Get Mystery Box with random crypto!

TECH TALK

የቴሌግራም ቻናል አርማ yegna_yegna — TECH TALK T
የቴሌግራም ቻናል አርማ yegna_yegna — TECH TALK
የሰርጥ አድራሻ: @yegna_yegna
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 53
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን ወደ TECH TALK ደና መጡ
😗😗በዚህ ቻናል ድንቅ ድንቅ ስራዎች ይቀርባሉ
👉አስደናቂ ታሪኮች
👉ግጥሞች
👉የተመረጡ መጽሐፍቶች እና ሌሎች የሚቀርብበት ቻናል ነው
💗አላማው የሰው ልጅ ከሁሉም ፍጡር የሚበልጥጠት
ኣእምሮ እና ልብ የሚያጠነክሩ እና የሰው ልጅ ልዩ ስጦታው እየተጠቀመበት እንዲኖር
የሚያደርጉ ሀሳቦች ማጋራት ነው።💜
👉ለማንኛውም አስተያየት @Abitiim

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-29 12:35:21 Top 3 Differences Between Rich and Poor

1. The poor always limit themselves in their dreams. For the rich, nothing is unattainable. They set a goal and go for it.

@yegna_yegna


2. After they get their salary, the poor usually try to spend it all. The rich are very practical with their finances.
The key word here --- is practical.

3. The poor always find excuses for their constantly empty wallet: "the boss is a fool, the government is bad," etc. The rich know that much in this life depends on themselves.
14 viewsÀbiti, 09:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 12:33:32 አንዲት የሥነ ልቦና ፕሮፌሰር ተማሪዎችን አዳራሽ ውስጥ ሰብስባ የጭንቀት አያያዝ መርሆዎችን
መድረክ ላይ በማስተማር እያለች፣ አጠገቧ የተቀመጠውን ውሃ የያዘ ብርጭቆ ከፍ በማድርግ ለሁሉም ተማሪዎች አሳየች ፣ ተማሪዋቹም ‹ብርጭቆው ግማሽ ባዶ ነው ወይስ ግማሽ ሙሉ› የሚለውን የተለመደ የፍልስፍና ጥያቄ ትጠይቃለች ብለው ይጠብቁ ነበር ፡፡ እሷ ግን ይልቁንም በፈገግታ “እኔ የያዝኩት ይህ የውሃ ብርጭቆ ምን ያህል ከባድ ነው?” ስትል ጠየቀች፡፡

ተማሪዎቹ የተለያዩ ግራሞችን በመጥራት የለያዩ ምላሾችን ሰጡ፡፡

እሷም “በእኔ እይታ ግን የዚህ ብርጭቆ ትክክለኛ የክብደት ቁጥር ምንም ፋይዳ የለውም፡፡ የክበደቱ ውጤት የሚወሰነው ብርጭቆውን
ምን ያህል ጊዜ እንደያዝኩት ሲታወቅ ነው ፡፡ለአንድ ደቂቃ ከያዝኩት በትክክል ቀላል ነው ልል እችላለለሁ፡፡ ለአንድ ሰዓት ያህል ከያዝኩት ክብደቱ ክንዴን ትንሽ ሊያሳምመው ይችላል። ለአንድ ቀን ቀጥ አድርጌ ከያዝኩት ደግሞ ክንዴ ሙሉ በሙሉ ሊደነዝዝ እና ብርጭቆውን ወደ ወለሉ እንድጥል ያስገድደኛል። በእያንዳንዱ ሁኔታ ፣ የብርጭቆው ክብደት አይቀየርም ፣ ግን ባቆይሁት መጠን ለእኔ የበለጠ ክብደት እየተሰማኝ ይሄዳል፣። '

ክፍሉ እርስ በእርስ መስማማታቸውን ጭንቅላታቸውን በመወዝወዝ አሳወቋት፣

እንዲህ ስትል ቀጠለች : - 'በሕይወታችሁ ውስጥ ያሉት ጭንቀቶች እና ፍራሀቶች በዚህ የውሃ ብርጭቆ ሊመሰሉ ይችላሉ ፡፡ አንድን ነገር ፈፅማችሁ ሁኔታውን ካለፋችሁ በውስጣችሁ ምንም ነገር አይከሰትም።ስለሁኔታው ትንሽ ማሰብ ስትጀምሩ ትንሽ መታመም ትጀምራላችሁ።ቀኑን ሙሉ ስለሁኔታው በሀሳብ መዋለል ከጀመራችሁ ልክ እንደ ብርጭቆው መደንዘዝ ይከተላል፣
ስትል አስተማረቻቸው።



በየቀኑ አዳዲስ የሆኑ እድል ይሰጡናል። የትናንት ጭንቀቶች አጥብቀን ምንሸከም ከሆነ ግን ዛሬን በሙሉ ሀይላችን መኖር አይቻለንም ።አንዳንድ ቀን እቅዶቻችን እንዳሰብናችው ላይሆኑ ይችላሉ፣ አንዳንዴ ካቅማችን በላይ የሆኑ ስራዎችን ወስደን ያሰብነውን ያህል ባለማጠናቀቅቃችን እንሰቃያለን ፡፡አንዳንዴ ደግሞ ያለጠበቀናቸው ነገሮች ትኩረታችንን ፈልገው ወደ እኛ ይመጣሉ ፡፡


ልብ በሉ እነዚህ ሁሉ የሕይወት የተለያዩ ክስተቶች ናቸው። በቀናችን ውስጥ የሚገጥሙንን ማናቸውም የሕይወት ሁኔታዎች ወደድንም ጠላንም ማስቀረት አንችልም ፡፡አንዳንድ ቀኖች በጣም ደስተኛ ያረጉናል ፣አንዳንዶቹ ደግሞ ይበልጥ ፈታኝ ይሆኑብናል።

የተፈጠረውን ማንኛውንም ነገር መቀበል እና ከሁኔታው ጋር እርቅ መፈጠር ግን ብልሀት ነው ፡፡ በዚህ ታላቅ የሕይወት ሚስጥር ለመቆየት ከትላንት ጭንቀቶች መላቀቅ አለብን ፣ትኩረታችንን ወደ አሁን መልሰን ማደረግ ምንችለውን ማስተዋል ይገባናል፣ በነበር እና በይሆናል መጨነቅ ችግራችንን አንድ እርምጃ አይፈታልንም ፡።

ይህንን ጽሑፍ በምታነብበት ጊዜ እንኳን የቱንም ያህል ቅርብ ይሁን ሩቅ ያለፍውን ነገር መተው ትችላለህ፡፡
እራስህን ወደሚመጣው አዲስ እድል ክፈት፣በዚህ ውድ ጊዜ እራስህን ሁን፣ትናንት ቀድሞውኑ አልፏልና ያለፈውን ተወው።

ሕይወትን አስደሳች እና ቀላል አርጎ መኖር ይችላል።የተሸከመከውን የሀሳብ ክብደት ለመተው ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅብሀል ፣የሕይወት እውነተኛ ክስተት አሁን ነው። አሁን ባለህ ጊዜ ሰላም ፍጠር! ዛሬን እንደዛሬ በአዲስ ለመመልከት ፣ትናንትህን መልቀቅ ይኖርብሀል ።

