Get Mystery Box with random crypto!

❤️የፍቅር ጨዋታ❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ yefeker_chewata1 — ❤️የፍቅር ጨዋታ❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ yefeker_chewata1 — ❤️የፍቅር ጨዋታ❤️
የሰርጥ አድራሻ: @yefeker_chewata1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.20K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-08-27 20:55:51 Fuck Romeo and Juliet I want what ቀጮ እና ጠጆ from የወንዶች ጉዳይ have
309 views◔͜͡◔ I ◔͜͡◔, 17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:55:50 My second break up was also in elementary she left me for "ዳርጌጌ ቡም ቡም" እያለ ለሚዘፍነው ልጅ
309 views◔͜͡◔ I ◔͜͡◔, 17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 19:37:30
395 views◔͜͡◔ I ◔͜͡◔, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 19:37:30
372 views◔͜͡◔ I ◔͜͡◔, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 19:37:30
370 views◔͜͡◔ I ◔͜͡◔, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 22:12:32
Jungkook my love
419 views◔͜͡◔ I ◔͜͡◔, 19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 07:36:06 እናት

....ቁጣን የሚያበርደው
ለሌላ የሚያስበው ያ ሁላ ደግነት
ዛሬ ከአይኔ ሳጣው
ልቤ ስብዕናሽን ከቶ ቢናፍቀው በዛ ብቸኝነት
ወዴት ብዬ ልሂድ በየትኛውስ መንገድ
አለሜን ፍለጋ ህይወቴን የእኔ እናት
እማ ፍቅርሽ እኮ
እስከ አለም ጥግ ብዞር ብሽከረከር የለሽ የሚተካሽ

ፀሐፊ:አብይ coffee
✦✦ ✦✦
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
Join us

@yefeker_chewata
@yefeker_chewata
@yefeker_chewata

…...…,•’``’•,•’``’•,M
…...…’•,’ ’ ,•’
...……...’•, ,•’,•’’•,•’’•,a
,•’’•,•’`’•,....’•,’ ’ ,•’
’•,’ ’ ,•’…....’•, ,•’m
’•,
971 viewsSpeed, 04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 07:36:06 ያበደው ፍቅሬ

ክፍል

ከምን ያክል ሰዓት በኋላ እንደሆነ አላውቅም.... ራሴን እዛ ጅምር የጭቃ ቤት ውስጥ ተኝቼ አገኘሁት። እንደምንም እየተንገዳገድኩ ከቤቱ ውስጥ ወጣሁ... ልብሴ በደም ተነክሯል፣ የሚሰማኝ የህመም ጥዝጣዜ ራሴን ሊያስተኝ ደርሷል ግን እንደምንም ተቋቁሜ ለመራመድ ሞከርኩ።
.....
.....

ብርሀን ለጨለማ ቦታዋን ብታስረክብም ደማቋ የምሽት ጨረቃ አካባቢውን በብርሀን ሞልታዋለች....

በቀስታ እየተራመድኩ ወደ መንገዱ ወጣሁ። አሁንም ደሜ አልቆመም በቀስታ ከጭኔ ላይ ሲወርድ ይሰማኛል። ከሩቅ ነጠላ ለብሶ የሚመጣ ሰው አየሁ አንደበቴን ከፍቼ ለመጣራት መከርኩ ግን በምጥ የወጡት ቃላቶች እንኳን ለሌላ ለኔም የሚሰሙ አልነበሩም።
......
......

ያለኝ አማራጭ ወደሚመጣበት አቅጣጫ ተራምጄ እንዲያየኝ ማድረግ ነው። እየቀረብኩት ስመጣ ቄስ እንደሆኑ ተረዳሁ.... አጠገባቸው ለመድረስ ትንሽ ሲቀረኝ ጉልበቴ ተብረከረከ፣ አቅሜ ተሟጠጠ፣ አጠገቤ መጥተው ያዙኝና

" ምነው የኔ ልጅ ችግር አለ ምን ሆነሽ ነው?" ድምፃቸው ከሩቅ የሆነ ያክል ይሰማኛል ። ልቤን ስልብ የሚያደርግ ህመም ተሰማኝ ከዛ በኋላ አላስታውስም
......
......

