2022-02-15 21:43:24
ብቸኝነቴን መልሺልኝ
ክፍል 13
ከዳኒ የወሰን ልጅ
.
.
.
የሰላም ባል አድማሱ ወደ ቢሮዋ ግራ በመገባት ስሜት ውስጥ ሆኖ በመሄድ
በሩን አንኳኩቶ በመክፈት ገባ እና መልሶ ዘጋው ። በንዴትና በተረበሸ ስሜት
ውስጥ ሆና በጨረፍታ አይነት ስሜት ተመለከተችው ። እሱም አያትና
" ስሜትሽ ጥሩ አይመስለኝም " አላት
" ያልበላህን አትከክ ...... ለመሆኑ ሰራተኞቹን አሳምንካቸው "
" ሁሉም አምፀዋል ሌላ ድርጅት ስራ ጀምረዋል "
" ሲጀመር አንተ እራስህንም ማሳምን አትችልም .... በፍጥነት ሌላ የስራ
ማስታወቂያ አውጣልኝ እና ቶሎ ብለህ ቅጠርልኝ እሺ አሁን ጨርሰናል ከቢሮዬ
ውጣልኝ " አለችው በቸለልተኛ ስሜት ። እሱ በግርምት ተመለከታት እና ።
" ኬብሮን ከዚህ ሲወጣ አየሁት ምን አዲስ ነገር አለ ?"
" ከጎሮቤቱ ጋር ሰርካለም ከምትባልዋ ጋር ፍቅር ጀምሯል የምትሰራበትን ቦታ
ነግሮኛል የቅርብ ጓደኛዬ ነው ከስራ እንዲያባርራት አሁኑኑ ሄጄ እነግረዋለው ድሀ
ለድሀ ከዛ አብረው እንዴት መሄድ እንደሚችሉ ቁጭ ብሎ ማየት ነው"
" ግራ የገባኝ ነገር የሁለቱ መፋቀር አለመፋቀር አንቺን ምን አስጨነቀሽ "
በግርምት ሲያያት ከቆየ በኋላ ።
" ምንም ነገር እንዲሳካለት ስለማልፈልግ የእሱ ስኬታማ መሆን ለእኔ ውድቀት
ነው ...... ይሄ የእኔ ጉዳይ ነው"
" አሀ ዛሬም ድረስ ሚካኤልን ታፈቅሪዋለሽ ማለት ነው ?" አላትጨአይን አይኗን
ሲያያት በንዴት እና በብስጭት አየቺውና ።
" እኔ እኮ ከእንዳተ አይነት ጨው እራስ ጋር አብሬ መሆኔ ነው የሚያናድደኝ .....
ውጣልኝ ከዚህ አሁን " ቃላቶቿ ብስጭት እና ንዴት ያዘሉ ባይሆኑም ከውስጧ
እንደ እሳት የሚነድ ንዴት ውስጥ እንደሆነች ፊቷ ያሳያል።
" እንደዚህማ ልታቋሺሺኝ እንደ ቆሻሻ ከቢሮሽ እንድትጠርጊኝ እና እንድታስወጪኝ
አልፈልግም ... በዚህ ድርጅት በጠቅላላ በሀብት ንብረትሽ የኔ ድርሻም
ሀላፊነትም አለብኝ " አላት አድማሱ የእውነት አናደዋለች ከሚካኤሌ ይህንን ሁሉ
ሀብት ዘርፋ እጇ ስታስገባ ከጥንስሱ ጀምሮ የበለጠው ሴራ እንደውም የእሱ
ነበር ይሀው አሁን ካገኘች በኋላ ተጋብተን አብረን እንኖራለን እንዳላለች አሁን
እንደ ምራቋ ሀክ ቱፍ ብላ እየተፋቺው ነው ካለ ምንም ጥቅም። ሰላም ደግሞ
የእሱ እንደዚህ ማለቱ እንደ ፌጣ ከተቀመጠችበት ፍንጥር ብላ በመነሳት
አይኖቿን አፍጣ ከንፈሮቿ እየተቀጠቀጡ።
" አቤት ... ምን አልክ አለህበት እንዴ? አንድ ብር አይደለም አንድ ሳንቲም ላይ
የለህበትምም አታገኝም " አለች በንዴት
" እረ ያ ማለት ከእኔ ጋር የመኖር ልጅ የመውለድ እቅድ የነበርሽን ሁሉ
ሰርዘሺዋል ማለት ነው " አላት ተስፋ ቆርጦ።
" እረ በፈጠረህ ሲጀመርም ከአንተ ጋር ለመኖር ፍላጎትም የለኝም እንዲሁ
እንድታልመው ብዬ ነው እሺ ልጅህን ያው ከአዳሪ ትምህርት ቤቷ ለዕረፍት
ስትመጣ አንተም እየመጣህ እያት እፈቅድልሀለው ከዛ ውጪ የእኔን አይን
እንዳታይ ውጣልኝ " አለች የመጨረሻውን ቃል እንደ መብረቅ እየጮሀች
አቧረቀችበት።
" እወጣለው ግን አንድ ነገር ልንገርሽ " አላት ወደ እሷ ጠጋ ብሎ።
" አትንገረኝ ስለ ልጃችን ረድኤት ልትነግረኝ ነው እሷን ከአንተ ጋር ተኝቼ
መውለዴ አይፀፅተኝም ለምን ያኔ የምበላው ያጣው ድሀ ነበርኩ አንተ ደግሞ
