Get Mystery Box with random crypto!

#ሀያትና_የአይን_ፍቅር #ክፍል_ዘጠኝ አብዱ ኤምሬ መድረሳ ብገባ | የፍቅር ለዛ (YEFKIR LEZA)

#ሀያትና_የአይን_ፍቅር
#ክፍል_ዘጠኝ

አብዱ ኤምሬ


መድረሳ ብገባም ዛሬም አብኪ አልመጣም ሲመስለኝ የሀዩን ስልክ ለመቀበል ብቻ ነበር የመጣው የመቀጠል ፍላጎት ያለው አይመስለኝም... ከመድረሳ ከወጣን ቡሀላ እንደተለመደው ሀዩን ብጠብቃትም ዛሬም አልመጣችም ነበር... በእውነቱ ዛሬ ስለቀረች ምንም አልተሰማኝም ምክንያቱም ዛሬ በቀረች ብዬ ሳስብ ነበር በመቅረቷ ደስ ብሎኛል ግን ሁለት ቀን የቀረችው ምን አጋጥሞት ይሆን የሚለው ጭንቀት እና ፍርሀት ግን አሁንም አለለቀኝም...

ሰርጉ የቀረው አንድ ሳምንት ብቻ ነው ቀኑ በቀረበ ቁጥር ቤታችን ውስጥ ያለው ዝግጅትም በዛው ልክ ይጨምራል። አብዛኛው ጊዜዬን የማሳልፈው ቴሌግራም ላይ ነው ምክንያቱም ቴሌግራም ላይ የሚለቀቁትን ሀይማኖታዊ ሆና የፍቅር ታሪኮችን ማንበቤ ራሴ ላይ ያለውን ጭንቀት እንድረሳ ያደርገኛል በእውነቱ ሌላ የማማክረው ሰው ወይም ጓደኛ ስለሌለኝ ቴሌግራም ላይ መዋሌ አያስደንቅም ቤተሰቦቼ ብዙ ጊዜ ጎደኛ እንድይዝ እና ውጪ ወጥቼ እንድዝናና ቢነግሩኝም ብዙም ግድ የሚሰጠኝ ነገር አይደለም...

ሰኞ ከት/ቤት መልስ ቡሀላ መድረሳ ብገባም ዛሬ ሀዩ አልመጣችም ዛሬ መቅረቷ ሀሳቤን ጭንቀቴ እና ፍርሀቴን ይበልጥ ጨምሮታል ነገ ባትመጣስ ስለዚህ ካልመጣች ደብዳቤ ልፅፍና ለኢክራም ልልክላት ወስኜ መፃፍ ጀመርኩ ከብዙ መቸክቸክ እና ወረቀት መቅደድ ቡሀላ ይህን ፃፍኩ ።

ይድረስ ለምወድሽ የልቤ ውስጥ ሸራ ደጋግሞ ለሳለሽ:
ፍቅርሽ በልቤ ላይ የበላይ ላረገሽ:
የሀሳብ ጥምጣም ክር ጎንጉኖ ላበጀሽ:
ውብ እኔነቴ ከውበት ምድጃ ስር ከስሎ ማንነቴ:
አድርጎ ሾሞሻል ንግስቴ የኔነቴ:
ሆኖብኝ ከልቤ ባንዳ አጋፋሪ:
እኔነቴ ከስሟል ጀግናው ፊትአውራሪ:

መውደዴን ልነግርሽ በልቤ አስብና:
አላምነውም ልቤን ያንቺ ሆኖልና
ዳግም በሌላ ቀን ወዳንቺ ሳማትር:
ሂድ ንገር ይለኛል ሆላ ሊያስወረውር የፍቅርሽን በትር:
አመኔታ አጥቼ እኔው ከራሴጋ ልቅረፅሽ ልሳልሽ ቀኔ እስከሚነጋ።

በዚህ ደብዳቤ ላይ ልነግርሽ ያሰብኩት
አስቤ የፃፍኩት ፅፌ የሰረዝኩት:
ሰርዤ የላኩት ስርዝ ድልዝ ሆኖ አልነበብ ካለሽ ሳልሰርዘው በፊት:
ሀሳቡ መልዕክቱ - ምን ይላል መሰለሽ?

መግቢያው መደምደሚያው ሀተታው በሙላ:
ሌላ አይናገርም ከናፈቅሽኝ እና ካፈቀርኩሽ ሌላ።

ከአንቺው አፍቃሪ ሰሚር

ዛሬም ኢክራም ብቻዋን ነበር ከመድረሳ የወጣችው ደብዳቤውን ለኢክራም ከመስጠት ሌላ አማራጭ ስለሌለኝ ኢክራም ብዬ ጠራሆት አልፋኝ ልትሄድ ስትል "አቤት" አለች ፈገግ ብላ ነጭ የሆኑት ጥርሶቾ ልብን የይዛሉ ሀያትን ፈልጌ ነበር በሰላም ነው እንዴ ጠፋች? አልኳት አንገቴን አቀርቅሬ "እ ሀያትን ፈልገህ ነው እንዴ እነሱ እኳ አዲስ ቤት ሰርተው ቤት ለቀዋል ስለዚህ እዚህ መድረሳ አትመጣም" አለችኝ በድንጋጤ ከቅፅበት ፊት በላብ ተጠመቀ የት ነው የሄደችው አልኩ ካቀረቀርኩበት ቀና ብዬ "ደብረዘይት ነው የሄደችው " ደብረዘይት ለማንኛውም ይሄን ደብዳቤ ካገኘሻት ስጪልኝ ብዬ ሰጥቼት ሄድኩ የሚሰማኝን ስሜት አላውቅም እንባዬ ዱብ ዱብ እያለ ነው...

ልነግርሽ ያልኩለት አላየሽም እንጂ ብታይው ደስ ባለኝ:
ልነግርሽ ያልኩለት እንዴት እንደሆንኩኝ:
እንቅልፍ አልተኛሁኝ:
አንዳች አልቀመስኩኝ:
ስላንቺ ነው እንጂ ሌላም አላሰብኩኝ:
ለሊቱ ረዝሞብኝ:
ንጋት እርቆብኝ:
እንዲያ ስገላበጥ ቅብዝብዝ ሲያረገኝ:
አላየሽም እንጂ ብታይ ደስ ባለኝ።

ይቀጥላል...

@YEFKIR_LEZA
@YEFKIR_LEZA