Get Mystery Box with random crypto!

#ማ_ይንገርሽ ♡ ♡ ብዙ አስብና ማፍቀሬን ልነግርሽ መኖሬ ላንቺ ነው ወድሻለሁ ልልሽ ግና ገና | የወልቂጤ💕 ተማሪዎች❤ብቻ😳👌

#ማ_ይንገርሽ


ብዙ አስብና ማፍቀሬን ልነግርሽ
መኖሬ ላንቺ ነው ወድሻለሁ ልልሽ

ግና ገና ሳይሽ

ያ ሁሉ ስቃየን አይደለም ልናገር
ላንቺ የሆንኩትን እንኳን ልመሰክር

ጉልበቴም ይዝላል
አካሌም ይደክማል
ልሳኔም ይዘጋል
ልቤም ያው ይፈራል

ታዲያ የኔ ፍቅር

የልቤን ፍላጎት አፌ ካላወራው
ፍቅርሽን መራቤን ልቤ ካላወጣው
ገና ሳይሽ አንቺን ጉልበቴ ከዛለ
አካል እስትንፋሴ ባንቺ ከተከለለ

ማን ይንገርሽ እና እንዴትስ ታቂያለሽ
እስከ ሞቴ ድረስ እኔ እንደምወድሽ

   ┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
      ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
      @yaberus_school_2