Get Mystery Box with random crypto!

መነበብ ያለበት አንድ ወጣት መንገደኛ አንድ ቀን አንድ በጣም ያረጁ ሽማግሌ የዛፍ ችግኝ ሲተክ | Yechalal ይቻላል ! በጎ አድራጎት ማህበር

መነበብ ያለበት

አንድ ወጣት መንገደኛ አንድ ቀን አንድ በጣም ያረጁ ሽማግሌ የዛፍ ችግኝ ሲተክሉ ያገኛቸው እና "የምን ችግኝ ነው የሚተክሉት አባቴ?" ብሎ ይጠይቃቸዋል ።እርሳቸውም "ጣፋጭ ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ ነው። "ይሉታል፡፡

"ከስንት ዓመት በኋላ?"በማለት ሲጠይቃቸው፣ "ተሰባ ዓመት በኋላ"ሲሉት ወጣቱ በጣም ይገረምና፣ "ከፍሬው ላይቀምሱ ምን ያደርግልዎታል? እንዲያው በከንቱ ነው የሚለፉት።" ይላቸዋል፡፡ሽማግሌው በወጣቱ ነገር ተገርመው "አይ ልጄ እንዳልከው እኔ አልደርስበትም ፡፡ግን ወደዚህ ዓለም ስመጣ ዓለም ባዶ አልነበረችም፡፡እኔም ከሄድኩ በኋላ ባዶ አትሆንም ፡፡እኔ ስበላ የኖርኩት ፍሬ አባቶቼ ከተከሉት ዛፍ ነው። እኔም በተራዬ ለልጆቼ በመትከል ላይ ነኝ። "አሉት ይባላል፡፡

በምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ ላይ ትውልድን እናስብ።