ከየትም ብለህ ይሄን ችግሬን የምትሸፍንልኝ ስለዚህ ማድረግ ያለብኝን አርጌ
ልይዝህ ይገባ ነበር ያስኩሁ እና ተጠቀምኩብህ አሁን ግን ያ ሁሉ አልፏል ከፊቴ
እንድትርቅ ነው የምፈልገው አንተ አትመጥነኝም የሚመጥነኝ ሰው እፈልጋለው "
አለች እሱ እንዲበሽቅ ያልመጣባትን ያላስቸገራትን ሳቅ በግድ እየሳቀች እሱ ግን
አልተናደደም ፈገግ አለና ።
" ትልቅ ስህተት ተሳሳትሽ ይሄ ስህተትሽ ደም ያስለቅስሻል ከሚኪ ይህንን ሀብት
የቀማሁበትን ሴራ ጠንከር አርጌ ወደ አንቺ አዞረዋለው እመኚኝ ለማንኛውም
ደህና ሁኚ " ብሏት በንዴት በሩን ከፍቶ ወርውሮት ሲዘጋው እሷ ቀሀይለኛው
እየሳቀች ነበር።
ኬብሮን ከመአዛ ጋር በስልክ እያወራ ሲለው በግርምት ሲስቅ ሲለው ደግሞ
ሲናደድ አጠገቡ አብሮት እየተራመደ በሚናገረው ነገር እየሳቀበት ያለውን
ሚካኤሌን እያየው ሲያወራ ቆይቶ በመጨረሻ በሰላም ስልኩን ዘግቶ ሚካኤልን
ተመለከተው እና
" እኔ የምልህ ሚኪ 100 ቁጥር ሚስማር አለ እንዴ " አለው።
" ደሞ መቶ ቁጥር ሚስማር አለ እንዴ? " አለው በፈገግታ።
" ለምን አያመርትም ፋብሪካዎች ቢኖር ወደ እኔ የሚመጡቱን ሴቶች እግራቸውን
በአናፂዎች በደንብ ነበር እግር ከእግራቸው አቆላልፌ የማሳስረው አፋቸውንም
ከእኔ ጋር ብቻ እኔዳያወሩ አርጌ በሀሚር የማጣብቀው "
" ተው አይባልም አንድ ቀን ያስፈልጉሀል ኬቡ " አለው
" እረ መቼም አያስፈልጉኝም ምንምም አልፈልግም እነሱ ... ሆሆ እነሱ " አለው
በምሬት ። ግን ቤታቸው ደርሰው ደረጃውን እየወጡ ስለነበር ።
" ይልቅ ይሄ የማይረባ ወሬህን ተወውና አሁን እኔን እናቷ ስታየኝ ስለምትሳደብ
አንተ አንኳኳና ስለ ልጅቷ ጤንነት ጠይቅ እሺ እኔ እውነት ደብሬያት ከሆነ ክችች
ማለትን ስላልፈለኩ ነው " አለው በትህትና
" አንተን እናትየው ብቻ ነችጨእኔን ግን እህትየውም ጭምር ነች በምን ጫቃዬ
እችላለው አልሄድም " አለ በብስጭት
" የአንተ እህትየው የፍቅር ነው እባክህ " ብሎ ለደቂቃ ሚካኤሌ እየለመነው
ኬብሮን ቀእንቢታ ቆየና በመጨረሻ እሺ ብሎት ሚካኤሌ ወደ በራቸው እየሄደ
ኬብሮን ሁለት ጊዜ ሲያንኳኳ ሰርካለም እንቢ አላረጅም ያለች አክስት አለችኝ
ያለችው ሴትዮ ወ/ሮ ተዋበች መጥተው ከፈቱ። እድሜያቸው 60ዎቹ አጋማሽ
ላይ ይሆናሉ ፊታቸው በሜካፕ ፀጉራቸው በቀለም ተለውጧል ከአይናቸው ኩልና
ከከፈራቸው ቀይ ሊፒስትክ አብዝተው ተለቅልቀዋል በጡት ማስያዣ በትንሹ
ጡታቸው እያሳዩ ወጥረውታል በቦዲ ሰውነታቸው ተገላልጧል አጉልበታቸው
በላይ የሆነ ጉርድ አርገዋል ። ብርድ ልብስ የሚያክል ማስቲካ በአፋቸው ውስጥ
እያላወሱ ያቋቁታል ። ኬቡን እንዳዩት ።
" እንዴት ነው የምታምረው የኔ ቆንጆ " አሉት በፈገግታ ከጉልበታቸው ሰበር ሰካ
እያሉ በፈገግታ ። ኬብሮን ደነገጠ ዙሪያውን አየና ሚካኤሌን ሲያየው እየሳቀ ነው
የእሱም ሳቁ መጣ በግርምት እየሳቀ አያቸውና ።
" እኔን ነው?" አለ በጣቱ ጭምር ወደ ልቡ እያመላከተ።
" አዎ የኔ ፍቅር ቅመም የሆንሽ ልጅ ትመስይኛለሽ ግድ የለም በምቾት ስቃይህን
አሳየሀለው ብቻ እንመቻች " አሉት። ኬብሮን የምር ደነገጠ ግራ ተጋባ ፊቱን
ዘወር አርጎ።
" ጌታዬ ሆይ የባስ አታምጣ " አለና ሚኪን አየው። ....
ይቀጥላል...
╔═══❖• •❖═══╗
@yegna_yegna
╚═══❖• •❖═══╝
❥❥ ⚘ ❥❥
72 viewsZizu, 18:43