Get Mystery Box with random crypto!

Virtuous women💃💃let's learn

የቴሌግራም ቻናል አርማ womensletlearn — Virtuous women💃💃let's learn V
የቴሌግራም ቻናል አርማ womensletlearn — Virtuous women💃💃let's learn
የሰርጥ አድራሻ: @womensletlearn
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.16K
የሰርጥ መግለጫ

Let's learn girls
#be strong 💪
#be wisely 👌
#be clever😙
#be discerning😑
You r number one😘
Created date april22/2021

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-18 19:49:32 እናት ልባም ሴት



እናት ስንል ወደ አይምሮዋችን ሊመጣ የሚችለው ሩህሩህ፣ ደግ፣ ፣አዛኝ፣ካላት ለሌሎች ደራሽና ተቆራሽ፣ መጋቢ ፣ ለልጆቿ እጅጉን ተጨናቂና አሳቢ፣ ቤት እንዳይፈርስ ጥፋትን ሸፋኝ ገበናንም ደባቂ ብሎም ከማህበረሰብ ጋር ተግባቢ በአጠቃላይ የፍቅር ሴት ማለት ናት

ታዲያ እናት ማለት ከብዙ በጥቂቱ ይህችን ሴት ትመስላለች ከላይ የተዘረዘሩት ባህሪዎቿ ሙሉ ለሙሉ ማለት ይቻላል አንዲት ጠቢብ ልባም ሴት የምታደርጋቸው ነው አየሽ አንቺ ሴት ልባም ሴት ማለት "የእናትነት ባህሪን" የያዘች ሴት ማለት ናት

"እናትነት የሚገኘው በልባምነት ውስጥ ነው"

የአንቺ ልባምነት የእናትነትን ባህሪ ሊያመጣ ይችላል ታዲያ አንቺ ምን ያክል የእናትነት ባህሪ አለኝ ብለሽ ታስቢያለሽ እውነት ለሰው አዛኝ፣መጋቢ፣ለጋሽ፣ገበና ሸፋኝ… ነሽን ብዙ ጊዜ ሰው ይህ የእድሜ ጉዳይ ይመስለዋል እውነት አዎን ግን መብሰል የእድሜ ጉዳይ ብቻ አይደለም ራስን ለነገሮች ዝግጁ ማድረግም እንጂ

ዛሬ ሆነሽ የእናትነትን ባህሪ ለመላበስ ሩጪ ትጊም አንዳንድ ሴቶች ገና በወጣትነታቸው እድሜ ምናምን ሰዎች" ውይ ይህች ልጅ እንዴት ያለች እናት የሆነች ልጅ ናት " ሲል እንሰማለን ስለዚህ ለነገ ዛሬ ነውና የሚሰራው ዛሬ ላይ ራስሽን ለመልካም ነገሮች ዝግጁና የቀባይም ለመሆን እጅጉን ትጊ የሚጠቅመው ይህ ነውና

@behayluminilu
@behayluminilu
577 views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 20:44:31 የወደድከው ሁሉ አይጠቅምህም!
፨፨፨፨፨፨፨////////////፨፨፨፨፨፨፨
የህይወት ትምህርት ግሩም ነው። አንዳንዴ አንድን ሰው ብትወደውም ምርጫህ ግን መለያየት ይሆናል፤ አንድን ሰው ብትናፍቀውም ከህይወትህ ስለወጣ ግን ደስተኛ ትሆናለህ፤ ትልቁን ስፍራ ብትሰጠውም ከእርሱ መራቅን ትመርጣለህ፤ አክባሪው፣ ወዳጁ ብትሆንም ቅርበቱን የማትፈልግበት ጊዜ ይኖራል። ይበልጥ የሚጠቅምህን ለማስቀደም የምትወደውን ትተዋለህ፤ የሚያስፈልግህን ለማግኘት የምትፈልገውን ትጥላለህ፤ መንገድህን ለማጥራት ከስሜትህ በላይ ታስባለህ፤ ለእራስህ ትጠነቀቃለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! አንተ የፈለከው ሁሉ ትክክለኛ ምርጫህ የማይሆንበት ጊዜ አለ። ፍላጎት ሌላ ምርጫ ሌላ ነው። ምርጫህ የምትፈልገውን፣ የወደድከውን፣ ልብህ የደነገጠለትን ሳይሆን የሚጠቅምህን፣ የሚበጅህንና የሚያስፈልግህን ነው። በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ቅድሚያ የምትሰጠው ነገር ይኖራል። አንድን ሰው ከእራስህ በላይ ስለወደድከው ብቻ የእራስህ ልታደርገው አትችልም። ቀዳሚው ያንተ ህልውና ነው፤ ዋናው ጉዳይ የፍቅርህ ቅቡልነት ነው። ምንም እንኳን አንድን ሰው ከልብህ ብትናፍቀው፣ ብታስብለት፣ ብትሳሳለት የህይወት አጋርህ ስላልሆነ ደስተኛ መትሆንበት ጊዜ አለ። ምክንያቱም ያንተ ናፍቆትና ስስት የሰውየውን ማንነት የመቀየር ደረጃ ላይ ስላልደረሰ፣ ከናፍቆቱና ከሃሳቡ በላይ አብረሀው መሆንህ አብዝቶ ስለሚጎዳህ።

