Get Mystery Box with random crypto!

የደም ሚስጥር .... ሰዎች ሳያስቡት የሚያደርጉት ነገር ካለ ደም ሲያዩ መደንገጥና ምንድን ነ | In Christ(በክርስቶስ)

የደም ሚስጥር ....

ሰዎች ሳያስቡት የሚያደርጉት ነገር ካለ ደም ሲያዩ መደንገጥና ምንድን ነው ማለት ነው። በሬ ታርዶ ደም ከፈሰሰ በኋላ ሸፈን ሸፈን ይደረጋል ። በየትኛውም አጋጣሚ ምንም ነገር ፈሶ ስናይ ምንም አይመስለንም። ደም ፈሶ ስናይ ግን ጥያቄ ይፈጥርብናል ፤ ምክንያቱም ደም ያወራል።

በዘመናት መሃከል ብዙ ደሞች ፈሰው ቀርተዋል ፤ ፈሰው ጠፍተዋል። ፈሶ ያልቀረ ፤ ፈሶ ምድር ያልዋጠችው ሕያው ሆኖ ለዘላለም የሚያወራ አንድ ደም አለ እሱም የኢየሱስ ደም ነው።

“የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ፣ እንዲሁም ከአቤል ደም የተሻለ ቃል ወደሚናገረው ወደ ተረጨው ደም ደርሳችኋል።”
— ዕብራውያን 12፥24 (አዲሱ መ.ት)


በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከምናገኛቸው ትልቅ ሚስጥር ኪዳን ሲሆን እግዚአብሔር ኪዳናትን ራሱን ከፍጥረታት ጋር ያስተሳሰረበት ስርዓት ነው። ከዘፍጥረት ጀምሮ እስከ ራእይ ድረስ ባሉ ሀሳቦች ብዙ የኪዳናት ግንኙነት አሉ። ከእነዚህ ኪዳኖች መሃከል አስደናቂ የሆነ ኪዳን የደም ኪዳን ነው።

ደም የሌለበት ኪዳን ፤ ኪዳን ሳይሆን ውል ሲሆን ውል ደግሞ ይፈርሳል። እግዚአብሔርም ለሰው ልጆች በአዲስ ኪዳን ፤ የኪዳናችን መሰረት ያደረገው የኢየሱስን ደም ነው።

#የኢየሱስ_ደም_የአዲስ_ኪዳን_መሰረት_ነው!!

“እንደዚሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ እንዲህ አለ፤ “ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው ደሜ የሚመሠረት አዲስ ኪዳን ነው።”
— ሉቃስ 22፥20 (አዲሱ መ.ት)


የኢየሱስ ደም የእግዚአብሔር የመጨረሻው ሐይል ነው። የእግዚአብሔርን ሐይል ማወቅ የምንፈልግ ከሆነ የደሙን ሐይል ማወቅ አለብን። ሰው የደሙን ሐይል ካላወቀ የእግዚአብሔርን ሐይል ማወቅ አይችልም።

WE MUST KNOW THE POWER OF THE BLOOD, IF WE ARE TO KNOW THE POWER OF GOD.

የእግዚአብሔር ሐይል በእኛ ሕይወት የሚሰራው ከእኛ ጥረት ሳይሆን በኢየሱስ ደም ሐይል ላይ በመመስረት ነው።

መልካም ቀን
ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ


ይ ላ ሉን
@GospelTvEthiopia
@GospelTvEthiopia
@GospelTvEthiopia
@GospelTvEthiopia