Get Mystery Box with random crypto!

ከፈላስፋዎች ጉያ ሊቁ ኮንፊሽየስና ደቀ መዝሙሩ ትዙሉ ታላቁ የቻይና ፈላስፋና መምህር ኮን | የማለዳ ብስራት

ከፈላስፋዎች ጉያ

ሊቁ ኮንፊሽየስና ደቀ መዝሙሩ ትዙሉ

ታላቁ የቻይና ፈላስፋና መምህር ኮንፊሽየስ በተራራ ላይ ተቀምጦ ድንኳን ዘርግቶ እያስተማረ በነበረበት አንድ ቀን ደቀ-መዝሙሩ ትዙሉን ውሃ እንዲያመጣለት አዘዘው። ትዙሉም ውሃ ሊያመጣ ወደ ወንዝ ሲወርድ ነብር ያጋጥመውና ነብሩን ጭራውን ይዞ ይገድለዋል። በሰራው ጀብድም ኩራት ስለተሰማው የነብሩን ጅራት ቆርጦ ኪሱ ከቶ አምጣ የተባለውን ውሃ ቀድቶ ወደ ኮንፊሽየስ ድንኳን ይመለሳል። ኮንፊሽየስንም እንዲ ሲል ይጠይቀዋል ፦

ትዙሉ አንድ ታላቅ ሰው ነብርን እንዴት አድርጎ ይገድለዋል አለው?

ኮንፊሽየስም፦ አንድ ታላቅ ሰው ነብር የሚገድለው ጭንቅላቱን ይዞ ነው አለው።

ትዙሉ፦ተራ ሰውስ?

ኮንፊሽየስ፦አንድ ተራ ሰው ነብር የሚገድለው ጆሮውን ይዞ ነው ።

ትዙሉ፦የማይረባ ከንቱ ሰውስ?

ኮንፊሽየስ፦የማይረባ ከንቱ ሰው ነብር የሚገድለው ጭራውን ይዞ ነው ።

ትዙሉ የኮንፊሽየስን ምላሽ በሰማ ጊዜ ከድንኳኑ ርቆ በመሄድ የነብሩን ጭራ ከኪሱ በማውጣት ወረወረው ፤ በንዴት ውስጥም ሆኖ መምህሬ ከወንዝ አጠገብ ነብር እንዳለ እያወቀ የላከኝ በነብር ተበልቼ እንድሞትና እንድገደል ስለሚፈልግ ነው አለና ኮንፊሽየስን ለመግደል በኪሱ ድንጋይ ይዞ ሄደ። ኮንፊሽየስ ጋር በደረሰም ጊዜ በድጋሚም እንዲ ሲል ጠየቀ፦ አንድ ታላቅ ሰው ሰው ሊገድል የሚችለው እንዴት ነው አለ ትዙሉ ?

ኮንፊሽየስም፦ታላቅ ሰው ሰው ሊገድል የሚችለው የሚፅፍበትን ብዕር ተጠቅሞ ነው አለ።

ትዙሉም፦ተራ ሰውስ ሰው ሊገድል የሚችለው እንዴት ነው?

ኮንፊሽየስም፦ተራ ሰው ሰው ሊገድል የሚችለው ምላሱን ተጠቅሞ ነው አለው።

ትዙሉ ፦የማይረባ ከንቱ ሰውስ እንዴት ነው ሰው ሊገድል የሚችለው አለ?

ኮንፊሽየስም ፦ የማይረባ ሰው ከሆነ ሰው ሊገድል የሚችለው ድንጋይን በመጠቀም ነው አለ።

ትዙሉ የኮንፊሽየስን መልስ በሰማ ጊዜ አሁንም እንደ ቀድሞው ከድንኳኑ ርቆ በመሄድ መምህሩን ሊገድልበት የነበረውን ድንጋይ ወረወረው።

ትዙሉም ከዚያ ግዜ ጀምሮ የኮንፊሽየስን የእውነት ታላቅ ሰው መሆን አምኖ ተቀበለ ፤ መምህሩን የሚያከብር ተማሪም ሆነ።

አንድ ታላቅ ሰው በነብር የተመሰለውን የሱን ሀሳብ ተቃራኒ የሆነ ጠላት በጭንቅላቱ ይዞ ወይም በሀሳቡ በልጦት ያሸንፈዋል። ተራ ሰው ግን በነብር የተመሰለውን የሱን ተቃራኒ የሆነ ጠላት በጆሮ ይዞ በጣፋጭ ቃላት ደልሎ ያሸንፈዋል። በማይረባ ከንቱ ሰው ደግሞ በነብር የተመሰለውን የሱ ተቃራኒ የሆነ ጠላት በጭራው በመያዝ ከጀርባው ሆኖ በሀሜትና ስሙን በማጥፋት ያሸንፈዋል ።

በሀሳብ ለማሸነፍ እንሞክር

ለቻናሉ አዲስ የሆናቹ Join በማድረግ ተቀላቀሉ

@yemaledabisrat
@yemaledabisrat
@yemaledabisrat