Get Mystery Box with random crypto!

ምዕራፍ 1 የሐዋርያው የጳውሎስ መልዕክት ወደ ፊልጵስዩስ 1:1-2 1፤ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪ | Yeka Abado Full Gospel Belivers'church

ምዕራፍ 1

የሐዋርያው የጳውሎስ መልዕክት
ወደ ፊልጵስዩስ 1:1-2

1፤ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤


2፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።


ጳውሎስ እራሱንና አብሮት የሚያገለግለውን ጢሞቴዎስን የኢየሱስ ባርያ ብሎ ይጀምራል ጽሁፉን::


ኢየሱስ ጌታዬ ነው በሰራሁት ስራ ሁሉ ጌታዬን ለማስደሰት ነው እያለ ይህንን እንደመረጃ እየሰጠ ያለው::

የተጻፈላቸውም የቤተክርስቲያንዋ አገልጋዮችና እንዲሁም ምዕመኑ በሱ አጠራር ቅዱሳን ብሎ ይጠራቸዋል ዛሬም ለኛ ቢጽፍ እንደዚህ አድርጎ ነው የሚጠርን ደግሞም ቅዱሳን ነን በጌታ ከመዋጀታችን የተነሳ::


የመግቢያው ሰላምታ እንደሰላምታ ብቻ አይደለም ባርኮትም አለበት ከአባታችን እንዲሁም ከኢየሱስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን:: አሜን!

ማንም በክርስቶስ ካልሆነ በስተቀር ይህንን ሰላም መለማመድ አይቻልም።

እርሱ የሚሰጠን ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው አይነት አይደለም ይልቁንም አእምሮን ሁሉ የሚያልፍ ነው::

ዛሬም ሰላሙና ጸጋው ይብዛልን ይትረፍረፍልን::