"ልጄ የኔ ስስት.... ምን አድርገውብኝ ነው? እባክሽ ተነሽ ሚጣዬ ተነሽልኝ..... የኔ ብቸኛ ልጅ... ያላንቺ ማን አለኝ.... ትተሽኝ እንዳትሄጂ.... ተስፋዬ.... ነገን የማይብሽ.... " አይኔን ሳልገልጥ የሰማኋቸው የእናቴ በሳግና በለቅሶ የታጀቡ ቃላቶች ናቸው... ከዛ ከባዱ ጨለማ ይውጠኛል።
ትንሽ ትንሽ ዙሪያዬ እየተፈጠረ ያለውን ነገር ባውቅም አይኔን ለመክፈት ወሰድ መለስ የሚያደርገኝን ጨለማ እና የተጫነኝ ከባድ ነገር መታገል ግድ ሆኖብኛል።
.....
....

"አሁንስ አልነቃችም አይደል" አለ የሆነ ጎርናና ድምፅ

" አልነቃችም ኢንስፔክተር ልጄን እንደዚህ ያደረገውን ሰው አገኛችሁት?" እማዬ ናት

" አይ... ወይዘሮ ወይንሸት አላገኘነውም እሱን ለመያዝ የልጆት ቃል ያስፈልገናል" የበር መዘጋት ድምፅ ተሰማኝ እኔም ወደዛው ጨለማ የሄድኩ መሰለኝ.... እንቅልፍ
.....
.....

ዛሬ የተሻለ ጥንካሬ ይሰማኛል። ልክ አይኔን ስግልጥ እናቴን አጠገቤ አየኋት የአልጋውን ጠርዝ ተደግፋ እንቅልፍ ወስዷታል። እጄን አንቀሳቅሼ ፊቷን ስዳስሳት ተነሳች... ወዲያው እልልታዋን አቀለጠችው።

"ልጄ ነቃሽልኝ የኔ ስስት.... ተመስገን ልጄ ነቃች" ዶክተሩ ምርመራ እስከሚያደርግልኝ ውጪ እንድትቆይና ነገራትና አንዳንድ ህክምናዎች ካደረገልኝ በኋላ

"ፖሊስ መጥቶ ቃልሽን ይወስዳል... እንደዚ ያደረገሽ አውሬ እንዲያዝ ከፈለግሽ ምንም ሳትፈሪ ሁሉንም ለመናገር ሞክሪ.... ደግሞ አይዞሽ በሚያስፈልግሽ ሁሉ ከአጠገብሽ አለን..." ብሎኝ ክፍሉን ለቆ እንደወጣ ሁለት ፖሊሶች ተከታትለው ገቡ።
....
.....

ከ አንድ ወር በኋላ
የሰፈር ሰው ሰምቶ ስለነበር ግማሹ ሲያዝን ግማሹ ደግሞ የራሱን መላምት ማስቀመጥ ጀመረ።
"ፈልጋ ነው እንጂ ሳትፈልግ ማን ሊነካት..." በነገር የምትታወቀው ብርቄ

"ኧረ ተይ እንደዚህማ አትበይ እናቷ እኮ መድሀኒት ቤት ልካት ስትሄድ አግኝቷት ነው አሉ" የእናቴ ጓደኛ አየለች

"ኡኡቴ እና ምን ልትልልሽ ኖሯል ልጄ ከኔ ተደብቃ ወንድ ፍለጋ ሄደች ትበልልሽ እናቷ እኮ ነች። ደግሞስ ከመች ጀምሮ ነው ሚጣን መድሀኒት ማስገዛት የጀመረችው...."