አንተ አሁን ላይ ሙሉ ሰው ነህ ፣ዘና በል።

ሰውየው

@yegna_yegna
14 viewsÀbiti, 09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 15:20:27 Live stream finished (1 minute)
12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 15:19:15 Live stream started
12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-10 13:30:39 ብቸኝነቴን ...... መልሺኝ

ክፍል ሀያ ሶስት (23)
.
.
.
በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ከምርመራ ቢሮ በር ላይ ማክዳ ተቀምጣ በር በሩን
ትመለከታለች። ውስጥ ደግሞ ኬብሮን በመርማሪ ፖሊስ በጥያቄ እያፋጠጡት
ነው መርማሪዋ ሴት ነች በጥላቻ ነው የምታየው ኬብሮን ደግሞ በሄደበት ሁሉ
ሴት የሚያጋጥመው ለምን እንደሆነ ግራ ገብቶታል ።
" አንተ የሰውን ነፍሰ ጡር ሚስት ማስኮብለል አይደብርህም አንተ ወንድ
አይደለህም እሷን ብታገባት ለአንተስ ታማኝ ትሆናለች የእኔ አይጥ የሆንክ ልጅ "
አለችው መርማሪዋ
" እረ በፈጠራቹሁ እኔ አላስኮበለልኳትም " አለ በልመና
" እና እኔ ነኝ ያስኮበለልኳት " አለች በቁጣ እያየቺው።
" እሱንማ እኔ ምን አውቃለሁ"
" ማወቂያህ ይደፈን አሁንም... ስለተደፈነ አይደል የሰው ሚስት የቀማሀው አሁን
እውነቱን ብታወራ ይሻልሀል"
" እሷ ነች ያስገደደቺኝ እውነቴን ነው" ሲላቸው እየተያዩ ሳቁበት እና መርማሪዋ
ወደ እሱ ቀረብ ብላ።
" እስቲ ከመጀመሪያ ጀምሮ አንተ አዲስ አበባ እሷ ክ/ሀገር ሆና የት አጊተሀት
እንዴት ለዚህ በቃቹሁ እውነቱን" አለችው በማስጠንቀቅ።
" እሺ ትውውቃችን በፌስ ቡክ ነው ማን የጓደኝነት ጥያቄ እንደጠየቀ አላውቅም
አንድ ቀን ሰላም አለቺኝ መለስኩላት እኔ በተፈጥሮዬ ሴትን ማወራት ደፋር
አይደለሁም f.b ላይ ሴቶቹ ልታናግራቸው ሀይ ስትል " ምን አባህ ፈለክ "
ስለሚሉኝ እነሱ ካላናገሩኝ ደፍሬ እኔ አላናግርም ስራ ስለሌለኝ ሁሌም ቀንም
ለሊት ኦን ላይን ላይ ነኝ ብዙ ጊዜ አነባለው ፊልም አያለው እንጂ ከሰው ጋር
አላወራም....."
" እኔ የአንተን እንቅልፋም ታሪክ አልፈልግም ከእሷ ጋር ስላለህ ግንኙነት እንጂ "
አለች መርማሪ ቆጣ በማለት።
" እሺ .... እናም ሰላም አልቺኝ መለስኩላት የማወራው ጠፋኝ ዝም አልኳት
ሁለቴ ሶስቴ ስታናግረኝ ጨዋታውም መጣልኝ ባለ ትዳር መሆኔን ጠየቀቺኝ
አይደለሁም አልኳት እሷም ስጠይቃት እንዳልሆነች ነገረቺኝ ጎበዝ ነጋዴ
እንደሆነች ነግራኝ እኔን ስትጠይቀኝ ጎበዝ ቦዘኔ በረዳ አዳሪ አይዞህ እንረዳዳለን
ባይሆን ሸገር ስመጣ ታስጎበኘኛለህ አለቺኝ ከዛ በስንተኛው ቀን 10 ሺህ ብር
ልኬልሀለው ሂድና ከባንክ አውጣ እራስህን ቀይር ቤት ተከራይ ስትለኝ
አላመንኩም ስልኩ እንደተዘጋ ወደ ባንክ እሮጥኩ ይህን ያህል ብር ሰው እጅ ላይ
እንኳ አይቼ አላውቅም ደግሞ እንዴት በአካል ለማታውቀው ይሄን ሁሉ ብር
ትልካለች ብዬ አይምሮዬን እያጨናነኩ ስሄድ ብሩ እውነት ነበር ደስ አለኝ"
" ደስ ብሎህ ተቀበልክ አይደል ?" አለቺው መርማሪዋ
" አዎ እንደ እኔ አይነቱ ሾላካ ድሀ አይደለም የትኛውም ሀብታም ቢሆን እንቢ
አይልም ... እረ ቆይ አንቺ እንቢ ትያለሽ መርማሪ እ?" አላት ኬብሮን
መርማሪዋም ዘወር ዘወር ብላ ሌሎች መርማሪ ፖሊሶችን አየችና በቁጣ።
" ዝም ብለህ የተጠየከውን መልስ እኔን አትጠይቅ አለችው "
" ....... ያኔ በጣም አመሰገንኳት ከልቤ ለእኔ አዝና ስለመሰለኝ ከትንሽ ቀን በኋላ
ለሞባይል መግዣ ብላ 6ሺህ ስትልክ በቃ እንጋባለን ስላለቺኝ ታምኜ ተቀምጬ
አገባታለው አልኩ የስልኩን ከላከች በኋላ ፀባያ ተቀየረ በተደጋጋሚ መሳደብ
ጀመረች ጠቅላላ እስከ ዛሬ 60 ሺህ ይሆናል በተለያየ ጊዜ የላከቺው ግን
በእራሷ ፍቃድ ነው ከዛም ከእኔ ውጪ ሌላ ሴት ብትካ አስገድለሀለው ትለኝ
ጀመር በቃ የገባኝ ብሩን የላከቺወ እኔን በገንዘቧ ለመግዛት እንጂ ከልቧ ለእኔ
አዝና እንዳልሆነ ገባኝ......" ሲላት መርማሪዋ በጩሀት
" ዝም በል ..... ደግሞ በህየወቷ ላይ ተጫውተህ ሌላ ወሬ ታወራለህ ባለጌ "
አለችው ንግግሩን አስቁማው
" እሷ ብር ስለላከቺልኝና በገንዘቧ ልትገዛኝ ፈልጋ እንቢ ስላልኩ በህይወቷ
ተጫወትኩባት አይደል.. እሷስ በእኔ ላይ በፍቅር ስትቀልድብኝ የእሷ ምን ሊባል
ነው ዛሬ የደረሰብኝን ተውትና ባለ ትዳር ሆናም አይደለሁም ማለቷ ልጠይቃቹሁ
እስቲ ፍቅር ወይስ ገንዘብ የቱ ነው ህመሙ ከባድ?" አላት ሌሎቹ መርማሪዎች
መልስ ስጪው አይነት አያት።
በሆስፒታል ውስጥ ሚጣ ዕናቷን በንዴት ታናግራታለች ።
" እማ .... አንቺ ብቻሽን መሆን ከፈለግሽ እሺ እኔ ግን ወደ አባቴ ጋር ልሄድ ነው
ተሽሎሻል አይደል ?" አለች ሚጣ
" አባትሽ ከየት መጥቶ ነው የምትሄጂው " አለች ሰርኬ በግርምት ልጇን
በግርምት እያየቻት
" የትኛው ያ ውሸታሙ እሱማ አይደለም አይሆንም የእኔ አባት እያፈቀርሽው
የውሸት በቁጣ የምታባሪው ሚኪ ነው የእኔ እውነተኛ አባቴ " አለቻት ሰርካለም
ደንግጣ ግራ በመጋባት ስታያት ሚጣ በአዎንታ ጭንቅላቷን ነቀነቀች። ....
~ ይቀጥላል ~~~~

