Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንዴ ህይወት የማትችለውን እንድትጋፈጥ ታደርግሀለች #ትልቁ__ፈተና ግን ትልቁ | Virtuous women💃💃let's learn

አንዳንዴ ህይወት የማትችለውን እንድትጋፈጥ ታደርግሀለች
#ትልቁ__ፈተና ግን

ትልቁ ፈተና መሞት አይደለም አለመኖር እንጂ!

ትልቁ ፈተና መፀለይ አይደለም አለማመን እንጂ!

ትልቁ ፈተና ማፍቀር አይደለም አለመፅናት እንጂ!

ትልቁ ፈተና መደመር አይደለም አለማካፈል እንጂ!

ትልቁ ፈተና ማጣት አይደለም ተስፋ መቁረጥ እንጂ!

ትልቁ ፈተና ማግባት አይደለም አለመግባባት እንጂ!

ትልቁ ፈተና መደሰት አይደለም ደስታን አለመቆጣጠር እንጂ!

ትልቁ ፈተና ማሰብ አይደለም የሚያስቡትን አለማጤን እንጂ!

ትልቁ ፈተና ችግር አይደለም ትዕግስት ማጣት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ማዘን አይደለም ማማረር እንጂ!

ትልቁ ፈተና ሃይማኖተኛ መሆን አይደለም መንፈሳዊ መሆን እንጂ!

ትልቁ ፈተና ስልጣን አይደለም አጠቃቀሙን አለማወቅ እንጂ!

ትልቁ ፈተና እውቀት አይደለም እያወቁ መሳሳት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ስደት አይደለም የተሰደዱለትን አላማ መርሳት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ወደራስ ማየት አይደለም ዘረኝነት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ስኬታማ መሆን አይደለም ራዕዩን መርሳት እንጂ!

ትልቁ ፈተና የፀለዩትን ማግኘት አይደለም ያገኙትን ማማረር እንጂ!

ትልቁ ፈተና ዝምተኛ መሆን መቻል አይደለም በዝምታ ውስጥ መረጋጋት ማጣት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ቤተክርስትያን ወይም መስጊድ መሄድ አይደለም የሚሄዱበት ምክንያት መዛባት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ገንዘብ አይደለም በገንዘቡ የምናደርግበትን ነገር አለማስተዋል እንጂ!

ትልቁ ፈተና ልጅ መውለድ አይደለም ልጅን መቅረፅ እንጂ!

ትልቁ ፈተና ዜግነት መቀየር አይደለም ማንነትን መርሳት እንጂ!

ትልቁ ፈተና መጣላት አይደለም ለበቀል ማቀድ እንጂ!

ትልቁ ፈተና ይቅርታ ማድረግ አይደለም ይቅርታውን ማመን እንጂ!

ትልቁ ፈተና መለያየት አይደለም እንደሚገናኙ አለማሰብ
እንጂ!

ትልቁ ፈተና ፈጣሪን ማሰብ አይደለም ፈጣሪን ማመን እንጂ!

ትልቁ ፈተና መማታት አይደለም ቅፉ ቃል መናገር እንጂ!

ትልቁ ፈተና ተሰሚነትን መጨመር አይደለም ለሚሰሙን መልካም አርአያ መሆን እንጂ!

ትልቁ ፈተና አብሮ ስራ መጀመር አይደለም አብሮ ስራውን መፈፀም እንጂ!

ትልቁ ፈተና አለማቀድ አይደለም ለማቀድ አለመሻት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ሞክሮ መበላሸት አይደለም ድጋሚ አለመሞከር እንጂ!

ትልቁ ፈተና ጓደኛ ማጣት አይደለም ወዳጅ ማግኘት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ማሸነፍ መቻል አይደለም አሸንፎ መፅናት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ተመስገን ማለት አይደለም አመስግኖ መርካት እንጂ!

ትልቁ ፈተና መደንገጥ አይደለም ግራ መጋባት እንጂ!

ትልቁ ፈተና መሸነፍ አይደለም ተሸንፎ መቅረት እንጂ!

ትልቁ ፈተና እንደ እዮብ መውደቅ አይደለም እንደ እዮብ መፅናት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ከልብ ማልቀስ አይደለም ተሰብሮ መቅረት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ሃገርን መውደድ አይደለም ሃገርን መስበክ እንጂ!

ትልቁ ፈተና ሰው ሆኖ መፈጠር አይደለም ሰው ሆኖ መኖር እንጂ!
ሼርርርር
@womensletlearn