2021-12-02 16:35:20
የእውነተኛ ፍቅር መሰናክሎች
~//~~~~~//~~
1. ቅናት
2. የሰው ወሬ መስማት
3. በመሃከላቸው መተማመን መጥፋት
4. ለኔ ብቻ ግዜ ስጠኝ/ስጪኝ ማለት ሲመጣ
5. እሱ ከሴቶች / እሷም ከወንዶች ጋር አትገናኝ /አትገናኝ ማለት ሲጀመር
6. መደማመጥ ሲያቅታቸው
7. በጋራ የወሰኑትን ጉዳይ በተናጥል ሲንዱት
8. ሲገናኙ የፍቅር ጨዋታ ቀርቶ ክርክር ሲመጣ
9. የሱን እንከን / የሷን እንከን መተያየት ሲጀምሩ
10. ላለመስማማት ሲስማሙ
11. እኔን ብቻ ስሚኝ/ስማኝ ማለት ሲመጣ
12. ራሳቸውን ለማሳደግ መጣር ሲያቅታቸው
13. በአስተሳሰብ እየተራራቁ ሲመጡ
ከላይ ያሉት ነጥቦች በእውነተኛ ፍቅር ውስጥ መከሰት ሲጀምሩ ያኔ ለፍቅራችሁ ስትሉ ንቁ ... እመኑኝ ንቁ! አለበለዚያ የት ይደርሳል ያልነውን ዛፍ ቀበሌ ቆረጠው እንደሚባለው ...
ይህ ፍቅር ያማረ ነው ፣
ፍቅር የሆነ ቤተሰብ ይመሰርታል ፣
መጨረሻው ያምራል እያልን የተደነቅንበት
ፍቅር ታሪክ ወደመሆን ይቀየርና ጊዜው አልፎ "ወይኔ ምነው እንዲህ ባደረኩኝ" እያልን በፀፀት አለንጋ የምንገረፍበት ጊዜ እንዳይመጣ ካሁኑ እናስብበት ...
አዎ ፍቅር ህይወት ነው ...
ጥንዶች ሆይ ራሳችሁን እዩበት
7.2K views@%%@& ደ, 13:35