╔═══❖• •❖═══╗
@yegna_yegna
╚═══❖• •❖═══╝
❥❥ ⚘ ❥❥
103 viewsÀbiti, 10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-07 20:10:33 ብቸኝነቴን ...... መልሺልኝ

ክፍል ሀያ ሁለት (22)
.
.
.
ከጥቂት ዓመታት በፊት የሚካኤሌ ሀሳብ
ምን መወሰን ምን ማረግ እንዳለበት ግራ ተጋብቶ በዱላው እየተመራ ወደ ሳሎን
ሄደ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ ምን ማረግ እንዳለበት እንቅልፍን ሳይተኛ ሲያስብ አደረ
። አማራጩ በዚሁ አይነ ስውር መስሎ መቀጠል እንዳለበት ህሊናውን አሳመነ።
የሚካኤሌ አይን እንደፈጠጠ ሰማይም ቦገግ ብላ ፈካች በዚህ ሰዓት የሰመመን
እንቅልፍ ወስዶት ነበር ። ውስጥ ሲጎዳጎዱ ብንን አለ ግን አልተነሳም እዛው
አይኑን ጨፈነ ። እነሱ ወደ ስራ ለመሄድ ዝግጅታቸውን ጨረሰው ወደ ሳሎን
መጡና እያዩት ተጠቃቀሱና ።
" ጨርሰናል አልጋውን ከፈለከው ጠረኔ አለልህ አንሶላውን ያረጠብንበት እሱን
በአፍጫክ እየማክ ተኛ።" አለችውና ሳቀች ዝም ብሎ ሰማት አይኑን በአንድ ቦታ
ተክሎ ከሰማት በኋላ።
" አይበቃኝም ሰላም ቤቴን ድርጅቴን ሀብት ንብረቴን ለቀሺልኝ ትሄጂ መካፈል
ያለብሽን ወጭ ሆነሽ ተከራከሪ " አላት ሰላምና አድማሱ እየተያዩ ከት ብለው
ሳቁበትና ።
" የምን ሀብት ንብረት ሁሉም በሚሊየን የሚቆጠር ብር ተበድረሀኝ መክፈል
ስላልቻልክ ሀብት ንብረቴን ለእኔ እንደሰጠህ የሚያረጋግጥ አሻራህም
ፊርማህም ያለበት ማስረጃ እጄ ላይ ነው ከዕነ ምስክሮቹ " አለችው ሚካኤሌ
አልደነገጠም ያኔ ዓይነ ስውር እያለ እንደሚስት አምኗት ፈረመላት ከፈረመ በኋላ
በጣም ትልቅ ስህተት እንደሰራ ገብቶታል የሆነ አንድ ነገር ጎትቶ እንደሚመጣ
ታውቆት ነበር ይሀው ሆነ ዝምታን መረጠ ። ሰላም ንግግሯን በመቀጠል "...ያው
እኔ ክፍ ስላልሆንኩ ቤት ተከራይቼልሀለው ከዛሬ ጀምሮ እዚህ ቤት እንዳላገኝህ
ንብረቴን ቀማቺኝ የምትል ከሆነ ፍ/ቤት ክሰሰኝ ከዚህ በኋላ እዚህ ቤት
ድርጅትም ዝር እንዳትል እኔ ባለትዳር ነኝ እሺ " አለችው
" እሺ ..... ግን ማን ነው የሚወስደኝ ወደ ተከራየሺው ቤት " አላት ፍፁም
ትህትና በተላበሰበትና በፈገግታ ።
" ሹፌር እልክልሀለው እሱ ይዞህ ይሄዳል እስከምችለው የቤት ክራይህንና
ምግብህን እችልሀለው ለፈጣሪ ስል ልጁ እስከሚመጣ እቃህን አዘጋጅ ይህን
ስል ልብሶችህንና የምታነባቸውን መፅሀፎች ብቻ ነው ይዘህ የምትወጣው "
ብላው ፈገግ እያለ ዱላውን አንስቶ እየተመራ እየሄደ
" ሄጄ ላዘጋጃ አይመስላቹሁም " አላት በመሳቁ መልስ ሳትሰጠው እየሄደች
ለአድማሱ የምትናደድበት ሰው መናደድ ሲኖርበት የእሱ መሳቅ ነው እናም
እያላገጠባት ይመስላል።
ከለሳብ መልስ አሁን ላይ
የሚጣ ፊት ሀይለኛ ዝናብ የዘነበበት መሬት መስሏል አይኖቿ በለቅሶ
ሞጭሙጨዋል የሰካራም አይን ይመስል ደፍርሷል ። ሚካኤሌ በሀሳብ
