Get Mystery Box with random crypto!

'ነገ ለአንተ የተሸለ ነው' ያለህበት ዛሬ ለአንተ እጅግ አሰልቺ ከሆነ ለነገህ ኑር። በዚህ ነገህ | የማንቂያው ደውል 🔔🔔🔔

"ነገ ለአንተ የተሸለ ነው"

ያለህበት ዛሬ ለአንተ እጅግ አሰልቺ ከሆነ ለነገህ ኑር። በዚህ ነገህ ዉስጥ አንተን ለማረጋጋት የእግዚአብሔር እጅ ወደ አንተ መዘርጋቱን ተመልከት፡፡ ይህንን ካደረግህ በዚህ ነገህ ዉስጥ ለችግሮችህ ብዙ መፍትሔዎችን መመልከት ትችላለህ። የአንተ ዛሬ ጨለማ ከሆነ ነገህ በፊትህ የብርሃን መስኮቶችን ይከፈትልሀል ፡፡

ቅዱሳን ነገ ለሚያገኙት የዘለዓለም ህይወት ስለ ኖሩ ተስፋቸዉን ሁሉ በዚህ ነገ ላይ ጥለዉት ነበር። ሳዖል ባሳደደዉ ጊዜ ነብዩ ዳዊት የኖረዉ ለነገዉ ነዉ። ነብዩ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ዉስጥ ሳለ የኖረዉም ለነገዉ ነዉ። ቅዱስ ዮሴፍ በወኅኒ ሳለ አባቱ ቅዱስ ያዕቆብ ደግሞ በወንድሙ በዔሳዉ በተሳደደ ጊዜ የኖሩት ለነጋቸዉ ነበር፤ ያዕቆብም ከመሰደድ ዮሴፍም ከግዞት ህይወት እንደሚወጡ በእግዚአብሔር ታምነዋልና።

ነገሮች ለአንተ አስቸጋሪ ከሆኑ ለራስህ ነገ መፍትሔ ይገኝላቸዋል ብለህ ንገረዉ። ከዚህም በኋላ ለዚህ ነገህ በፈገግታና በደስታ ኑር!!

(ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ)