Get Mystery Box with random crypto!

የማንቂያው ደውል 🔔🔔🔔

የቴሌግራም ቻናል አርማ yemankiyaw_dewl — የማንቂያው ደውል 🔔🔔🔔
የቴሌግራም ቻናል አርማ yemankiyaw_dewl — የማንቂያው ደውል 🔔🔔🔔
የሰርጥ አድራሻ: @yemankiyaw_dewl
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 506
የሰርጥ መግለጫ

የቤተክርስቲያንን ስርዓት ባማከለመልኩ የማንቂያው ደውል ቻናል ስርዐት ባለውመልኩ ጽሁፎችን እንለቅላችሀለን የዚህ ቻናል አላማው
ሁሉንም ሰው የሚያስተምር ነው፡፡
ስናገኝ ደግሞ ስነጹፎችን ፣ ግጥሞችን ፣ ጭውውት ፣ እንዲሁም መዝሙሮችን እና
ሌላም ሌላም ነገሮች እንለቅላችሇለን
የቻናሉን ሊንክ ለጓደኞቻችሁ #ሼር በማድረግ
አባላት እንጨምር #ሼር

ለማንኛውም ነገር @Robellllll_bot

Ratings & Reviews

1.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

3


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-14 16:51:49 ያን ጊዜ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ በመብረቅ ላይ ተጭኖ በረረ እነዚያ አጋንንት ወደአሉበትም ወረደ። ደመናትም ከበቡአቸው መላእክትም በእሳት ሰይፍ መተሩአቸው በመብረቅም አጨዱ አቸው አመድም ሆነው በነፋስ በተኑአቸው። የእነዚያም አጋንንት ቁጥራቸው ሰባት መቶ ሺህ እልፍ ከአንዱ ሺህ ነበር። ከዚህም በኃላ ጌታ ክርስቶስን የካዱ ወዳሉበት ወደ ምእራብ ሀገር ወሰደው። ነገስታቱና መሳፍንቱ መኳንንቱም በሚወጡበትና በሚገቡበት ጉዳና ላይ አቆመው ጌታችንም በዚች ጉዳና ብዙ መከራ ያገኝሀል ግን በርታ ታገስ ብሎት በዚያ ተወው። በዚያን ጊዜም የአርብ ንጉስ ጣዖታቱን አስይዞ መኳንንቱን ሰራዊቱን አስከትሎ በዚያች ጎዳና መጣ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስን በጎዳና ውስጥ በተገናኙት ጊዜ ጣኦታቱ ወድቀው ተሰባበሩ።

ንጉሱም አባታችንን በአየው ጊዜ አንተ ጠጉር ለባሽ ምንድነህ ሰው ነህን አለው።አባታችንም አዎን ክብር ያለው የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያው የሆንኩ ሰው ነኝ ብሎ ለከሀዲው ንጉስ መለሰለት። ንጉሱም ዳግመኛ አባታችንን በዚያ አይሁድ በሰቀሉት ታምናለህን አለው አባታችንም በሰው ፊት አምንበታለሁ።ስለ እኔ በተሰቀለው አላፍርበትም ስለ እኔ ብቻ የተሰቀለ አይደለም ስለ አንተና ከአንተ ጋራ ስለ አሉትም ነው እንጂ ንጉስ ሆይ የዘላለም ህይወትን ታገኛላችሁ እመኑበት አለው።

ንጉሱም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ተቆጣ ሰራዊቱንም ጠርቶ በፍጥረት እሳትን አንድዱ ለተሰቀለው ለናዝሬቱ ሰው ባሪያው ነኝ የሚለውን ጠጉር ለባሽ ወስዳችሁ ጨምሩት አላቸው።የእሳቱም ነበልባል በረጅም ዛፍ መጠን ከፍ ከፍ እስከሚል አነደዱ። አባታችን ግን ንጉሱና ሰራዊቱ ሁሉ እያዩት አልፎ በፈቃዱ ወደ እሳቱ ገባ። እሳቱም እንደወንዝ ውኃ ሆነ ሰረዊቱም እጅግ አደነቁ እኩሌቶቹም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። ንጉሱም ሲያደንቁ በአየ ጊዜ ፈፅሞ ተቆጣ ከሰባ ሰባት አርበኞቹ ጋራ በቁጣ ተነስቶ ያደነቁትንና ያመኑትን አንገታቸውን ቆረጠ ።