ከሄደበት ሲመለስ የእሱም ዓይን እንባ አዝሎ ነበር ጭምቅ አርጎት እንባዎቹን
ከመሬት ፈጠፈጣቸው።
" ጋሼ እሷን ስናስባት ሴጣን የዋህ ነው እንበል " አለቺው እና እሱ ፈገግ ብሎ
ዝም ሲላት ።" .... ጋሼ እረ ቆይ ለምንድን ነው እንዲህ ክፍ የሆነቺው? " አለቺው
" ሚጣዬ እሱን እንኳን እኔ እሷስ ታውቀዋለች " አላት በዚሀ ሰዓት ሰርካለም
የተኛችበት መኝታ ክፍል ተከፍቶ ዶክተሩ በመውጣት ወደ እነሱ በመምጣት።
" የተደረገላት ኦፕሬሽን በተሳካ ሁኔታ ተፈፅሟል አሁን ልታያት ትችላላቹ
በቅድሚያ ግን እንኳን ደስ አላቹሁ አለና ጨበጣቸው ሁለቱም በደስታ እየሮጡ
መኝታ ክፍሉን ከፍተው ሲገቡ ሰርካለም ሚካኤሌን እንዳየቺው በጩሀት
እንዲወጣላት አባረቀችበት ሚጣም እሱም ደንግጠው በቆሙበት ደርቀው ቀሩ።
ኬብሮን ሚስት ሳይሆን ያገባው ፌዴራል እስር ቤት ነው ያለው ብላ በዱላ ጫት
ቃም በዱላ ተኛና ወሲብ አርገኝ በዱላ ሆኖበት ምርር ብሎታል ፊቱ ቆስሏል ።
አሁንም ቁጭ ብሎ እየቃመ እሷ ቡና እያፈላች ነበር ። እናም መፀዳጃ ቤት ደርሼ
ልምጣ በማለት አስፈቅዶ ወደ መፀዳጃ ቤት አስፈቅዶ በመሄድ ሽንቱን እየሸና
ሳለ ሞባይሉ ጮሀ ከኪሱ አውጡቶ ደዋያን ሲመለከት ሰላም ነበረች ማናገር
ጀመረች።
" አንተ ምን አባህ ልሁን ብለህ ነው ብሬን በልተህ የጠፋሀው" አለችው ሰላም
" እረ በመድሀኒያለም ፣ በማርያም ፣በሚካኤል ፣ በገብርኤል እባካቹሁ ሴቶች
ተውኝ በቃ ..... ቆይ ማን ነው በእኔ ላይ ያዘመታቹሁ እኔ የኢትዮጵያ ጠቅላይ
ሚኒስትር አልነበርኩ ማን አቃጥላቹሁ ድፍት ብሏቹሁ ነው?" አለ በምሬት
" አንተ ደግሞ ሰው ሆነህ አንተን ለመግደል ሰው ይላካል ውርጋጥ አሁን ስለ
ሚኪ ንገረኝ አለበለዚያ አስደፋሀለው " አለች ሰላም በዚህ ወቅት መዓዛ መቆየቱ
አናዷት ስትመጣ ከሴት ጋር እያወራ ነው በንዴት አየቺው ።
" ምንም የለኝም ....እሱማ ግልግል ነው ላኪብኝና አድርጊው በጣም ይሻለኛል"
እያለ ዘወር ሲል አያት በድንጋጤ አይኑ ፈጠጠ እሷም ያን ቡጢዋን አቅምሳው
ከሽንት ቤቱ ሲንክ ላይ አጋደመቺውና።
" እኔን ተደብቀህ ትጀናጀናለህ አንተ አህያ እገልሀለው እሷንም እገላታለው"
አለቺው እና በወደቀበት ምራቋን ተፋቺበት።
ኬብሮን ጠዋት የተነሳው የቤቱ በር በለይል ሲንኳኳ ነበር ።ተነስቶ ቤቱን ተዟዙሮ
ሲያይ የለችም መዓዛ ፊቱ ላይ ብልዝና ፕላስተር ሞልቷል በሀይል ወደ ሚንኳኳው
በር ሄዶ ሲከፍት የታጠቁ ፖሊሶች እና ሲቢል የለበሰ በዕድሜው ፀና ያለ
አስቀያሚ ሰውዬ ቆሟል ስሙን ጠርተውት እሱ መሆኑን አረጋገጡ መዓዛ
እንዳለች ጠየኩት አለመኖሯን ተናገረ ሲቢል የለበሰው ሰው በጥላቻ እና በንዴት
እያየው።
" ነፍሰ ጡሯን ሚስቴን በፍቅር አጃጅለህ ብሬን እየዘረፈች እንድትሰጥህ ከደረክ
አስኮብልለህ አብረሀት ትኖራለህ ያዙልኝ ይሄን ወንጀለኛ " አለ ሰውዬው
ፖሊሶቹም ልብስ እስኪለብስ አልጠበቁትም እያዳፍት ወሰዱት።.........