አዎ! የወደድከው ሁሉ አይጠቅምህም፤ የተመኘሀው ሁሉ አያሳድግህም፤ የምትለምነው ሁሉ አያሳልፍህም። በስሜትህ ልክ ብትወደውም፣ በግንዛቤህ አቅም ትጥለዋለህ። የወደዱትን ስራ መስራት ጥሩ ነው፤ ነገር ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ካመዘነና በህይወታችን ለውጥ ካላመጣ ምንም ዋጋ የለውም። ከውሳኔህ በፊት ስሜትህን አስተካክል። በስሜት የተጀመረ ህይወት በስሜት አይገፋም። ምርጫና ውሳኔህን ከጥቅምህ አንፃር ቃኛቸው። ብትወደውም ካልጠቀመህ የመተው አቅመን ተላበስ፤ ቢናፍቅህም ባለማግኘትህ ደስተኛ ከሆንክ ይቅርብህ። ከቻልክ የወደድከው እንዲጠቅምህ አድርግ ካልሆነ ግን በፍቅር ሳቢያ ከሚመጣብህ ጥቃት እራስህን ተከላከል፤ አንተ ከኖርክ ዳግም የሚጠቅምህን መውደድ ትችላለህና በውዴታ ፍቅርህን ለደህንነትህ ብለህ መሱዓት አድርገው።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel
693 views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 21:01:52 የወንድምህን ችግር ለብቻው ንገረው ጥሩ ነገሩን ግን በሰው ሁሉ ፊት ንገረው
ይሄን ምታደርግ ከሆነ እለት እለት ችግሩን እያፈረስክ ትክክለኛ ማንነቱን ትገነባለ ብዙ ግዜ ብዙ ሰሆች ተሰብረው ሚቀሩት ችግራቸውን በሰው ፊት ስለ ምንነግራቸው ጥሩ ነገራቸውን ስለ ማንነግራቸው ነው ልብ በል ችግርን ተናጋሪ ብቻ አትሁን መልካም ነገር ተናጋሪም ሁን

መልካም ምሽት

@behayluminilu
1.0K views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 23:24:27 አንድ ትንሽ ወንድ ልጅና ሴት ልጅ አብረዉ እየተጫወቱ ነበር። ልጁ ደሳስ የሚሉ ብዮች ነበሩት። ልጅቷ ደግሞ ጣፋጭ ከረሜላዎች ነበሯት።
“የኔን ብዮች ልስጥሽና ያንቺን ከረሜላዎች ስጪኝ” አላት። ልጅቷ በመቀያየሩ ሃሳብ ተስማማች። ልጁ ካሉት ብዮች ውስጥ ትልቅና ቆንጆ የሆነዉን ደብቆ አስቀርቶ ሌሎቹን ሰጣት። ልጅቷ ግን ቃል እንደገባችዉ ያሏትን ሁሉ ከረሜላዎች ሰጠችዉ። ያን ቀን ማታ ልጅቷ ሰላማዊ እንቅልፏን ተኛች። ልጁ ግን “እኔ ደብቄ ቆንጆዉን ብይ እንዳስቀረሁት እሷም የሚጣፍጠዉን ከረሜላ መርጣ አስቀርታ ይሆን እንዴ?” የሚል ሃሳብ ይዞት እንዲሁ ሲገላበጥ አደረ።

