Get Mystery Box with random crypto!

ጠብታ እውነተኛ ፍቅር አንድ ሰው ቆንጆ ልጃገረድ አገባ። እሱም በጣም ይወዳት ነበር | የማለዳ ብስራት

ጠብታ

እውነተኛ ፍቅር

አንድ ሰው ቆንጆ ልጃገረድ አገባ። እሱም በጣም ይወዳት ነበር፡፡ አንድ ቀን የቆዳ በሽታ ያዛት፡፡ ቀስ እያለች ውበቷን ማጣት ጀመረች፣ ያሰጨንቃትም ጀመር፡፡

አንድ ቀን ባልዋ ለጉብኝት ራቅ ወዳለ ስፍራ ሄደ፡፡ በሚመለስበት ጊዜ አደጋ አጋጠመውና ማየት አቃተው፡፡ ሆኖም የጋብቻ ሕይወታቸው እንደተለመደው ቀጠለ፡፡ ቀናት እያለፉ ውበቷ ደረጃ በደረጃ እየባሰ፣ ሙሉ ወበቷን አጣች፡፡ ዓይነ ስውር ባል ይህንን አያውቅም እናም በትዳር ሕይወታቸው ውስጥ ምንም ልዩነት አልነበረም፡፡ እሷም እሱን መውደዷን ቀጠለች እሱም በጣም ይወዳት ነበር፡፡

አንድ ቀን በድንገት ሞተች፡፡ ድንገት መሞቷ ታላቅ ኀዘን አመጣበት፣ ኀዘኑም ሲበረታበት ከዚያች ከተማ ለመልቀቅ ፈለገ፡፡ በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች “አሁን እንዴት ብቻውን መሄድ ይችላል? ሚስቱ ነበር የምትረዳው፡፡” ብለው ይወያዩ ነበር፡፡ ሰውየውም “አይነስውር አይደለሁም ብሎ መለሰ፡፡ ይህን ያህል ጊዜ የማላይ መስዬ ነበር የቆየሁት፣ ምክንያቱም የቆዳ በሽታ እንዳለባት አውቅ ስለነበር የሷን ስሜት እንዳይጎዳ ብዬ ነው፡፡ ውበቷ ሲጠፋ መጨነቅ ስለጀመረች ምንም እንዳልሆነ እንዲሰማት ነበር፡፡ ስለዚህ እንደማላይ ነገርኳት፡፡ እሷ ለኔ በጣም ጥሩ ሚስት ነበረች፡፡ እሷን ደስተኛ ማድረግ ብቻ ነበር የምፈልገው አላቸው!

አንዳንድ ጊዜ አይተን አውቀን እንዳላየን ልናልፋቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ስናልፋቸው፤ በዙሪያችን ካሉ ሰዎችን ጋር ያለን መልካም ግንኙነት እንዲጠነክር ይረዳል፡፡

ለቻናሉ አዲስ የሆናቹ Join በማድረግ ተቀላቀሉ

@yemaledabisrat
@yemaledabisrat
@yemaledabisrat