Get Mystery Box with random crypto!

'' ፍቅሬ ብለህ ጥራኝ '' አወ አብርን አድገናል አፍርም ፍጭተናል በአንድ ስሀን ብልተን ባንድ | የወልቂጤ💕 ተማሪዎች❤ብቻ😳👌

"" ፍቅሬ ብለህ ጥራኝ ""

አወ አብርን አድገናል አፍርም ፍጭተናል
በአንድ ስሀን ብልተን ባንድ አልጋ አድርናል
የልጅነት ነገር ሆኖብን ነገሩ ባሌ ሚስቴ
ተባብለን ነበር እንዲት ደስ ይል ነበር አወይ ልጅነቴ

የስውነት ግዝፍት የእድሜም መርዘም
የአእምሮ መብስል ማስብ ማገናዘብም
ተጅምሮ ዛሬ አይናፍርነትም መጣ ተከትሎ
እንዱ ሲያለቅስ አንዱን ላያስቅ አባብሎ

ልክ እንደ ልጅነት እንደጥንቱ ግዜ
ድንገት ሳላስበው ነይ እህት አለም በምትለኝ ግዜ
ውስጤን ይከፍዋል ከእህትነት ይልቅ ፍቅርህ ከብዶታል
እንዳልተነፍስው እንዳልናገርው ልቤ ፍራተባ ይላል

እስኪ በል ንገርኝ ልክ እንደልኝነት
እንደ መልካሙ ጊዜ እንዲያ እንዳለፍንበት
ፍቅሬ ብለህ ጥራኝ ካልሆነልህ ሚስቴ
ተንፍስልኝና እኔም እፎይ ልበል ይፍታ ምኞቴ

ፍቅሬ ብለህ ጥራኝ እንደ ልጅነቴ
ባሌ ብዬ ልጥራህ ይሳካ ምኞቴ
@yaberus_school_2