በዚያችም ቀን የተቆረጡ አርባ መቶ ሺህ ሆነው ተቆጠሩ።ንጉሱም የአባታችንን አንገት ሊቆርጥ ሰይፉን መዞ ተወርውሮ ሄደ። ያን ጊዜም ከመብረቅና ከነጎድጓድ ጋራ ታላቅ ንውፅውፅታ ሆነ ንጉሱንም ከሰራዊቱ ጋራ አጠፋው ከከሀዲው ንጉስ ጋራ የሞቱት ቁጥራቸው አራት ሺህ እልፍ ሆነ።

ጌታችንም አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስን ጠላቶችህንና የኔንም ጠላቶች አጠፋሁልህ አለው።አባተችን ግን በመብረቅ የሞቱትን ሬሳቸውን ነፍሳቸውንም መላእክተ ፅልመት ወደ ስቃይ ሲወስዱአቸው በአየ ጊዜ መድኃኒታችንን እሊህን ስሁታን ማርልኝ ሰው ስሁትና ከዳተኛ ነውና አቤቱ አንተ ግን መሀሪ ይቅር ባይ ታጋሽም ነህ አለው።አባታችንም ይህን ሲናገር ጌታችን ተሰወረ።

አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስም ከዚያ ሄደ ታላቅ ገደልም አገኘ እግሮቹንም በገመድ አስሮ በገደሉ ውስጥ ተዘቅዝቆ ተሰቀለ።ሰይጣንም መጥቶ ያቺን ገመድ ቆረጣት ወደ ታችም ተወርውሮ ወረደ።ቅዱስ ሚካኤልም ቀድሞ አባታችንን ያዘው በእግርህ ላቁምህ ወይም በራስህ አለው በራሴ እቆም ዘንድ ተወኝ አለው ትቶት ሄደ።

በዚያም በራሱ ቁሞ በጥርሶቹም ደንጊያ ነክሶ እስከ ሰላሳ አመት ኖረ አንጀቱና ናላው ሁሉ እየፈሰሰ አልቆ መላ አካሉ እንደእንጨት ቅርፊት ሆነ። ከሰላሳ አመትም በኃላ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባታችንን ገብረ መንፈስ ቅዱስ እያለ ሶስት ጊዜ ጠራው። እርሱም እነሆኝ ጌታዬ አለ ጌታችንም እነዚያን ከሀዱዎች ምሬልሀለሁ ከዚህ ተነሳ አለው።ያን ጊዜ የነከሰውን ደንጊያ ትቶ ተነሳ።ጥርሱም ተነቅሎ በድንጊያ ተተክሎ ቀረ። ክንፎችም ተሰጥተውት እየበረረ ከእግዚአብሔር ፊት ደረሰ ጌታውንም ከማርክልኝ ከስጋቸው ጋራ ተነስተው በመጠመቅ ክርስቲያኖች ይሁኑ ብሎ ለመነው። መድኃኒታችንም በሽተኞችን ልትፈውስ ሙታንን ልታስነሳ ስልጣን ሰጥቼሀለሁ አሁንም ወደተገደሉት ሄደህ በመስቀል ምልክት በላያቸው አማትብ ህይወት መድኃኒት በሆነ ስሜም አስነሳቸው አለው።ያን ጊዜም በድኖቻቸው ወዳሉበት ሂዶ አስነሳቸው አጥምቆም ክርስቲያኖች አደረጋቸው ከእርሳቸውም ሄደ።

ከዚህ ዓለም የሚለይበት በቀረበ ጊዜ እነሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እነሆ ተገለጠለት። ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ እስከ አስራ አምስት ትውልድ የምህረት ቃል ኪዳን ሰጠው።የእድሜውም ዘመናት አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ሲሆን በሰላም በፍቅር አረፈ። ጌታችንም ነፍሱን ተቀበለ አቅፎም ሳማት በመላእክትና በቅዱሳን ሁሉ ምስጋና አሳረጋት።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መጋቢት)
578 views፩ ፪ ፫ ፬ ፭......., 13:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-13 18:59:45 #ምኩራብ
(የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት)

