Get Mystery Box with random crypto!

ቀጫጫዋ እና ሆዷ ቁዝር ያለውን የክፍላችንን ልጅ ምንትዋብን አስታውሼ ማንም ምንትዋብ ብሎ የሚጠራት | ❤️የፍቅር ጨዋታ❤️

ቀጫጫዋ እና ሆዷ ቁዝር ያለውን የክፍላችንን ልጅ ምንትዋብን አስታውሼ ማንም ምንትዋብ ብሎ የሚጠራት የለም ሁሉም "ቁዝር" ነው የሚሏት። እኔም እንደሷ ቁዝር እየተባልኩ የተማሪዎች መሳለቂያ ልሆን ነው.... ወይኔ... ከሄድኩበት ሀሳብ እናቴ ልብሴን እላዬ ላይ ስታሳርፈው ተመለስኩ

' እንዴ እማ በደንብ ሳልታጠብ' እንዳልሰማ ዝም ብላ አለበሰሽኝና እየተጣደፈች ወደቤት ገባች። ተከትያት ገባሁ ነጠላዋን ለበሰችና እኔንም አነስ ያለች ፎጣ አለበሰችኝ

'ወዴት ልንሄድ ነው እማዬ'

"ሀኪም ቤት"

'ሳልታመም'

"አይ ታመሻል" እጄን ይዛኝ ስትሄድ በዝምታ ተከተልኳት
....
......


እናቴ ቁጭ ብላ እንባዋን ታዥጎደጉደዋለች። እኔ በድንጋጤ ደርቄ ምን ማሰብ እና መናገር እንዳለብኝ ግራ ገብቶኝ ቆሚያለሁ። ድንገት የሆነ ሀሳብ መጣልኝና ከቆምኩበት ኮሊደር ላይ ሳላንኳኳ የዶክተሩ ቢሮ ገባሁ።

"አቤት ሩት" አለኝ ዶክተሩ ካቀረቀረበት ቀና ብሎ ካየኝ በኋላ

'ማስወረድ እፈልጋለሁ' አልኩት

"ምን" የሚል ድምፅ ስምቼ ስዞር እናቴ ከኋላዬ ቆማለች።

ይቀጥላል



ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@yefeker_chewata
@yefeker_chewata