ከዚህም የባሱ ብዙ ሽሙጥና ስድቦችን በተቃራኒውም ብዙ አይዞሽ በርቺ የሚሉ ቃላቶችን እሰማለሁ። ለኔ ግን ከአስር አይዞሽ አንድ ምናባሽ ልቤን ያርደው ነበር። ጭምትና በትንሽ ነገር የምበረግግ ፈሪ ሆንኩ።

እኔ እምቢ ብልም በእናቴ ጉትጎታ ወደትምህርት ቤት ሄድኩ። እዛም የባሰው ነገር ጠበቀኝ አንድም ሊቀርበኝ የሚፈልግ ልጅ የለም ሁለም ራቅ ራቅ ብለው በዩኒፎርማቸው ኮሌታ አፋቸውን ሸፍነው ይንሾካሾካሉ።

ሁሉም ነገር ሊያሳብደኝ ደረሰ የሚያውቁኝ እንደማያውቁኝ ሲሆኑብኝ ጓደኞቼ እኔን ለመቅረብ ሲፈሩ ማየት አሳመመኝ። ምንም ሳልል ቦርሳዬን ይዤ ከትምህርት ቤት ወጣሁ። አረማመዴ ሁላ የእልህ ነበር። ቤት ስደርስ እማዬን አሻሮ እየቆላች አገኘኋት...

" ከዚህ ከተማ አስወጪኝ... እማ ለምን እልም ያለ ገጠር አይሆንም ሄጄ የከብት እረኛም ቢሆን እሆናለሁ ብቻ ከዚህ አርቂኝ ' እግሯ ላይ ተደፍቼ እየተንሰቀሰኩ ለመንኳት

"ችግርሽ ሳይገባኝ ቀርቶ መሰለሽ እኔም ወሬው ሰልችቶኛል የኛ ሰፈር ሰው እንኳን ይቺን አግኝቶ.... እህ.. መች አጣሁት... ግን የፖሊሶቹ ምርመራ አልቆ ያን እርኩስ ሰው ታስሮ ሳላይ ከዚህ ንቅንቅ አልልም። ያኔ እውነቱ ሲታወቅ አንቺም ቢሆን አንገትሽን ቀና አድርገሽ ትሄጃለሽ" እንባዬን ጠራርጋ እና አባብላ ብዙ መከረችኝ ምክሮቿም ብርታት ሆኑኝ።
....
.....

ምንም እንኳን በተኛሁበት መበርገጌ የምጥ እንቅልፍ መተኛቴ ባይቀርልኝም የሰፈሩ ሰው ግን ቀስ በቀስ ወሬውን እየረሳው ጓደኞቼም " ነይ እንጫወት" እያሉ መምጣት ጀመሩ።

ትምህርት ቤትም ተማሪዎቹ እንደድሯቸው ሆኑልኝ እኔ ግን እንደድሮዬ መሆን አቃተኝ ትምህርት ስማር በሀሳብ ጭልጥ ብዬ እሄዳለሁ... ወንድ አስተማሪ ሲገባልን እሱም ልክ እንደዛ ሰው አውሬ እንደሆነ አስብና እጠላዋለሁ ከመምህሩ እኩል የሚያስተምረውም ትምህርት ያስጠላኛል። እንዳዛ እንደዛ እያለ የእናቷ " ሚጣ" እኔ 'ሩት በዛብህ' ከማንነቴ ተፈናቅዬ እንዳልነበርኩ ሆንኩ። ሰው ሲያየኝ እንደበፊቱ ብመስልም ውስጤ የተረበሸ ከተማ ሆነ።
....
.....

ከአራት ወር የፓሊሶች ምርመራ እና ድካም በኋላ ውጤቱ ፍሬ አልባ መሆኑን ለእናቴ ነገሯት.... ደፋሪዬ ደብዛውም የለም። እኔ በነገርኳቸው ትንሽ ምልክት ብቻ እሱን ለማግኘት መሞከር እንደሚከብዳቸው ስለገባኝ አላዘንኩባቸውም።
....
....