╔═══❖• •❖═══╗
@yegna_yegna
╚═══❖• •❖═══╝
❥❥ ⚘ ❥❥
68 viewsÀbiti, 17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-06 19:57:12 ብቸኝነቴን.... መልሺልኝ

ክፍል ሀያ አንድ (21)

ከዳኒ
.
.
.
" የምነግርህ ነገር አንተንማ እደፋሀለው ነገሩ ድሮውንም የሞትክ ነክ እኔን እዛ
አስቁመህ አንተ እዚህ ፍቅር ትሰራለህ " አለች መዓዛ የኬብሮንና የማክዳን ሁኔታ
ተመልክታ ኬብሮን አልደነገጠም ዘወር ብሎ ተረጋግቶ አያትና ።
" አዎ ደስ የሚል ፍቅር እየሰራን ነበር አንቺ ባትደርሺብን ምን አለ ትንሽ ቆይተሽ
ብትመጪ እራቁታችንን ሆነን ስታገኚኝ ያኔ ይበርድልሽና እርግፍ አርገሺኝ ጥለሺኝ
ትሄጂያለሽ " አላት ደረቱን ነፍቶ ማክዳ ገርሟት እያፈራረቀች አየቻቸው።
" መስሎህ ነው መቼም አልተውህም ..... ግን እሷ ምንህ ነች እንዲህ እኔን
እንዳታይ አይንህን የጨፈነችብህ " አለች በዛ ግዙፍ ሰውነቷን ሰበር ሰካ
በረገጠችበት በእግሯ ጎን በጎን ከወገቧ ዘንበል እያለች እያለች ቀረበቺው ።
" ንፁሁ የነበረውን ውሀ አንቺ መጥተሽ አደፈረሺው እንጂ እሷማ በጣም
የምወዳት የምሞትላት ፍቅረኛዬ ነበረች " አላት እሷ በንዴት ወደ እሱ ቀርባ
አየቺው እና በግምት 25 ኪሎ የሚሆነውን እጇን ቦክስ ( ቡጢ ) ጨበጠችና
ጎድጉዶ አጥንቱ የወጣበት ጉንጩን ነረተቺው ከቤቱ ቡሎኬት ግድግዳ ጋር
ተጋጭቶ ተመልሶ ሊወድቅ ሲል ያዘችውና።
" እና እኔስ ምንህ ነኝ አንት ቆሻሻ ግማትም " አለቺው ኬብሮን በአፍ የሞላውን
ደም ወደ መሬት ተፍቶት አየትና።
" ሰው ነው ወይስ መብረቅ የመታኝ እእእእ አላወኩም " አለ ኬብሮን ግራ
በመጋባት ።
" እኔ ነኝ የመታሁሁ ...... አይጡ ቆይ ልድገምህ " አለችውና ባልተመታበት
እሷም ባልመታቺው እጇ ደገመቺው አሁን ግን እንዲወድቅ ለቀቀቺው በቀጥታ
መሬት ላይ ወደቀ።
ሚካኤሌና ሚጣ በሆስፒታሉ ኮሪደሩ ላይ ባለ አግዳሚ ላይ ቁጭ ብለው ሚጣ
አይን አይኑን ስታየው ቆይታ ።
" ጋሼ ቅጥልልኝ መጨረሻው ምን ሆነ ለምን አይነ ስውር መሰልክ ? ግን እመነኝ
ለማንም አልናገርብህም " አለችው በጉጉት እያየቺው ።
" የኔ ልጅ እንደማትናገሪ ስለማውቅ ነው የነገርኩሽ ... አይኔን ብቻ አይደለም
ህሊናዬንም አይቶ እንዳለየ እንዲያልፍ አድርጌዋለሁ ስለዚህ በቃ እናም ብዙ
ነገር አይቼ አይኔ እንደማያይ አልፌዋለሁ " አለ በግርምት ፈገግ ብሎ
" ለምሳሌ ምን ምን?" አላችው ዘወር ብሎ ፈገግ ብሎ አያትና ፀጉሯን እያሻሸ
ለእሷ ሳይነግራት እሱ በሀሳብ ሄደ ።
ሀሳብ ነው ወደ ኋላ ከዓመታት በፊት
ሚካኤሌ ሳሎን ውስጥ የአይነ ስውራን መፅሀፍ በጣቶቹ እየነካካ እያነበበ ትንሽ
ደቂቃ ቆየና ።
" የኔ ፍቅር ምነው ሻዩ እስከ አሁን አልፈላም እንዴ?" አላት
" እረ.... ፈልቷል.. ይ.... ይ ...ዤልህ እየ...መጣሁ .. ነ ው " አለችው ቁና ቁና
እየተነፈሰች በተቆራረጠ ቃላቶች ከዛም ብዙም ሳትቆይ እራቁቷን ሆና ሻዩን ወደ
ፊት ይዛ ከኋላዋ አድማሱ እየወሰለታት ሲመጣ ሚካኤሌ አየና ደነገጠ ግን ያለየ
በመምሰል አንገቱን አቀረቀረና።
" ፍቅሬ ከእኔና ከአንቺ ውጪ ሌላ ሰው አለ እንዴ?" አላት
" እረ የለም .... ምነው ?" አለች እየተሳሳቁ ሙድ ያዝንበት አይነት ፈገግታ ፈገግ
እያሉ።
" አይ ተይው በቃ መሬቱ ክብድ ብሎኝ ነው " አላት እሷ እየወሰለተች ሻዩን ይዛ
አጠገቡ መጥታ ጠረጴዛ ላይ አድርጋ እየቀዳችለት ።
" ምነው መሬትን ተሸከምካት እንዴ " አለች እየሳቁ የእነሱ የወሲብ እንቅስቃሴ
ጠረጴዛው ይንቀሳቀሳል እየተቀጠቀጠች ነው የምትቀዳው ። ሚኪ አየሩን
በአፍንጫው ወደ ውስጥ ጎተት ጎተት አረገና ።
" ጥሩ ጠረንም አይሸተኝም " አለ ግን መልስ ሳይሰጡት እነሱ ዝም ብለው
እየባለጉ ሄዱ ሚኪ መነፅሩን አውጥቶ እንባዎቹን ጠረገ ።
በሌላ ቀን ጠዋት ወደ ስራ ሄጃለው ብላው በኮሪደሩ ላይ ጉርድ ቀሚሷን ከፍ
አድርጋ ሸሚዟን ቀዶት ቁልፍን ነቃቅሎት ጡቷ እየታየ አድማሱ ሱሪውን አውልቆ
ያደርጋሉ ይህንን ተመልክቶ ።
እጅግ የከፋውና ሲያስበው ዛሬም ድረስ የሚያስለቅሰው አንድ ቀን ለሊት
አብረው ተኚተው እያለ ግማሽ ለሊት ሆናል የመኝታ ክፍላቸው በር ሲከፈት ሰማ
ገብቶታል እዛው አልጋ ላይ ወሲብ መፈፀም ጀመሩ ለእሷ ጀርባውን ሰጥቶ ነበር
የተኛው እና ሳታየው ሲያለቅስ ቆየና ሁለቱም ሲያቃስቱ አይምሮው መሸከም
አልቻለም እያየ እንዳላየ ሆነላት ግን እየሰማ እንዴት አለመስማት ይችላል
ድንገት ከተኛበት ተነሳና ቁጭ ብሎ ።
" አሁንስ በዛ ሰላም ከማን ጋር ነው ሴክስ የምታደርጊው?" አላት ። ደንግጠው
ሳይላቀቁ አዩትና አድማሱ ከላያ ላይ ሊወርድ ሲል ወገቡን ጭምቅ አርጋ
እንዳያቆም ይዛው ይለይለት ብላ በጣም እየጮሀች ማረጓን ቀጠለች እሱ
ከአልጋው ወርዶ ማስመሰያ ዱላውን ይዞ እያለቀሰ ከመኝታ ክፍሉ ወጣ።..........
~~ ይቀጥላል ~