••• *×*×*×*×* •••

ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት በቀናነት እና በሃቅ ነገሮችን ካላደረግን ሁሉም እንደራሳችን እየመሰለን ሌሎችን ሁሌ በጥርጣሬ እያየን የህሊና ሰላማችንን እናጣለን። የሌሎችንም ሰዎች ሰላም እንነሳለን። ሰዉ ዞር ባለ ቁጥር ስለነሱ የምናወራ ከሆነ ሰው ተሰብስቦ ባየን ቁጥር “እያሙኝ ይሆን?” ብለን እንብከነከናለን። “ሌባ እናት ልጇን አታምንም” እንደሚባለው መሆኑ ነዉ!

ከ ፌስቡክ መንደር የተወሰደ

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
➥ @womensletlearn
➥ @womensletlearn
1.1K views20:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 07:59:38 በእድል ነዉ ወይስ በአጋጣሚ ነው የምታምኑት?
717 views04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 22:32:29 ከፍቅር
ከጤና
ከሰላም
አንድ ምረጡ ብትባሉ ምን ትላላችሁ??
789 views19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 21:19:55 ዉሸት ምንድ ነዉ?
942 views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 21:35:44 ገንዘብ ሊገዛው አይችልም የምትሉት ነገር አለ? ካለ እስኪ ንገሩኝ?
923 views18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 20:58:30 እንወያይበት እስኪ
Hulet haymanotachew yeteleyayu sewoch befkr hiwot wust abrew bihonu chigru mndnew?

Except "ብርሃን ከጨለማ ጋር ህብረት የለውም"
@womensletlearn
1.4K views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 09:55:06 ከጋብቻ በፊት ከሰው ተደብቆ የሚደረግ ወሲብ ስርቆት ነው።

ይህ አባባል ለዚህ ዘመን ጊዜዉ ያለፈበት ቢመስልም ሀቅ ነውና አይካድም።

በትልቁ ላወራው የፈለኩት ከስርቆቱ ሁኃላ አሻራ ለማጥፋት ስለሚወሰደው እርምጃ ነው።
እጅግ የሚያሳዝን ቅድመ ጋብቻ ወሲብ ከተደረገ ቡኃላ የሚፈጠርን የሰዉ(የህፃን) ህይወት ሳናስበው ነው የተፈጠረው በማለት የስህተት ማስተካከያ ይሆን ዘንድ ለጨካኝ እጆች( ለአስወራጆች/ ለነፍሰ ገዳዮች) ታልፎ ይሰጣል ይገደላል።

ያለበደሉ በግፍ ሲሰቃይ የሲቃይ ድምፁን አስተውሎ የሚሰማለት የለም። ከዛ በቃ ማንም ሰው እንዳያውቅ ችግሩ ተቀርፎዋል ይላሉ "ችግር" ይሉታል አይይ ላልፈለጉት "ችግር" ለእግዚአብሄር ግን የእጁ ስራ ነው። ታዲያ ማታለያዉ ለማነው እግዚአብሄር እንደሆነ አለማት በፊቱ ናቸው። የማያየው ከዐይኑ የተሰወረ ነገር የለም ታዲያ ከማን ነው የሚሸሸው?

ነገሩ ስማችን እንዳይጠፋ የተረገዘው ይጥፋ ነው። ግን ከሰው ፍርድ የእግዚአብሄር ይበልጣል የነፍሱን ዋጋ ከእርሱ ያገኛል። አስተዋይ ግን ወንድሙን እንደገደለው እንደ ቃየል ሳይረፍድበት በደጁ በምታደባ ሃጢያት ላይ (ከጋብቻ በፊት ከሚደረግ ወሲባዊ ግብዣ ላይ) ፈጥኖ ይንገስባታል!!!

ተወዳጆች ሼር አድርጉ

ቻናሉን ይቀላቀሉ
@behayluminilu
@behayluminilu
1.3K views06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