Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ትንሽ ወንድ ልጅና ሴት ልጅ አብረዉ እየተጫወቱ ነበር። ልጁ ደሳስ የሚሉ ብዮች ነበሩት። ልጅ | Virtuous women💃💃let's learn

አንድ ትንሽ ወንድ ልጅና ሴት ልጅ አብረዉ እየተጫወቱ ነበር። ልጁ ደሳስ የሚሉ ብዮች ነበሩት። ልጅቷ ደግሞ ጣፋጭ ከረሜላዎች ነበሯት።
“የኔን ብዮች ልስጥሽና ያንቺን ከረሜላዎች ስጪኝ” አላት። ልጅቷ በመቀያየሩ ሃሳብ ተስማማች። ልጁ ካሉት ብዮች ውስጥ ትልቅና ቆንጆ የሆነዉን ደብቆ አስቀርቶ ሌሎቹን ሰጣት። ልጅቷ ግን ቃል እንደገባችዉ ያሏትን ሁሉ ከረሜላዎች ሰጠችዉ። ያን ቀን ማታ ልጅቷ ሰላማዊ እንቅልፏን ተኛች። ልጁ ግን “እኔ ደብቄ ቆንጆዉን ብይ እንዳስቀረሁት እሷም የሚጣፍጠዉን ከረሜላ መርጣ አስቀርታ ይሆን እንዴ?” የሚል ሃሳብ ይዞት እንዲሁ ሲገላበጥ አደረ።

••• *×*×*×*×* •••

ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት በቀናነት እና በሃቅ ነገሮችን ካላደረግን ሁሉም እንደራሳችን እየመሰለን ሌሎችን ሁሌ በጥርጣሬ እያየን የህሊና ሰላማችንን እናጣለን። የሌሎችንም ሰዎች ሰላም እንነሳለን። ሰዉ ዞር ባለ ቁጥር ስለነሱ የምናወራ ከሆነ ሰው ተሰብስቦ ባየን ቁጥር “እያሙኝ ይሆን?” ብለን እንብከነከናለን። “ሌባ እናት ልጇን አታምንም” እንደሚባለው መሆኑ ነዉ!

ከ ፌስቡክ መንደር የተወሰደ

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
➥ @womensletlearn
➥ @womensletlearn