╔═══❖• •❖═══╗
@yegna_yegna
╚═══❖• •❖═══╝
❥❥ ⚘ ❥❥
61 viewsÀbiti, 16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-04 17:58:28 ብቸኝነቴን መልሺልኝ

ክፍል ሀያ (20)

ከዳኒ
.
.
.
ሚካኤሌ ፍዝዝ ብሎ ሚጣን ሲያያት እሷም ዝም ብላ እያየቺው ቆይታ።
" እህ ንገረኝ ለምን አይነ ስውር መሰልክ .... ግድ የለህም ለማንም አልናገርም
..... ነው በእራሴ ልማልልህ " አለችው
" እረ እንዳትምዪ በቃ እነግርሻለው ....." አላትና ለደቂቃ በዝምታ ሲያያት ከቆየ
በኋላ ንግግሩን ቀጠለ ".... ሚጣዬ እኔ ወደ አራት የሚጠጉ የትልልቅ ድርጅት
ባለቤት ነበርኩ አይኔም ያያል እና እናትና አባቴ እንዲሁም ታናሽ እህቴ በመኪና
አደጋ ሞተው ነበር የቤተሰቤ አነስተኛ እና አንድ ብቻ የነበረውን ድርጅት ጠንክሬ
ቀን ከለሊት ለፍቼ ሰርቼ ትርፋማ አድርጌ አራት ወጤታማ እና በጣም ትርፍ
የሚያስገኙ ድርጅት አረኳቸው በዚህ ሰአት ብቸኝነቴን የምትጋራኝ ሚስት አገባሁ
። እሷ ለካ ወዳኝ አልነበርም ሀብቴን ንብረቴን ፈልጋ ነበር አንዲት የምታምር ልክ
እንደ አንቺ ልጅ ወለደችልኝ ደስ አለኝ እንዴት እንደምወዳት ልጄን ልነግርሽ
አልችልም በጣም ነው የምወዳት።
የሆነ ጊዜ ጠዋት መኪናዬን አስነስቼ ወደ ስራ ስሄድ ፍሬኑ ተበላሽቶ ነበረና ከሲኖ
ትራክ ትልቁ መኪና ጋር ፍሬዬኑ እንቢ ብሎኝ ተጋጨው የመኪናው የፊት
መስታወት ተሰብሮ አይኔ ውስጥ ገብቶ አይኔን አጠፋኝ።
ሆስፒታል ገብቼ ለረዥም ቀናት ታከምኩ አይኔን እዚህ ማዳን ስለማይችል ውጪ
ሄጄ እንድታከም ታዘዝኩ እና ከሆስፒታል ወጣሁ ። እናም ወደ ውጭ ልሄድ ስል
ድርጅቱን ሀብትና ንብረቱን በውክልና እኔ ላስተዳድረው ብላኝ ሚስቴ
አስፈረመችኝ ከዛ ውጭ ሄጄ ታክሜ አይኔም አይቶ ሰፕራይዝ ላደርጋት ሚስቴን
ስመጣ ወንድሜ ነው ትለኝ ከነበረቺው ልጅ ጋር በቤቴ ፍቅር ላይ ነች ልጄ ብዬ
ያሳደኳትም የእኔ ሳትሆን የእሱ ልጅ መሆኗን ሰማሁ....... ከሀብት ንብረቴ በላይ
የጎዳኝ ልጄን ማጣቴ የእኔ አለመሆኗን ማወቄ ነበር" አለና እንባ በጉንጮቹ
በአራት አቅጣጫ ይፈሱ ጀመር ሚጣም እያየቺው አለቀሰች ወደ እሱ ሄዳ
አቀፈቺው አቀፋት ።
" ጋሼ ከዚህ በኋላ አትዘን እኔ ልጅህ አለው እሺ አታልቅስ ከዚህ በኋላ አባዬ
እልሀለው የአባቴንም ስም የአንተን ነው የምፈልገው ለእማ እነግራታለው "
አለቺው እሱ እቅፍ አርጎ ሳማት ተቃቅፈው ተላቀሱ።
ህይወት መከራ ሴቶች የጋለ ብረት ምጣድ የሆኑበት ኬብሮን መኖርን ጠልቶ
እራሱን ቢያጠፋ በወደደ ነበር ግን ከፈጣሪ ጋር ጠብ ነው እራስን ማጥፋት ብሎ
እቺ ግፍ እየሰራችብት ያለችን የህይወት መንገድ እና ሴቶችን ሳይወድ በግዱ
መጋፈጥን አምኖ ተቀብሏል።
መዓዛ አሁን የመጣቺው ከእሱ ጋር ለመሆን መሆኑን ነግራው ቤት ተከራይተው
አንድ ላይ እንኑር ብላው አልፈልግም ቢልም ሚካኤልን እንደ ምክንያት
ቢያቀርብም እንቢ ብላው እሷ ኮደሚኒየም ተከራይታ ዕቃህውን ሄደን እናምጣ
ብላው ተያይዘው ኮንትራት ታክሲ ይዘው ሄዱ።
በኬብሮን አውቆ እንድትጠላው ሲጋራ በእሷ ፊት በተደጋጋሚ ያጨሳል እሱ
ካልቃመ ለሲጋራ ብዙም አይደለም እረ ሲቅምም ብዙ አያጨስም ግን በቃ አሁን
እሷ በጣም አጫሽና ቃሚ ነው ብላ እንድትጠላው ነበር አልተሳካለትም እሷ
ታየውና።
" ኬቡ ሁሌ እንደዚህ ነው የምታጨሰው ?" አለችው
" ማ እኔ አንቺን አፍሬ እንጂ የዚህን ሁለት እጥፍ ነው የማጨሰው " አላት
የደበራት መስሎት በደስታ።
" አይገርምም እንደዚህ የምታጨስ አልመሰለኝም ነበር ... ማጨሱን አጭስ ግን
እራስህን እንዳትጎዳ " አለቺው በንዴት አያትና።
" አንቺስ?" አላት የእሱ አባባል ጥለሺኝ ትሄጃለሽ ወይ ለማለት ነበር እሷ ግን
ፈገግ ብላ አየቺውና።
" እኔ ምን ላጭስልህ እ ወይ ዘድሮ " ብላው ስትስቅ እሱ በሀሳቡ ።" እኔን
እያጨሺኝ ምን ታጨሺያለሽ " አለ እሷ ንግግሯን በመቀጠል " ኬቡዬ ስትቅም
ግን ደስ ይለኛል .... ለምን መሰለህ ማታ ሴክስ እናደርግ ጀግና ትሆናለህ " ብላ
አፏን ከፍታ ስትስቅ በንዴት እና በጥላቻ አያት የታክሲ ሹፌሩ በንግግራቸው
በግርምት ፈገግ አለና ታክሲውን አቁሞ መድረሳቸውን ነገራቸው ። መዓዛ እዛው
ተቀምጣ እሱ ቶሎ ደርሶ እንዲመጣ ነገረችው እና እሱ ከታክሲው ወርዶ ወደ
ቤት በመሄድ ደረጃውን ወጥቶ በኮሪደሩ ላይ መራመድ ሲጀምር ማክዳ ልትወጣ
አለችና እሱ ሲመጣ አይታው መልሳ ስትገባ እየጠራት በፍጥነት በመሄድ
ልትዘጋው የነበረውን በር ያዘባትና ሰላም ሲላት እንዲወጣ ተናግራው ወደ
ውስጥ ስትገባ ተከትሏት ገባና ምን አርጓት እንደሆነ ደጋግሞ ቢጠይቃትም
መልስ አልሰጠቺውም ለምን እንደሚለምናት አልገባውም ግን እንድታናግረው
ወደ እሷ ተጠግቶ ይለምናታል እሷ ጀርባዋን ሰጥታው ዝም ካለቺው በኋላ
በመጨረሻ በንዴትና በጩሀት እንዲወጣላት ተናግራ ፊቷን ወደ እሱ አዙራ
በጥፊ አጮለቺው ደንግጦ ጉንጩን ይዞ ምን እንደሆነች ሲጠይቃት ተመልሳ
በጥፊ ልትደግመው ስትል እጇን ያዛትና ወደ እሱ አስጠግቶ ከንፈሯን ግጥም
አድርጎ ሳማትና ለቀቃት እሷ አፍጣ ስታየው።
" እመቤቴን ማኪ አውቄ አይደለም " አለ ደንግጦ። መዓዛም ተጠራጥራ
ስትከተለው ነበረና በሩ ላይ ቆማ በንዴት ታየው ነበር እነሱ አላያትም።...........

ይቀጥላል....

╔═══❖• •❖═══╗
@yegna_yegna
╚═══❖• •❖═══╝
❥❥ ⚘ ❥❥
63 viewsÀbiti, 14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-03 22:19:36 ብቸኝነቴን መልሺልኝ

