2022-08-30 14:06:22
20 ምርጥ መልዕክቶችን ላካፍላችሁ
1 ነገሮች ሲጠኑባችሁ ወደ ሱጁድና ዱዓእ ፍጠኑ እንጂ ብሶትና ለቅሶ አታብዙ፡፡
2 ሁሉም ነገር ይሄዳል፤ ሲሄድ ግን አይመለስም፡፡ ዱዓእ ሲቀር፡፡ ዱዓእ ተስፋን፣ በረከትን፣ ሲሳይን፣ ድልን፣ ስጦታን ይዞ ይመለሳል፡፡
3 በምድር ላይ አንድም ስኬታማ ሰው የለም፡፡ ለወላጆቹ መልካም የመዋል ታሪክ ያለው ቢሆን እንጂ፡፡
4 የሰው ልጅ ሆኖ ከሀሳብ ነፃ የሆነ የለም፡፡ ሆኖም ግን ያለበት ሀገር ዱንያ መሆኗን እያስታወሰ ፈገግ የሚል ብዙ ሰው አለ፡፡
5 ምርጦቹ ጓደኞችህ ዱንያ የሳቀችልህ ቀን አይደናገጡም፡፡ በዞረችብህ ጊዜም አይደሰቱብህም፡፡
6 ግርማ ሞገስን ከሚያጎናጽፉ ነገሮች መካከል ብዙ አለማውራት፤ የፊትን ዉበት ከሚጨምሩ ነገሮች መካከል ፈገግታን ማብዛት ይገኙበታል፡፡
7 የሰው ልጅ ባያምንበትም እንኳ የሚናገርን ሰው ሀሳብ ቢያዳምጥ የሚማረው ነገር ይኖራል፡፡
8 ልጅህን ቁርኣንን አስተምረው፤ ቁርኣን ሁሉንም ነገር ያስተምረዋል፡፡
9 ትላልቅ ሰዎችን አክብሩ፤ ዘመናቸው ባልሆነ ዘመን ውስጥ እየኖሩ ነውና፡፡
10 ሁሉንም ሰው ለማስወደድና ለማርካት አትፍጨርጨር፡፡ በዚህ ጉዳይ ነቢያትም እንኳን አልተሳካላቸውምና፡፡
11 ዉስጥህን ህመም እየተሰማህ ፈገግ የምትል ከሆነ የጥንካሬህ ማሳያ ነው፡፡
12 የሰው ልጅ የሚመዘነው ባለው ነገር ሳይሆን በሚሰጠው ነው፡፡ ፀሐይ እሳት ጭምር አላት ነገርግን ብርሃን ትሠጣለች፤ ፍጥረተ ዓለሙን በብርሃን ትሞላለች፡፡
13 በእናቱ እግር ሥር አገልጋይ ሆኖ የኖረ በሰዎች አናት ላይ ንጉስ ሆኖ ይኖራል፡፡
14 ብዙ በመናገር የማይታወቅ ሰው መናገር ሲጀምር ትኩረት ይስባል፡፡
15. ባመለጠችህ አንዲት ኮከብ አትከፋ፡፡ ሰማይ በከዋክብት የተሞላች ናት፡፡ እሷን ከረሳህ ምናልባት ጨረቃ ትወጣልህ ይሆናል ማን ያውቃል፡፡
16. ከአላህ (ሱብሀነ ወተአላ.) መልካም ነገር እንጂ አላየንም፣ አልሰማንም፡፡ ወደ ቀናው መንገድ መራን፣ ጤና ሰጠን፣ ዕድሜ ሰጠን፣ ቤተሰብ ሰጠን፣ ብዙ ብዙ ነገር ሰጠን፡፡
17. ልንረሳቸው ብንፈልግ እንኳን ዉስጣችን የማይረሳቸው ብዙ ኃጢአቶችን ይዘን እየዞርን ነው፡፡
18 . የሐዘን ባቡር ፉርጎው ቢበዛም ቢረዝምም የመጨረሻ ፌርማታው ደስታ ስለመሆኑ አንጠራጠር፡፡
ዕድል
19. ዕድሜ ዕድል ነው፡፡ አንዳንድ ደግሞ ዕድሜ ነው፡፡ ዕድሜህ ሊሆን የሚችልን ዕድል በቀላሉ አታሳልፍ፡፡
20 . የተጃጃለ ሰው ሁኔታው እንደ በራሪ አዕዋፍ ነው፡፡ ከፍ ባለ ቁጥር ሰውን አሳንሶ ይመለከታል፡፡https://t.me/ye_ewqetmahder
336 viewsያሙቀሊበል ቁሉብ ሰቢት ቁሉበና አላ ድንክ alhamdulilah, 11:06