Get Mystery Box with random crypto!

Love is the answer “All you need is love.” ~ John Lennon በአብ | የሀሳብ መንገድ

Love is the answer

“All you need is love.” ~ John Lennon

በአብሮ መኖር ሸንጎ ውስጥ ከባለቤቱ ፍቃድ ውጭ ልታደርግ የምትችለው ብቸኛ ነገር ማፍቀር ነው… ለማፍቀር ፍቃድ አያስፈልግህም… ማስገደድም ጭምር!!

ጎረቤትህን ልትሰርቀው ትችላለህ፣ ተቀናቃኝህን ልትገድለው ትችላለህ፣ ወዳጅህን ልትበድለው ትችላለህ… ከሌላኛው ሰው ፍላጎት ውጪ ብዙ Negative ነገሮች ልትፈጽም ትችላለህ… ሁሉም ግን እንደ ሁኔታው Consequence አላቸው… ቢያንስ ሕሊናህን ሲኮሰኩሱ መኖራቸው አይቀርም… ለማፍቀር ግን ፍቃድ አያስፈልግህም… በየትኛውም የጊዜና ቦታ ርቀት ውስጥ ያለን ሰው ማፍቀር ትችላለህ… በማንኛውም የኑሮና የስታተስ ደረጃ ላይ ያለን ሰው መውደድ ትችላለህ…

ማፍቀር Risk የለውም… ያኛው ሰው ሲያውቅም ሳያውቅም ማፍቀር… ሲረዳህም ሳይረዳህም ማፍቀር… ግድ ሲያጣም ግድ ሲለውም ማፍቀር… ያለ ስሌት ማፍቀር… ምክንያት አልባ ሆኖ ማፍቀር… ሳይጠብቁ ማፍቀር… ይሄ ፍቅር ሪስክ የለውም…

ይልቅ ጓደኝነት ፍቃድ ይፈልጋል… ውስጡ መዋደድ ቢኖርም መፈላለግን ይፈልጋል… አብሮነት በጓደኝነት ውስጥ የሚጸናው የሁለቱን ወገኖች ፍቃድ ሲያገኝ ብቻ ነው… Request ትልካለህ Confirmation ትጠብቃለህ… ፍቅር ግን እንዲህ አይደለም… አስፈቅደህ አታፈቅርም… ዝም ብለህ ትሰጣለህ እንጂ… መልሶ ከመጣ እሰየው… መልስ ስለሌለ ግን ፍቅር አይሞትም…

“Being deeply loved by someone gives you strength while loving someone deeply gives you courage.” ― Lao Tzu

@yehasab_menged
@yehasab_menged