ክፍል 19

ከዳኒ የወሰን ልጅ
.
.
.
ሚጣ በግርምት ፍዝዝ ብላ ሚካኤሌን አየቺው ምን እንደሆነ ያላወቀችው
የግርምት ይሁን የደስታ ፊቷ እየፈካና እየበራ ሄዷል እሱ ደግሞ በድንጋጤ አይኑ
ፈጦ ተመለከታት። ሚጣ በንገረኛ ፊቷን ነቀነቀች ።
" ሚጣዬ አንቺ እኮ የሰማሽውን ያየሺውን ቆልፈሽ በሚስጥር ማስቀመጥ
አትችይም " አላት ፈገግ እያለ።
" ጋሽዬ ስለ መልካም ስራህ አንተ ማሳወቅ ባትፈልግም እኔ ግን ከፈጣሪ በታች
ህይወት የሰጠኝን ሰው የአለም ህዝብ ሁሉ ቢያውቅልኝ እደሰታለው ለእኔ
ህይወት ለእናቴ እና አስቴ ሰላምን ሰጠህልኝ እና ማሰወቄ ስህተት የለውም ጋሼ
" አለች የሆነ ደስ በሚል ፍንክንክ ብላ ለመግለፅ በሚያዳግት....
" የእኔ ቅመም ..... የሆንሽ ... ፍቅር የሆንሽ ልጅ ነሽ አንቺ አለመውደድ በእራሱ
ይቅርታ የሌለው ሀጢያት ነው " አለና ወደ እሷ ሄዶ እቅፍ አርጎ ጉንጯን ሳማት።
" ጋሽዬ የምን ቅመም የወጥ ነው....... ልትሸውደኝማ አትሞክር ንገረኝ ......
አሁን አይኔ አያይም ብለህ ለእኔ እንደምታይ ብትነግረኝ የደበክበት ምክንያት
ስላለህ እኔ ልሙት ለማንም አልናገር " ስትለው ኮስተር ብሎ ሚኪ አያትና ።
" ከዚህ በኋላ ሚጣ እኔ ልሙት ብለሽ ስትምዪ እንዳልሰማሽ እሺ እኔ ክፍት
ይለኛል እሺ እና .... እኔ አያለው እሺ
" እኔ አላምንም ...... ወይኔ ታዲዬ ...... እኔ እኮጰአሁን ወደ እኔ ጋ ስትመጣ
ጠርጥሬያለው ..." አለችና በደስታ እየጮሀች ስታቀፈው አፏን ያዘና እናቷን
አሳያት ከዛም ዝም አለች ሳመቺውና።
" ጋሼ እማ ለምን እንደምትቆጣህ ታውቃለህ...... አታውቅም አይደል እኔ ግን
አውቃለው" አለችው ደነገጠ ሚኪ አያት
" .... እእእእእ ለምንድን ነው? " አላት በግርምት እያያት
" እኔ ነኛ እንደምታፈቅራት ነግሬያት " አለች እሱ ደነገጠ ገረመው ፈገግ ብሎ
አያት ።
" በምን አወቅሽ ወይስ ማን ነገረሽ ?" አላት ሚኪ
" የአንተ ሁኔታን ዝም ብዬ ጠረጠርኩና ለምን አላጣብሳቸውም ብዬ ዘይት
ሳላበዛ ምጣድ ላይ አርጌ ለመጣበስ ሞከርኩ ሳስበው እሷም ጠበሳው
የተስማማት መሰለኝ " አለች ሚኪ ግራ ገብቶት በዝምታ አያት።
ልባቸው ሊፈነዳ የደረሰ ይመስላል ቁና ቁና ይተነፍሳሉ። መርፌ እና ክር ከሆኑበት
ተላቀው በጀርባቸው ከአልጋው ላይ ተንጋለሉ።
" አንተ.....እራስህን ገለህ እኔንም ልትገለኝ ነው እረ በቃ .... አልጋዬንም
ልትሰብረው እኮ ነው" አለች ሰላም በተደጋጋሚ በስሜት ከጨፈረባት በኋላ
ደክሟት በተቆራረጠ ትንፋሽ።
" ቆራጥ እንዳልሆን ያረገኝ ይሄ አማላይ ገላሽ አይደል ክፍያዬን የማውቀው እሱን
በደንብ አድርጌ ስደበድበው ነው"
" አንተ የተረገምክ ነህ ባክህ " አለችው
" ከአንቺ የበለጠ የተረገመ ሰው አለ እንዴ ? ..... የሚገርመኝ ይሄ ከፈጣሪ በላይ
የምትመኪበትን ገላ ብታጪ ምን ልትሆኚ እንደምትቺዪ ሳስብ ይገርመኛል" አላት
ሰላም ከምር ተናደች።
" ትሰማለህ በውበቴና በገላዬ ማንም ሲመጣብኝ አልወድም ከዚህ በኋላ
እንዲህ እንድትለኝ አልፈልግም እሺ" አለች
" እረ ቀስ ..... እረ ቀስ...በቃ ይቅርታ እና ግን ለምን ነበር የፈለግሺኝ ዋናው
ቁም ነገሩ እሱ ነው አይደል?" አላት
" ነበር ቃልኪንን ከዕነ ባሏ መግደል ወይም አካለ ስንኩል ማረግ ግን አሁን
ሳስበው ከእነሱ በፊት አንተ የእነሱ እጣ ሊደርስህ ይገባል" አለችው ሰላም
እውነቷን ነበር በውበቷ በመተማመኗ ማንም ክፍ መናገር አይደለም እራሷ
ለእራሷ ክፍ ማሰብ አትፈልግም ።
በሆስፒታል ኮሪደር ላይ መዓዛ ተቀምጣ ኬብሮን ከግራ ወደ ቀኝ ይዟዟራል ።
በሀሳቡ " ቆይ ማን ነው የተረገመው እኔ ወይስ እቃዬ አልገባኝም ...... ምን
አለበት ሽንት የምሸናበት ተከፍቶ ከሴት ጋር የምገናኝበትን በደፈነው ..." ሲል
ቆየና ፊት ለፊቷ ቆሞ መዓዛን አያት ። መዓዛ ከእሱ ዕድሜ ቢያን 7 አመት
ትበልጠዋለች ታላቅ እህቱ እንጂ ሚስቱ አትመስልም አያት አትኩሮ ።
" ይቅርታ መዓዚ አንዴ ሽንት ቤት ሽንቴን ሸንቼ ልምጣ " ብሏት ወደ መፀዳጃ ቤቱ
ሊሄድ ሲል ።
" የት አባህ ነው የምትሄደው ስንቴ ነው ሽንትህ የሚመጣው በ5 ደቂቃ ሀያ ጊዜ
እንዴት ሽንትህ ይመጣል ... ና ቁጭ በል"
" እረ ዛሬ ነው የእኔ መሽናት ያሳሰበሽ ያኔ ስሸና ምነው ተው አትሽና ባልሺኝ ነበር
.... እኔን ለማሳበድ ሴቶች ብቻ ሳትሆኑ የእራሴውም እቃ ተፅኖ ፈጥሮብኛል ....."
አለና ግራ ገብቶት መሄጃ ሲፈልግ የመዓዛን ስም ተጠራና አንዲት ነርስ ወደ እሷ
በመምጣት አጠገቧ ስትቆም ኬብሮንም ለመስማት ጓጉቶ አጠገባቸው ቆመ።
" እንኳን ደስ አለሽ ወሮ መዓዛ ..." ስትል ኬብሮን በፍጥነት እጁን ዘርግቶ
የነርሷን በግድ ይዞ ጨበጣትና።
" እንኳን አብሮ ደስ አለን ..... እርጉዝ አይደለችም አይደል " አለ ይህንን ነበር
የፈለገው።
" አይ አይደለም ነፍሰ ጡር ነች ... የወንድ ልጅ እናትና አባት ልትሆኑ ነው ደስ
ይላል " አለች በፈገግታ
" እረ ኡኡኡኡኡኡ ..... እንኳን ደስ አላቹሁ ወይስ እንኳን ተረገማቹሁ " አለና
የነርሷን እጅ እንደያዘ መሬት ላይ ዝርፍጥ ብሎ ቀመጠ ።.............
ይቀጥላል ~~

╔═══❖• •❖═══╗
@yegna_yegna
╚═══❖• •❖═══╝
❥❥ ⚘ ❥❥
55 viewsĴozzz , 19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-02 09:48:41 ብቸኝነቴን መልሺልኝ

