Get Mystery Box with random crypto!

አናማርር! እንታገስ!! ቆሮንቶስ 10:13 ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም | ይሰበካል የእዉነት ወንገል

አናማርር! እንታገስ!!

ቆሮንቶስ 10:13
ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው።
ትታገሱም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫን ደግሞ ያደርግላችኋል።

አብዛኛውን ጊዜ በተለያየ የሕይወት ፈተና ውስጥ እንወድቃለን ብዙ እንገላታለን አልፈንም እስከማማረር ድረስ እንደርሳለን።

አምላክ ለምንድነው እኔን ብቻ የሚፈትነኝ?
የማልችለውን በዛ ላይ በጣም ከእኔ አቅም በላይ የሆነ ፈተና ለምን ያመጣብኛል?

ሌሎች በስላም እየኖሩ ሁል ጊዜ እኔን ፈተና አያጣኝም እያልን እናማርራለን።

እስቲ ከላይ የተጠቀሰውን ጥቅስ ልብ ብለን እንይ
ይህን ጥቅስ ስናይ ብዙ ነገሮችን እንረዳለን።

ለሰው ሁሉ ከሚሆን በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም ይላል። ይህ ማለት ማንም ሰው እንደሚፈተነው ሁሉ እኛም ተፈተንን እንጂ ፈጣሪ እያዳላ አንዱ ላይ ፈተና እያዘዘ ሌላኛውን የማይፈትን አይደለም ሁላችንም ልጁ ነን ጌታ ለሁሉ እኩል ነው የእንጀራ አባት የሆነለት ሰው የለም ስለዚህ እኛን ብቻ ለይቶም እንደሚፈትን አድርገን መቁጠር የለብንም።

ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው። ይላል እዚህ ጋር የምናየው ሁላችንም በአቅማችን ልክ እንደምንፈተን ነው። ግለሰቡ ከሚችለው በላይ ፈተና አይታዘዝበትም በትንሽ ፈተና የምንሰበር ሰነፎች ከሆንን አንደ እዮብ ሚስት እግዚአብሔርን ለመሳደብ ይቃጣናል ማለት ነው። ጠንካሮች ከሆንን ደግሞ እንደ እዮብ እስከመጨረሻ እንፀናለን። ልብ በሉ ጥንካሬአችን በበዛ ቁጥር ፈተናችንም በዛው መጠን እየጨመረ ይመጣል አንድ ክፍል ገብቶ ተፈትኖ ያለፈ ተማሪ ለቀጣዩ ፈተና እራሱን ማዘጋጀት አለበት ክፍል እየጨመረ በመጣ ቁጥር ፈተናውም እየጠነከረ ይመጣል ማለት ነው ጎበዙን ከሰነፍ ለመለየት ፈተና የግድ ነው።

ትታገሱም ዘንድ እንድትችሉ ...
የትእግስታችንን ደረጃ ወይም አቅም ለመለካት እንደምንፈተን ይናገራል።
እግዚአብሔር ምን ያህል ጠንካራ እና ብርቱ እንደሆንን ለማወቅ በተለያየ አጋጣሚ የተለያየ መሰናክሎችን እያመጣ ይፈትነናል ነገር ግን እኛን ብርቱዎች እና ጠንካሮች ለማድረግ እንጂ እሱ ባመጣብን መሰናክል ተደናቅፈን ወድቀን እንድንቀር አይደለም።

ከፈተናው ጋር መውጫን ደግሞ ያደርግላችኋል።
ይህ ማለት ሁሉም ሰው አቅሙ እስከቻለው ድረስ ተፈትኖ ስያበቃና መድከሙ ሲታይ አቅሙ ምን ያህል እንደሆነ በትክክል ከተረጋገጠ ቦሀላ ከዛ ፈተና እንዴት መውጣት እንደሚችል ጌታ ዘዴ ይሰጠዋል ማለት ነው።
እስቲ ማነው ወደፈተና ገብቶ በራሱ ሀይል ከገባበት ፈተና መውጣት የሚችል? እንደውም በእራሳችን መንገድ ከፈተናዎቻችን ለመውጣት ጥረት ማድረግ ስንጀምር ነገሮች የባሱ ይሆናሉ። እንደውም ጭራሽ የማንችለው ፈተና ይጨመርብናል። ነገር ግን ይህን ፈተና እኔ አልቻልኩም ከእኔ አቅም በላይ ነው ብለን ተደፍተን ብናነባ እና የከበደንን በጌታችን ፍት ጥለን አንተ እወቅልኝ ብንለው ከአቅማችን በላይ እንድንፈተን ስለማይፈልግ ፈጥኖ ሸክማችንን ያቀልልናል።

ፀሎት
አምላኬ ሆይ እኔ ደካማ ፍጡር በመሆኔ በገባሁባቸው ፈተናዎች ሁሉ እያማረርኩ አንተን አሳዝኜሀለሁ። አንተ በእኔ ላይ ያለክ አላማ ፍቅር እንደሆነ ተረድቻለሁ። የምፈተነውም ለመልካም እንጂ ለውድቀት ስላልሆነ ለፈተናዎች ሁሉ እጄን እንዳልሰጥ አንተ አበርታኝ።
መውጫ ቀዳዳም እየሰጠህኝ የምስጋና ሰው አድርገኝ።
በኢየሱስ ስም አሜን።

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH

የመወያያ ግሩፕ @marantawoch