Get Mystery Box with random crypto!

¶ጥሎሽ (ነግቶ ነው መሰል አልነጋ አለኝ!) ክፍል 1 | የቃል ጠብታ

¶ጥሎሽ

(ነግቶ ነው መሰል አልነጋ አለኝ!)
ክፍል 1

(በልቦለዱ ውስጥ የገጸ ባህሪ ስምና ባህሪ ቢመሳሰል አጋጣሚ እንጂ ሆን ተብሎ የተደረገ እንዳልሆነ ይታወቅ። )

ነግቷል። መንጋቱን ያመንኩት አይቼ አይደለም ሰምቼ ነው።ዶሮ ነገረኝ። ወፍ ነገረኝ።

እንደነጋ ቢየገረኝም ግን ምንም የሚታይ ነገር የለም። ሁሉ ነገር የተዳፈነ ጭለማ ነው። ምክንያቱም ተሸፋፍኜ ተኝቻለሁ። ለካ ስለነጋ ብቻ አይነጋምም።

ተኝተው በሚነቁበት በዚህ በዚህ ዘመን ሲቀርብም በዚህ ሰዓት ሰው ነቅቶ ይተኛል?

የኔን ንጋት የሚያውጅልኝ ተፈጥሮ አይደለም። ንጋቴ ልቤ ውስጥ እምነቴ ውስጥ ነው ያለው። ልክ ከአልጋዬ ስወርድ ያኔ ለኔ ይነጋል። ተፈጥሮ ግን ይጨልማል። መነሳት ስለማልፈልግ መነሳት አልችልም። አለመፈለግ መቻልን ይገድለዋል። ስንት ዘመን ላርፍድ። አለማርፈድ አልፈልግም ለምን...

"መሌ!"

እናቴ ናት። ቁርስ ደርሷል ማለት ነው። ከዶሮ እና ከወፎች ባሻገር መንጋቱን የሚያሳውቀኝ የእናቴ ጥሪ ነው። እናቴ ሳትኖር ግን መንጋቱን በምን አውቅ ይሆን? መቼም ንጋቴን እንዳላምን ተስፋዬን የነጠቀ አምላክ እምነቴን ከኔ ያሸሻል ብዬ አላስብም።

"መሌ!"

ዝም አልመለስኩም።

"ልጄ!"

ጭጭ

"አባ!"

እ... ድምጽ አሰማሁ። እንቅልፌን አልጨረስኩም እንደማለት።

"ተነስ አባዬ ቁርስ ደርሷል።"

ትንሽ ልተኛ እንጂ

"ከዚ በላይ እስከ ስንት ሰዓት ልተኛ አሰብክ። አንተ እንደፈለክ ግን በብዙ ስተኛ ፍራሹ ያልቃል። ፍራሹ ከሳሳ እንደ ብርድ ልብስ ለብሰህ መሬት ላይ ትተኛለህ እንጂ ፍራሽ የሚገዛህህ የለም።"

አረ እማዬ! ምንድነው

"አረ አትበለኝ! ይኸው ሻይ አፍልቻለሁ። ዳቦ ደግሞ መሶቡ ዎ
ውስጥ አለ። ከፈለክ ጎረቤት ሄደህ ወጥ አስጨምረህ ቁርስህን ብላ። ካልበላህም ጥሩ ነው ለምሳ ይሆንሃል።"

የማጠጋጋት ህግ መሆኑ ነው?

"ስም መስጠት ላይማ ጎበዝ ነህ። ለማንኛውም እየወጣሁ ነው በሩን ዝጋው። ቶሎ ሳትነሳ ሻዩ ቀዝቅዞብህ ድጋሜ ለማሞቅ ከሰል አያይዛለሁ ብትል ውርድ ከራሴ!"

እንደውም እማዬ ርብቃ መጥታ እሳት አያይዛ ቤቱን ሞቅ ብታደርገው ደስ ይለኝ ነበር።

እንደዛማ የሚያደርገው ወንድ የሆነ ሰው ነው። አንተ ዝም ብለህ ተጋደም በል ሻዩን ቀድቼልሃለሁ። ቤት ጥለህ ደግሞ እንዳትወጣ! ካልሆነም ቤቱን ቆልፈህ ቁልፉን ጎረቤት አስቀምጥልኝ።

ብርድ ልብሴ በትንሹ ገለጥ አድርጌ ሳያት በሩን ገርበብ አድርጋ ወጣች። በበሩ ቀዳዳ የሚገቡ የጸሐይ ጨረር ቤቱን ዲም ላይት የተለክሰበት አስመሰሉት።

እናቴ ከቤት ስትወጣ ገላዋን ፀሐይ ሲነካት ተሸሽጎ የነበረው ጥላ መሬት ላይ መሳል ጀመረ።

እንደ ጥላ ፈሪና እንደ ጥላ ክፉ አለ?


አልጨረስኩም ለነገሩ መች ጀመርኩና!


¶መላኩ ነኝ!


@yekal_tebta
@DBU111 Discussion
@Dbu11 Daily news
@dbu_entertain Entertainment on telegram

Subscribe our youtube channel

https://youtube.com/channel/UCAS829K6929J4CVsxrwsyzA
@dbudailyaskbot