Get Mystery Box with random crypto!

እውነት Vs ውሸት..! 'አንድ ቀን እውነት እና ውሸት ይገናኛሉ። ውሸት ለእውነት “ዛሬ አስደናቂ | የፍቀር ነገር... 🔥😍😉

እውነት Vs ውሸት..!

"አንድ ቀን እውነት እና ውሸት ይገናኛሉ። ውሸት ለእውነት “ዛሬ አስደናቂ ቀን ነው” ትላታለች። እውነት ወደ ሰማይ ቀና ብላ ትመለከትና እውነትም ቀኑ እጅግ ውብ መሆኑን ታስተውላለች። ከዚያም ቀኑን ሙሉ አብረው ያሳልፉና በመጨረሻ በአንድ የውኃ ጉድጓድ አጠገብ ይደርሳሉ ።

ውሸት እውነትን በድጋሚ “ውሃው በጣም ጥሩ ነው፤ አብረን እንታጠብ!” ትላታለች። እውነትም የጉድጓዱን ውሃ ባየች ጊዜ ጥሩ መሆኑን ተገነዘበች፡፡ በዚህም፣ እውነት የአብረን እንታጠብ ግብዣውን ተቀብላ ልብሳቸውን ከጉድጓዱ ዳር አስቀምጠው መታጠብ ይጀምራሉ።

መታጠቢያ ጉድጓዱ ውስጥ እያሉ ውሸት ከውሃው በድንገት ትወጣለች፤ የእውነትንም ልብስ ትለብስና ትሸሻለች። በሁኔታው በጣም የከፋት እውነት ከጉድጓዱ ትወጣና ውሸትን ለማግኘት እና ልብሷን ለመቀበል በየቦታው ትሯሯጣለች። በየመንገዱ የምታገኛቸው ሰዎች እውነትን እርቃኗን በማየታቸው በንቀት እና በንዴት ይመለከቷታል።

ውሸትን ሮጣ መያዝ ያልቻለችው ምስኪኗ እውነት ወደ ጉድጓዱ ተመልሳ የውሃው ጉድጓድ ውስጥ በመደበቅ ለዓለም ስትል እርቃኗን ለዘላለም ትሸፍናለች። እነሆ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ውሸት እንደ እውነት ለብሶ በዓለም ዙሪያ በመዘዋወር የኅብረተሰቡን ፍላጎቶች በማርካት ላይ ይገኛል፡፡

ዓለምም እውነትን የመፈለግ በጭራሽ ፍላጎት የለውምና የእውነት ለዘለዓለም በጉድጓዱ ውስጥ መቅረት አያስጨንቀውም። ዓለም፣ እውነት እርቃኗን ስትሆን የሚሸከምበት ሞራልም ስለሌለው በመደበቋ ደስተኛ ነው። ከውሸት የፀዳ፣ በእውነት ያሸበረቀ ቀን ተመኘሁ! መልካም ውሎ

@yefekrneger