪስታን አብዱልቃድርን በአንድ ጊዜ ልታምነው አልቻለችም ። እናም አስፈላጊው መጣራት ከተደረገበት በሗላ ከዙልፊቃር አሊቡቶ ጋር ተገናኝቶ ተነጋገረ ። አሊቡቶ አብዱልቃድርን ያን ያክል ተስፋ ባይጥሉበም "ጥሩ ነው " በማለት ሀሳቡን ተቀበሉት ።

የምንጊዜም ጠላቷ ህንድ " የቡድሃ ፈገግታ " በተሰኘው የድል ብስራቷ የኑክሌር ባለቤት መሆኗን ያረጋገጠች ሆና ሳለ ፓኪስታንን እንቅልፍ ሊወስዳት ቀርቶ ሊያንጎላጃት አይችልምና ዙልፊቃር አሊቡቶ የሀገሪቱን ሳዬንቲስቶች በአስቸኳይ የኑክሌር መሳሪያን እንዲሰሩ ቀጭን ትእዛዝ የሰጡበት ጊዜና ሳይንቲስቶቹ በሚስጥር ጥድፊያ ላይ በነበሩበት ወቅት ነው አብዱልቃድር ኻን ከሰማይ እንደወረደ መላኢካ ከድንገት ዱብ ያለው ።

ግና ቀድመው የነበሩት የፓኪስታን ሳይንቲስቶች በቅናት ይሁን በአጉል ኢጎ ከአብዱልቃድር ጋር መስማማት ተሳናቸው ። እርሱ የነርሱን ስራ የኑክሌር ባለቤት እንደማያደርግ ሲነግራቸው ጭራሽ መካረሩ ጦፎ የፓኪስታን ኑክሌር ሳይንቲስቶች ለሁለት ተሰነጠቁ ። ይህ ያስደነገጠው የፓኪስታን መንግስት በአብዱልቃድር ኻን ስር የሚመራ ተቋም አደራጀ ። አብዱልቃድር ኻንም ይዞ የመጣቸውን የማይገኙ የኑክሌር ሚስጥሮች ስራ ላይ አዋላቸው ።

ከብዙ ጥረትና ልፋት በሗላ እጅግ በረቀቀ ሚስጥር የኑክሌር ቁሳቁስችን ከአውሮፓና አሜሪካ ጭምር በጥብቅ ሚስጥር እየለቀሙ ወስደው ከሰሩ በሗላ ፓኪስታን ለአለም የኑክሌር ባለቤትነቷን አሳየች ። በዚህ ጊዜ ከእስራኤል እስከ ህንድ በድንጋጤ ቢዋጡም በቁጣ ቢንተከተኩም ነገሩ ያለቀለት ነበርና ምንም ማምጣት አልቻሉም ነበር ። ሳይንቲስቱ ዶክተር አብዱልቃድር ኻን የኑክሌር ቦንቡን ባበሰረበት ወቅት " የታጠቅነው የኑክሌር ቦንብ ህንድን ብቻ ሳይሆን እስራኤልንም ማውደም የሚችል ነው " በማለት ነበር እስራኤልን ኩም ያደረጋት ። እናም እስራኤል በኢራንና ኢራቅ እንደፈፀመቺው አይነት ጥቃትና ትንኮሳ በፓኪስታን ላይ ለማድረግ ከቶም አልደፈረችም !

አብዱልቃድር ኻን ፓኪስታንን ያስታጠቃት ኑክሌር ብቻ አይደለም ይልቁንስ ረጅም ርቀት ሊመዘገዘጉ የሚችሉ ሚሳኤሎች ባለቤት ትሆንም ዘንዳ ያስቻላት የማይተካ ልጇ ነው ። ፓኪስታን አብዱልቃድር ኻንን የመሰለ ከሺህ አመታት አንድ ጊዜ የሚፈጠር ልጅ ባይኖራት ኖሮ ዛሬ እኔደ ኢራን ኑክሌር ለመታጠቅ 30 አመታት የሚፈጅባት ሀገር ትሆን ነበር ።

የምእራባዊያን ጠላቱ አብዱልቃድር ኻን የኑክሌር ባለቤት ያደረገው ሀገሩን ፓኪስታንን ብቻ አይደለም ! ይልቁንስ የኪሞቹን ሀገር ኮሚኒስቷን ሰሜን ኮሪያን ጭምር እንጅ ። እነዚያን አብዱልቃድር እንጅ ሌላው የሌለውን የኑክሌር ቀመሮች ለሰሜን ኮሪያ ባይሰጣት ኖሮ ሰሜን ኮሪያ አሜሪካ የምትፈራት የኑክሌር ባለቤት ሀገር ላትሆንም ትችል ነበር ። አብዱልቃድር ለሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ቴክኖሎጂን ለማስተላለፍ ከ 13 ጊዜ በላይ እንደተመላለሰ ምንጮች አረጋግጠዋል ። ይህም በፓኪስታን መንግስት በተሰጠው ትእዛዝ ነበር ። ፓኪስታን ለሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ቴክኖሎጂን ስታስተላልፍ ሰሜን ኮሪያ በአፀፋው የሚሳኤል ቴክኖልጂዎችን ለፓኪስታን ታስተላልፍ ነበር ።

አብዱልቃድር ኻን ከሰሜን ኮሪያ በተጨማሪ ለኢራን እና ሊቢያ የኑክሌር ቴክኖሎጂዎችን እንዳስተላለፈ ይነገራል።

ይህን የደረሰችበት አሜሪካም በፓኪስታን ላይ ልምጯን መዘዘች ። ፓኪስታንም ከአሜሪካና አጋሮቿ በትር ለማምለጥ ስትል ይህንን ያደረገው ካለ እውቅናዋ አብዱልቃድር መሆኑን ለነ አሜሪካ ገለፀች ። እናም አብዱልቃድር ታሰረ ። ፓኪስታን ከነአሜሪካ ማእቀብ ለማምለጥ ስትል የቁርጥ ቀን ልጇን ፊዳ አቀረበቺው ። ልጇም አላሳፈራትም ። " እኔ ሀገሬን ለማዳን እንኳን መታሰርና የህይወት መስዋእትነትም እከፍላለሁ " በማለት ሃላፊነቱን ወስዶ የቁም እስረኛ ሆነ ። ሁሉም የፓኪስታን ቁማር ነበርና በሗላ ላይ ነፃነቱ በፍርድቤት ተረጋግጦለት ከእስር ነፃ ሆነ ።

አብዱልቃድር ኻን እንደዚህ ይላል
" እኔ ፓኪስታንን ሁለት ጊዜ አድኛታለሁ አንደኛው የኑክሌር ቦንብ ባለቤት አድርጌ የማትደፈር ሀገር ሳደርጋት አድኛታለሁ ሁለተኛው ደግሞ የኑክሌር ቴክኖሎጂን ለነ ኮሪያ አሳልፈሻል ተብሎ ከፍተኛ ማእቀብ ሊጣልባት ሲል ራሴ ሃላፊነቱን ወስጄ አድኛታለሁ " በማለት ገልጿል።

አብዱልቃድር ኻን በፓኪስታን ውስጥ ያልተሸለመው አይነት ሽልማት የለም ። ታላላቆቹ የፓኪስታን ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉም በሽልማትና ዶክትሬት አንቆጥቁጠውታል ። በእርሱ ስም ያልተሰየመ ግዳና እና ተቋም የለም ። እርሱ ፓኪስታኖች ፈጣሪ የሰጣቸው በረከት