Get Mystery Box with random crypto!

#በእንተ_ምጽዋት 'ከዕለት ጉርስኽ የተረፈኽ ቢኖር ለደኻ ስጠው። . . . ክብር ይግባውና ወደ ፈ | የማንቂያው ደውል 🔔🔔🔔

#በእንተ_ምጽዋት

"ከዕለት ጉርስኽ የተረፈኽ ቢኖር ለደኻ ስጠው። . . . ክብር ይግባውና ወደ ፈጣሪ ለመቅረብ እንደ ምጽዋት ክሂል የሚሰጥ የለም። ከሥራም ወገን ወድዶ ሰጥቶ እንደመቸገር በልቡና ኅድዓት (ፀጥታ ፣ ዕረፍት ፣ ሠላም) የሚያደርግ የለም። ሰጥተኽ መጽውተኽ አጥተኽ 'አላዋቂ' ቢሉኽ ይሻልኻል። ጨብጠኽ ይዘኽ አስተዳደር ዐዋቂ ከሚሉኽ።. . . ኅብስቱን ከውሃ ጣለው ብሎ ተናግሯልና። ከውሃ የጣሉት እንዳይመለስ ፣ 'ይ 'ሰጠኛል' ብለኽ አትስጥ ሲል ነው። አንድም ኀብስቱን ከእግዚአብሔር ፊት አኑረው ሲል ነው። በፍጻሜ ዘመንኽ ዋጋኽን ታገኛለኽ።

ባለጸጋውን ለይተኽ ለድኻ አትስጥ። 'ይኽ ይገባዋል ይኽ አይገባውም' አትበል። አላ ኩሉ ሰብእ ይኩኑ ዕሩያነ በኅቤከ -በምትመጸውትበት ጊዜ አስተካክለኽ መጽውት እንጂ! አስተካክለኽ በመስጠትኽ ወደ በጎ ሥራ ለማቅረብ ትችላለኽ። ምንም የበቁ ባይኾኑ ነፍስ በመብል በመጠጥ ምክንያት ወደ ክቡር እግዚአብሔር ትሳባለችና! በምጽዋት ጊዜ 'ይኽ አይሁዲዊ ነው። ይኽ ከሀዲ ነው' አትበል። 'ይኽ ነፍሰ ገዳይ ነው' አትበል። ይልቁንስ ብታስታውለው ወንድምኽ ነው እንጂ። አእምሮ አጥቶ ከሃይማኖት ተለየ እንጂ።ከበጎው ነገር ወገን ለሰው ያደረግኽ እንደኾነ መክፈልን አትውደድ።. . .

መጽውተኽ ብትቸገር ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር ቸርነት ከትካዝ ሥጋዊ ትድናለኽ! ከኹሉ በላይ ትኾናለኽ! ሰው ኹሉ ለገንዘቡ ሲገዛ እሱ ለእግዚአብሔር ይገዛልና። . . . 'በዝናም ያበቀለው በፀሓይ ያበሰለው የእግዚአብሔር ገንዘብ ነው' ብለኽ ምጽዋትኽን በትሕትና መጽውት። ጻድቃን በሚከብሩበት ጊዜ ይቅርታን ታገኛለኽ"

(መጽሐፍተ መነኮሳት (ማር ይስሐቅ) ፣ አንቀጽ ፩ ፣ ምዕ.፲፪፣ ገጽ ፳፩ - ፳፫)