Get Mystery Box with random crypto!

በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና በመከናወን ላይ የሚገኙ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ግምገማ | Addis Ababa Education Bureau

በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና በመከናወን ላይ የሚገኙ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ግምገማ ዛሬም ቀጥሎ ተካሂዱዋል፡፡

(ሰኔ 19/2016 ዓ.ም) መርሀ ግብሩ የኢትዮ ቴሌኮም ባለሙያዎችን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፤ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮች እንዲሁም የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን የኢትዮ ቴሌኮም ባለሙያዎች በነሱ በኩል የተከናወኑ የኮኔክቲቪቲና ተያያዥ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዱዋል ።

በከተማ አስተዳደሩ የ2016ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በስኬት ለማጠናቀቅ ከኢትዮ ቴልኮምና ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በቅንጅት በተሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆን መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ገልጸው በመጪው ቅዳሜ በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች በተመሳሳይ ሰአት ለተማሪዎች የሙከራ ፈተና ኦንላይን ተሰጥቶ የፈተና ጣቢያዎቹን ዝግጁነት የማረጋገጥ ስራ እንደሚሰራም አስገንዝበዋል፡፡