ክፍል 18

ከዳኒ የወሰን ልጅ
.
.
.
የኬብሮን ጭንቅላት መብረቅ እንደወደቀበት ለሁለት ተከፈለ ከፍራሹ ላይ ቁጭ
አለ መልሶ ተነሳ ተመልሶ ቁጭ አለ እንደገና ተነሳ ማክዳ ልቧ እንደ ክምር በረዶ
በየማይክሮ ሴኮንዱ ሲቀልጥ ይሰማታል አይኗ በሀዘን ተስፋ በመቁረጥ
የቀለጠው ልቧ ሀዘኑን በአይኗ በኩል በእንባ መልክ ያፈሰው ጀመር።
" አታሹፊ እንጂ መዓዛ .... እውነት ነው ከእኔ አረገሽ ?" አላት ግራ ገብቶት
የሚገባበት ጠፍቶት ጭንቅ ጥብብ ብሎት።
" ምን ለማለት ፈልገህ ነው ከሌላ ወንድ ተኛሽ ኤያልከኝ ነው አንተ... አንተ
የማትረባ እእእ" አለችው መዓዛ በንዴት እያየቺው ወደ እሱ ለመቅረብ ጠጋ
ስትል።
" ቆይ መአዚ እዛው ሁኚ..እኔ ሌላ ወንድ ጋር ሄድሽ አላልኩም ግን አንድ ቀን እኮ
ነው አብረን የተኛው እንዴት ሆነ ብዬ"
" አዎ አንድ ቀን ነው አንተ ጨዋ ነህ ዝም ብለህ ነው የተኛሀው...... ሙሉ ለሊት
ዘፈን እንደተከፈተልህ ስትጨፍርብኝ አይደል እንዴ ያደርከው ?" አለችው
በግርምት እያየቺው።
" እናቴ ትሙት እረ እኔ ጭራሽ ጭፈራ አልችልም .... ግን ወሲብ አድርገናል አዎ
ትዝ ይለኛል ግን ጭፈራ ..." ብሎ ሊደግመው ሲል ከት ብላ ስትስቅበት
ንግግሩን አቆመ።
" ታዲያ ጭፈራ ማለቴ ወሲቡን አይደል እንዴ? "አለችው ከሳቀችበት በኋላ
እሱም መዓዛን ካያት በኋላ ዘወር ብሎ ማክዳን ሲያያት እያለቀሰች እሷም
አየቺውና በሩን በመክፈት ወጥታ ስትሄድ እሱም በዕፍረት አንገቱን ደፍቶ።
" ነው ላካ ስደነግጥ ስለምረሳ እንጂ ጭፈራ ገብቶኝ ነበር እኮ " አላት እና ወደ
ሱሪው ዚፕ ተመለከተ ንብረቱን አሰበ።
የሳላም ባል አድማሱ አንድ አንስተኛ መኪና የተጎዳች ወደ 10 ሰዓት ገደማ
እየነዳ ከሰላም ቤት ግቢ በራፍ ላይ ሲደርስ ትላክስ አደረገ ጥበቃው ከፈተለት
ሰላምታ ሰጠውና ወደ ውስጥ አስገባው ወደ ሶስት ከሚጠጉ ዘመናዊና
የሚያምሩ መኪናዎች ጀርባ አሸማቆት የራሱን መኪና አቆመ እና በመውረድ ወደ
ቤቱ ሄደ በመሄድ በሩን በዝግታ ከፍቶ ወደ ውስጥ ገባ ሳሎኑን በአይኑ አማተረ
ማንም የለም ቆሞ በአይኑ ሲማትር ከመኝታ ቤቷ በሌሊት ልብስ ሰላም
በመውጣት ።
" ሀይ ... ና እዚህ ነኝ " አለችውና ወደ መኝታ ክፍሏ ስትገባ እሱም በመሄድ በሩ
ላይ ቆሞ ተመለከታት እሷም ቢጃማዋን ሙሉውን በማውለቅ እንደ አልማዝ
የሚያንፀባርቀውን ገላዋን እንደፍጥርጥሯ ካለ ምንም መሸፈኛ ጨርቅ
አሳየቺው።
" አሀሀሀ ና ብለሽ የደወልሺው ለእዚህ ነበር ያ ማለት ችግር ውስጥ ገብተሻል
ማለት ነው አይደል?" አላት
" እሱን በኋላ እናወራለን አሁን ናልኝ በሩን ዝጋውና ተርቤያለው ሰው ተርቦ እኮ
አያወራም " አለቺው እሱም ይሄን እያየ መመለስ አልፈለገም እንደ ዘዶ
ተወርውሮ ተጠመጠመባት እና ተያይዘው ከአልጋው ወደቁ።
ቁልቁል አቀርቅሮ ወደ ሱሪው እየተመለከተ በንዴት፡
" አንተ የተረገምክ ከ5 ዓመት በላይ አንገትህን ከሽንት ውጪ ምንም ሳትፈልግ
ሳያምርህ አርፈህ ኖረህ ያኔ ምን አባህ ልሁን ብለህ ነው እኔ ነኝ ወንዱ ብለህ
ዘራፍ ብለህ ቀና ያልከው እ..እ ..ተናገር አንተ የተረገምክ ነገሩ መረገምክ ከሱሪ
እና ከፓንት ስር የወሸቀህ አሁንም ከዛው አትወጣ የሰው ታምር ይሰራል የእኔ
ታምር ታሰራብኛለህ...." እያለ የእራሱን ንብረት ሲረግም ።
" አንተ ደደብ ምን አባህ ነው የምትለው እ?" አለችው መዓዛ
" እህ ምን አልኩ ምንሽ ላይ ደረስኩ የአንቺ ጋር አልደረስኩ የእራሴንም መርገም
አልችልም እንዴ ?..... ይሄ ጦሰኛ ምናለ ፈጣሪ ወደ እዛ ቆርጦ ቢጥልልኝ......
ውይ ጌታዬ ይቅር በለኝ ደግሞ በምኔ እሸናለው .... ውይ ... ውይ " አለ በምሬት
" አንተ እውነትም ደደብ ነህ አንተ ባትፈልገው እኔ እፈልገዋለው ከአንተ ልጅ
መደገም እፈልጋለው " ብላ በዛ ጉዙፍ ሰውነቷ ዘላ ተከመረችበት አልቻላትም
ተያይዘው ፍራሹ ላይ ወደቁ።
ሰርካለም በምትታከምበት ሆስፒታል በመኝታ ክፍል ውስጥ ሚጣ ወደ እና
ሚካኤሌ ወደ ቤት አንሄድም ብለው ውሎም አዳራቸውም እዚሁ ከሆነ ቆይቷል
ግን ለሚጣ ጥሩ ሆኗል ሚካኤሌ የሆስፒታሉን ሀላፊ አናግሮ ለእሷም አልጋ
ከእናቷ አጠገብ እንዲሰጣት አድርጎ ለልቧ ክትትል እንዲያደርጉላት አርጓል።
አሁንም ከእናቷ አጠገብ በጉና ተኝታ በጀርባዋ በህክምና መሳሪያ ተከባ
የተኛችውን እናቷን እያየቻት ሳለ በሩ ሲከፈት የተኛች መሰለች አንዲት ነርስ
በእጇ የመዳህኒት ማዘዣ ወረቀት ይዛ ገባች ሁለቱንም አየቻቸውና ወረቁቱን
አልጋው ላይ አርጋ ልትወጣ ስትል ሚካኤሌ ከመፀዳጃ ቤት እየወጣ ::
" ሲስተር እዚህ ነኝ " አላት እሷም መድሀኒት እንዲገዛና ወረቀቱን አልጋ ላይ
ማረጓን ነግራው በሩን ዘግታ ሄደች እሱም ቀጥታ በመሄድ ወረቀቱን አንስቶ
ሲያይ ሚጣ በጨረፍታ በግርምት አየቺውና ተነስታ ቁጭ አለች አልጋው ላይ
እሱም አያትና።
" ተነሳሽ እንዴ ሚጣ " ሲላት ደንግጣ
" ጋሼ ሚኪ ማየት ትችላለህ እንዴ " አለችው እሱም ቀድንጋጤ ዞሮ አያት። .......

ይቀጥላል

╔═══❖• •❖═══╗
@yegna_yegna
╚═══❖• •❖═══╝
❥❥ ⚘ ❥❥
47 viewsĴozzz , 06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