Get Mystery Box with random crypto!

ማቅለጫ ምድጃዎች፣ ቅርፅ ማውጫዎቹ ሁሉ ወደ ፍርስራሽ ኮረብታነት ተለወጠ። የተጀመሩት የመንገድ ሥራ | Yalelet Wondye

ማቅለጫ ምድጃዎች፣ ቅርፅ ማውጫዎቹ ሁሉ ወደ ፍርስራሽ ኮረብታነት ተለወጠ። የተጀመሩት የመንገድ ሥራዎች ባሉበት ቆሙ። ተሠርተው አግልግሎት መስጠት ጀምረው የነበሩት ጋሪዎች በተረተሩ ወድቀው ቀሩ። በጣና ሐይቅ ላይ የሚንሳፈፉ ጀልባዎችን ለማሠራት የነበራቸው ምኞትም ሰምጦ ቀረ። በጥቅሉ የቴዎድሮስ የተሃድሶ ሥራዎቻቸው ተቋረጡ። ፈጠራዎቻቸውም ያለ ጥቅም ቀሩ።

ምናልባት ቴዎድሮስ ህዝቡም፣ ቀሳውስቱና ሽፍታው እንቅፋት ባይሆንባቸው ኖሮ ለዐማራ ብሔርተኝነት ማበብ ጀምረውት የነበረውን የዐማራ ግዛቶችን በመንገድ፣ በአስተዳደርና በኢኮኖሚ የማስተሳሰር ሂደት ጠንካራ የዐማራ ክልላዊ ብሔራዊ አንድነት መፍጠር ይቻል ነበር። ነገርግን ህልማቸውንም ትልማቸውንም የተረዳችው ባለመኖሩ ያነን ተከትሎ በወሰዱት እርምጃ ደጋፊ ከማሳጣቱ በላይ ከእንግሊዞች ጋር የገቡት ውዝግብ የራዕያቸው መቋጫ የሕይወታቸው መጨረሻ ሆነ። ጀምረውት የነበረው የዐማራ ብሔርተኝነት መጠናከር የዐማራ ብሔር ምሥረታም በአጭር ተቀጨ። ምናልባት የዎድሮስ ትልም ተሳክቶ ቢሆን ኖሮ የዐማራው ብሔርተኝነት መግለጫ አሁን ካለበት የተለየ መልክ ይዞ በቆየን ነበር።