Get Mystery Box with random crypto!

#ሀያትና_እና_የአይን_ፍቅር #ክፍል_አስራሁለት አብዱ ኤምሬ የዩኒቨርሲቲ | የፍቅር ለዛ (YEFKIR LEZA)

#ሀያትና_እና_የአይን_ፍቅር
#ክፍል_አስራሁለት


አብዱ ኤምሬ

የዩኒቨርሲቲ ኢንትራንስ ፈተናዬን በጥሩ ውጤት አልፌ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኢኮኖሚ ትምህርት ተመድቤለሁ ቤተሰቦቼም ሆነ ጓደኞቼ በጣም ተደስተዋል ይበልጥ እኔም ደስተኛ ሆኛለሁ ምክንያቱም ከቤተሰቦቼ እና ከለመድኩት አከባቢ ማህበረሰብ እና አኗኗር መራቅ ስለማልፈልግ ይሄ ለኔ ጥሩ እድል ነው...

ዛሬ የዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ቀኔ ነው በጊዜ ወደ ክፍል ገብቼ ከክፍሉ መሀል ባለ ወንበር ላይ ተቀምጬ የእለቱን ትምህርት እየተጠባበቅኩ ነው ሁሉም ተማሪዎች ወደ ክፍል መግባት ጀምረዋል እኔም በር በሩን እያየሁ በሀሳብ ስምጫለሁ በድንገት ሳላስበው ሳልገምተው ይሆናል ብዬ የማላስበው ነገር ተፈጠረ አንድ ሰው ወደ ክፍሉ እየገባ ነበር አይኔን ማመን አልቻልኩም የእውነት ሀያት ነች እንዴት ሊሆንስ ይችላል ይሄ አጋጣሚ ብቻ አይደለም የአላህ ተአምርም ነው..

ሀዩ ወደ ክፍል ገባች ሳላስበው ደስታ እና ሀዘን የተቀላቀለ እንባ ከአይኔ ይፈስ ጀመር አጠገቧ ሄጄ ባቅፋት እና የልቤን ሁሉ አውጥቼ ብነግራት ምን ያህል ደስ ባለኝ ነበር ግን እሷን ሳያት አይደለም መናገር የማደርገውን እንኳን አላውቅም ከዛም ሀዩ ከክፍሉ ፊት ለፊት ባለው ወንበር ሄዳ ተቀመጠች በእርግጥ በራሴ ተናድጃለሁ ምን አለ ፊት ተቀምጬ በነበረ አይኔን ከሀዩ ላይ መንቀል አልቻልኩም መቼም አያታለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር በዛ ላይ ካደረገችው ጥቁር ሂጃብ ጋር በፊት ከነበራት ውበት በላይ በጣም አምሮበታል ምን አልባት ፈጣሪዬ ያን ሁሉ ስቃይ እንዳሳልፍ እና አንድ አመት እንድደግም ያደረገው ለዛሬዋ ቀን ይሆናል.... ዛሬ ትምህርት ስላልነበር ትውውቅ ከተደረገ ቡሀላ ሁላችንም ከክፍል ወጣን ሀዩ ብቻዋን ነበር እየሄደች የነበረው ሲመስለኝ የምታውቀው ሰው የለም...

ሄጄ ከአጠገቧ ለመሆን እና በዚህ አጋጣሚ ጓደኛዋ መሆን እንዳለብኝ ወስኜ ወደ ሀዩ ጋር ሄድኩ ሀያት ብዬ ጠራሆት በቀስታ አቤት አለች ዞር ብላ... የእኔን መልስ ሳትጠብቅ ቀጥላ ከዚህ በፊት አውቅሀለሁ ልበል አለች "አዎ ሰሚር እባላለሁ አንድ መድረሳ ተምረናል አልኳት" አዎ አሁን አስታዋስኩህ "የአቡኪ ጓደኛ ነህ አይደል?" በድንጋጤ ቀጥ ብዬ ቀረሁ አቡኪ ነው ያለችው ግራ ተጋባሁ ደግሞ አቡኪን የት አውቃው ይሆን....

በነገርሽ መሀል አትስጊ ግድ የለም:
ዶሮ ጮኸ አልጮኸ መንጋቱ አይቀርም:
ይሄው ነው በእጅ ያሳደጉት ጅብ አጉራሽ እጁን ቢነክስ መልሶ:
ዘመኑ ይሆናል ወላጁን ሰውቶ ተሹሞ የሚኖር መንጎችን ገርስሶ:


ይሁና ከሆነ በመገርሰስ መሀል ራስ ሆኖ ከኖረ:
መስማቱን ዘንግቶ ወራጅ አለ እያሉት ዘግቶ ከበረረ:
ለምን እንዳትይ አትስጊ ግዴለም:
ዶሮ ጮኸ አልጮኸም መንጋቱ አይቀርም።

ይቀጥላል....

@YEFKIR_LEZA
@YEFKIR_LEZA