2021-12-16 19:40:07
ዝኩኒን /Cucumber/ መመገብ የጤና ጥቅሞች #ዝኩኒ በፈረንጆቹ ደግሞ ኩከንበርግ እየተባለ የሚጠራው ይህ የአትክልት ዝርያ በአለም በከፍተኛ ደረጃ ከሚመረቱ የአትክልት ዓይነቶች አራተኛ ደረጃን ይዟል፡፡
እስቲ ይሄን አስደናቂ የምግብ ዓይነት መመገብ ያለውን 14 ጥቅሞች ትንሽ እናውጋቹሁ፡-
1. አትክልቱ 90 በመቶ የሚሆነው ይዘቱ ውሃ በመሆኑ የሰውነታችን የውሃ ፍላጎትን ያሟላል፡፡
2. በፀሐይ ንዳድ የሚመጣ የሰውነት ሙቀትን ያበርዳል።
3. በሰውነት ውስጥ የሚገኙ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ያሶግዳል።
4. ለሰውነታችን በሽታ መከላከል አቅምና ሀይል የሚሰጡ ቫታሚን ኤ ፣ቢ ፣ሲን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ቫይታሚኖችን ያበረክታል።
5. ለሰውነት ቆዳ ተስማሚ የሆኑ ፖታሺዮም ፣ማግኒዢየም እና ሲሊከን ንጥረ ነገሮችን ይዟል።
6. በሰውነት ውስጥ ለምግብ መንሸራሸር እና ለክብደት ለመቀነስ ይረዳል።
7. በስሱ የተላጠ ዝኩኒ አይን ላይ ማድረግ የአይን ጤንነትን ይጠብቃል።
8.የተለያዩ የካንሰር በሽታ አደጋዎችን ለመቀነስ ይጠቅማል ወይም የካንሰር በሽታን ለመከላከል ይረዳል።
9.የስኳር በሽታን ለመፈወስ ፣በሰውነት ውስጥ ያለውን የቅባት መጠን ለመቀነስ እና የደም ግፊትን ለመቆጣጠር ይጠቅማል።
10.የአፍ ጤንነትንና ጠረን ይጠብቃል።
11.የሰውነታችን ፀጉር እና ጥፍር ጤናማ እድገት እንዲኖራቸው በመርዳት ጠንካራና አንፀባራቂ እንዲሆኑ ይረዳል።
12.የሰውነታችን የአጥንት መገጣጠሚያ እንዲጠነክሩ ያግዛል።
13.ከአልኮል መጠጥ በሃላ አትክልቱን ከተመገቡ አንግጎቨርና እራስምታት እንዳይከሰት ይረዳል።
14.በሰውነታች ውስጥ የሚገኝ ዮሪክ የተባለ አሲድ መጠን እንዲቀንስ በማድርግ የኩላሊታችንን ጤንነት ይጠብቃል።
➹share &Join Us
@ye_ewket_mahider
410 viewsᎽᎥᏕᎪᏦ Ꭰ, 16:40