Get Mystery Box with random crypto!

#ሀያትና_እና_የአይን_ፍቅር #ክፍል_አስራአንድ አብዱ ኤምሬ ዛሬ የዩኒቨርሲ | የፍቅር ለዛ (YEFKIR LEZA)

#ሀያትና_እና_የአይን_ፍቅር
#ክፍል_አስራአንድ

አብዱ ኤምሬ


ዛሬ የዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ቀን ትምህርቴን ለመከታተል በዩኒቨርሲቲው ክፍል ውስጥ መሀል ላይ ተቀምጩ ሳለሁ በሀሳብ ያለፈውን ማስታወስ ጀመርኩ ያ ሁሉ ነገር መከራ እና ደስታ እንደዚህ በፍጥነት ማለፉ በጣም ገርሞኛል "ከሶስት አመታት በፊት ከወንድሜ ሙሀመድ ሰርግ ቡሀላ ራሴ ላይ የነበረው ጭንቀት ናፍቆት ድብርት እየጨመረ ሄደ ይባስ ብሎ ሰውነቴ ከቀን ወደ ቀን እየቀነሰ እና ነገሮችን በራሴ የማድረግ ጉልበት እንኳን አጣሁ ሆስፒታል ለሆስፒታል ብዞዞርም ምንም መፍትሔ ሊገኝ አልቻለም ቤተሰቦቼ ብዙ ገንዘብና ጊዜቸውን ቢያጠፉም ህመሜ እየባሰ እንጂ ልድን አልቻልኩም በየሆስፒታሉ የሚሰጡት መልስ የተለያየ ነበር ሀኪሞቹ እንኳን ሳይቀር በህመሜ ግራ ተጋብተዋል የኔ በሽታዬ ሀዩ ነበች መድሀኒቴ ልትሆን የምትችለው እሷ ብቻ እንደሆነች የሚያውቅ የለም...

ቤተሰቦቼ ሀኪም ቤት እየቀያየሩ ቢያሳክሙኝም ምንም ለውጥ ሊያገኙ ስላልቻሉ ወደ ቁርዐን ቤት ወስደውኝ ቁርዐን ይነበበልኝ ጀመር ከዛን ጊዜ ጀምሮ የውስጤ ህመም እና ጉዳት መፈወስ ጀመረ ቀን በቀን ኡስታዙ እየመጡ የተወሰነ የቁርዐን ክፍል ያነቡልኝ ነበር በእውነቱ ሀያ አራት ሰአት ሙሉ ባዳምጥም ደስተኛ ነኝ...

ቁርዐን ይነበበልኝ ከጀመረ ቡሀላ ሙሉ ለሙሉ ማገገም ቻልኩ ነገር ግን አሁንም የቤተሰቦቼ ጊዜ እና ገንዘብ በኔ ምክንያት መባከኑ ጭንቀት ፈጥሮብኛል በተጨማሪ በህመም ምክንያት ትምህርት በማቋቅኳረጤ ቤት ውስጥ ስለመውል እሱም አንድ ጭንቀት ነው በእርግጥ አቡኪ በእረፍት ጊዜው እኔ ጋር እየመጣ ያሳልፋል ያጫውተኛል ሀሳቤን እና ጭንቀቴን ከሱ ውጭ የምነግረውም ሰው የለም አቡኪ ሀዩን እያፈላለገልኝ ቢሆንም እስካሁን ሊያገኛት አልቻለም ሰዎች አፍቅረው ካለዩት በቀር በፍቅር ይሄን ያህል መጎዳት ቀልድ አድርገው ሊያዩትና ሊመስላቸው ይችላል እኔም በአንድ ወቅት እንደዚህ ነበር የማስበውና...

የአንደኛ ሴሚስተር ውጤቴ የተሻለ የነበረ ቢሆንም አንድ አመት ለመድገም ተገድጃለሁ አቡኪ አሁን ላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነው ከእሱ ጋር ብማር ለእኔ ጥሩ ይሆን ነበር ቢሆንም ግን እረፍት ሰአት እና ምሳ ሰአት አብረን ነው የምናሳልፈው በህይወቴ አንድ ልረሳው የምፈልገውና ባላስታውስ ደስ የሚለኝ ነገር ቢኖር ሀያት ነበረች ነገር ግን ልረሳት በሞከርኩ ቁጥር ፍቅሬ ናፍቆቴ እየጨመረ እና እየባሰ ነው...

ሀዩን ብናፍቃት እና ባስባትም አሁን ላይ ከአጠገቤ አለመኖሮ ላያት አለመቻሌ ለኔ ከባድ ህመም ነው አንድ የምፅናናበት ነገር ቢኖር አንድ ቀን ምሽት ከሀዩ ጋር ስጋባ ያየሁት ህልም ነው እሱን ባሰብኩ ቁጥር ተስፋዬ እና ምኞቴ ይጨምራል ምን አልባት ሀዩን በህልም አለም ከማግባት ውጪ በእውኑ አለም ከሷ ጋር የመሆንና እሷን የማግባት ተስፋ ያለኝ አይመስልም...

ገለጥ ሲልልኝ ድርብርቡ አፈና:
ጨለማው ተገፎ ሽኩቻ ለትግል
እንቅልፍ ሲነሳ በሀገሩ ለፍፎ
ምንም አትበይ ዛሬ ቃላት አጥተሽ
አፍሽ ቢቀየድም አትስጊ ግዴለም:
ዶሮ ጮኸ አልጮኸ መንጋቱ አይቀርም።

እንደነቃሁ ገና ሲነጋ ልነግርሽ:
ከንፈሬን ላልሼ ቃላት ፈልግና:
ሳስብ እፈራለው ሚስጥር እንዳይሾልከኝ ቃል እንዳላዛባ ሳላስብ ሆነና:
ምን አልባት በነገርሽ መሀል ሌላን:
ብተነፍስ ከመሀል ቆይቼ:
ቃል ግቢልኝ! አዝልቀሽ ላትሰጪኝ ላሳደኳቸው ነፍስ ወስደሽ ለጅቦቼ።

ይቀጥላል.........

@YEFKIR_LEZA
@YEFKIR_LEZA