ምኩራብ ማለት ለአምልኮትና ለትምህርት ለህብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጥ የአይሁድ ቤተ ጸሎት ነው። ጌታ በመዋዕለ ስብከቱ በእስራኤል ሀገር ብዙ ምኩራቦች ስለነበሩ እየገባ ወንጌልን አስተምሮባቸዋል። በዚህም “ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሀረ ቃለ ሃይማኖት” እንዲል ቅዱስ ያሬድ ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ ገብቶ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ። ከሚለው የቅዱስ ያሬድ ዜማ ሥያሜውን አግኝቷል።

በምኩራብ ጸሎትና ትምህርት ይፈጸምበታል። መሥዋዕት ግን አይከናወንም። መሥዋዕት ግን በታላቁ ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም ብቻ ይፈጸም ነበር። በዚህ ሳምንት የሚነገረው ታሪክ ጌታ ቤተ መቅደሱን የገበያ ማዕከል አድርገው ሸቀጥ ዘርግተው በጉን ላሙን ርግቡን እየሸጡ አገኛቸው። በዚህ ተቆጥቶ በጉን ላሙን ርግቡን ከምኩራብ አስወጥቶ ሸቀጣቸውንና መደርደሪያቸውን እንዲሁም ወርቅና ብራቸውን በነፋስ በተነባቸው ይላል።

በዚህ ሁኔታ ከቤተ መቅደስ አስወጥቶ "ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች እናንተ ግን የሽፍቶችና የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችኋት" በማለት ወቅሷቸዋል። “አሰስሉ ወአውፅኡ ዘንተ እምዝየ ወኢትረስዩ ቤተ አቡየ ቤተ ምሥያጥ” እንዲል ዮሐ. 2፥16፤ ማቴ. 21፥13። ይህን ተአምር በማሳየት ቤተ ጸሎት የተቀደሰ ከገበያ የተለየ መሆኑን አስተምሮበታል።

በሰንበተ ምኩራብ ጌታ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለዋጮችን ማስወጣቱ ወርቅና ብሩን በነፋስ መበተኑ ላሞችን በጎችን በጅራፍ መግረፉ ቤተ መቅደሱን ማንጻቱ ወዘተ ይነገራል።

(የዚህም በዓል ታሪክ ዝርዝር ሁኔታው ማቴዎስ 21፥12-13 ላይ ተጠቅሷል፡፡)

#የቅዳሴ_ምንባባት፦

ቆላስ. 2፥16-23
«እንግዲህ በመብል ወይ በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፣ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው፡፡ .......፡፡»

ያዕ. 2፥14-26
«ወንድሞቼ ሆይ፣ እምነት አለኝ የሚል፣ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን ......፡፡»

ሐዋ. 1ዐ፥1-9
«በቂሣርያም ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራ የመቶ አለቃ የሆነው ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ ሰው ነበር፡፡ እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክና የሚፈራ ለሕዝብም እጅግ ምጽዋት የሚያደርግ ወደ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ፡፡ ....፡፡"

#ምስባክ- መዝ 68፥9
እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ፡፡

(የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና
ነፍሴን በጾም አስመረርኋት፡፡)

#ወንጌል፡- ዮሐ 2፥12-25
«ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፣ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ፡፡ የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡ ወደ መቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤ የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፣ .....፡፡»

(ከመድብለ ታሪክ እና ግጻዌ የተወሰደ)
496 views፩ ፪ ፫ ፬ ፭......., 15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-11 09:00:32
463 views፩ ፪ ፫ ፬ ፭......., 06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-07 20:59:05
ዜና ዕረፍት
አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ !!!

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትን ከ30 ዓመታት በላይ የመሩት አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ።

ብፁዕነታቸው ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል።

በሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ፣ ጥር 14 ቀን 1972 ዓ.ም. ከተሾሙት 15 ብፁዓን አባቶች አንዱ የኾኑት ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም፤ እስከ ዕርግና ዘመናቸው ከቆዩበት ደብረ ብርሃን ቀደም ብሎ፣ በአርሲ እና በመቐለ አህጉረ ስብከት ተመድበው ጉልሕ ሐዋርያዊ አገልግሎት አበርክተዋል፡፡

የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን።
547 views፩ ፪ ፫ ፬ ፭......., 17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