ከእለታት በአንደኛው እሁድ
ፀጉሬን ከታጠብኩ በኋላ ገላዬን ልታጠብ የበርሜል ጉራጅ ላይ ቁጭ ብዬ ሙቅ ውኋዬን እስከምታመጣ እናቴን እየጠበኩ ነው። ውሃው መጣና እኔ ከፊቴ እናቴ ደግሞ ከጀርባዬ እያጠበችኝ
"እስኪ እጅሽን ዞር አድትጊ አሁን በዚህ ጭራሮ እጅሽ አሽተሽው ነው የሚጠራው..." ሁሌም እናቴ ከፊት ለፊቴ ልታጥበኝ ስትል የምትለው ነገር ነው። ልማዴ ስለሆነ እኔም አልቃወማትም እጄን ከፍ አድርጌላት እያጠበችኝ ድንገት የያዘችውን ውሃ የያዘ ጆግ ለቀቀችው። በርሜል ውስጥ ስለወደቀ ከስር ያለው ውሃ ተፈናጥሮ አለበሰኝ።

'እንዴ እማ ምን ሆነሽ ነው ታጥቤ ታጥቤ' ተነጫነጭኩና ጆጉን አንስቼ ውሃ ልቀዳ ስል

"ቆይ ቆይ ቆይ እስኪ አንዴ ቁሚ" አለችኝ። ቀና ብዬ ሳያት ደንግጣለች

'እማዬ ምን ሆነሻል' አልኳት

"ወሬውን ትተሽ ያልኩሽን አድርጊ" ብላኝ እየተርበተበተች እጄን ይዛ አቆመችኝና ፍጥጥ ብላ ሆድ ሆዴን ካዬች በኋላ

"ልጄ" አለችኝ በሚያሳዝን ቅላፄ

'ወዬ እማ ለምን ነው እንደዚህ የምታይኝ'

"ሆድሽ" ጎንበስ ብዬ አየሁት እኔንም አስደነገጠኝ

'አብጦ ነው እማ? ወይስ እንደ ምንትዋብ ቁዝር ልሆን ነው' አልኳት።

ይቀጥላል
@yefeker_chewata
@yefeker_chewata
@yefeker_chewata
ከወደዳችሁት
818 viewsSpeed, 04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 07:36:06 ቀጫጫዋ እና ሆዷ ቁዝር ያለውን የክፍላችንን ልጅ ምንትዋብን አስታውሼ ማንም ምንትዋብ ብሎ የሚጠራት የለም ሁሉም "ቁዝር" ነው የሚሏት። እኔም እንደሷ ቁዝር እየተባልኩ የተማሪዎች መሳለቂያ ልሆን ነው.... ወይኔ... ከሄድኩበት ሀሳብ እናቴ ልብሴን እላዬ ላይ ስታሳርፈው ተመለስኩ

' እንዴ እማ በደንብ ሳልታጠብ' እንዳልሰማ ዝም ብላ አለበሰሽኝና እየተጣደፈች ወደቤት ገባች። ተከትያት ገባሁ ነጠላዋን ለበሰችና እኔንም አነስ ያለች ፎጣ አለበሰችኝ

'ወዴት ልንሄድ ነው እማዬ'

"ሀኪም ቤት"

'ሳልታመም'

"አይ ታመሻል" እጄን ይዛኝ ስትሄድ በዝምታ ተከተልኳት
....
......


እናቴ ቁጭ ብላ እንባዋን ታዥጎደጉደዋለች። እኔ በድንጋጤ ደርቄ ምን ማሰብ እና መናገር እንዳለብኝ ግራ ገብቶኝ ቆሚያለሁ። ድንገት የሆነ ሀሳብ መጣልኝና ከቆምኩበት ኮሊደር ላይ ሳላንኳኳ የዶክተሩ ቢሮ ገባሁ።

"አቤት ሩት" አለኝ ዶክተሩ ካቀረቀረበት ቀና ብሎ ካየኝ በኋላ

'ማስወረድ እፈልጋለሁ' አልኩት

"ምን" የሚል ድምፅ ስምቼ ስዞር እናቴ ከኋላዬ ቆማለች።

ይቀጥላል



ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@yefeker_chewata
@yefeker_chewata
627 viewsSpeed, 04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 07:36:06 በህይወት በፍፁም ማንንም አትውቀስ።
ምክንያቱም
ጥሩ ሰዎች………………………ደስታን

መጥፎ ሰዎች………………….ልምድን

ክፉ ሰዎች……………………...ትምህርትን

መልካም ሰዎች………………..ትውስታን

ይሰጡሀልና።



𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 𝐒𝐇𝐄𝐑

@yefeker_chewata
@yefeker_chewata
569 viewsSpeed, 04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