Get Mystery Box with random crypto!

The Ethiopian Economist View

የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View
የሰርጥ አድራሻ: @wasealpha
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 20.04K
የሰርጥ መግለጫ

Wase.belay12@gmail.com(0913243956)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-07-01 07:55:24 በየዓመቱ ሀገራት የጠቅላላ ሀገራዊ ምርት መጠን (GDP) እድገትን ሪፖርት ያደርጋሉ! እንዴት ይሰላል? በኢትዮጵያ የGDP አድገት ቁጥር  ክርክር አያጣውም!


በቀላል ለመረዳት የሚከተለውን

በምሳሌ የተቀመጠ ቀመር ተመልከቱ።
5.2K viewsWasyhun Belay, 04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 20:37:40 በየዓመቱ ሀገራት የጠቅላላ ሀገራዊ ምርት መጠን (GDP) እድገትን ሪፖርት ያደርጋሉ! እንዴት ይሰላል? በኢትዮጵያ የGDP አድገት ቁጥር  ክርክር አያጣውም!


በቀላል ለመረዳት የሚከተለውን

በምሳሌ የተቀመጠ ቀመር ተመልከቱ።
5.0K viewsWasyhun Belay, 17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-29 19:32:39 የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጠናቀቂያ ወቅት ማለትም 1944 የዓለማችን 40 ሀገራት 730 ተወካዮቻቸውን በመላክ አሜሪካ ውስጥ የወርቅ ክምችትን እንደ ጠንካራ የዓለም የምንዛሬ ተመን ለመጠቀም ሶስት ሳምንታት የፈጀ ውይይት በማድረግ ስምምነት ላይ ደረሱ ስምምነቱ በአካባቢው ስያሜ Bretton Woods Agreement ይባላል፡፡


የምንዛሬ ተመኑ ዓላማ በፉክክር ምክንያት የሚፈጠር የገንዘብን የመግዛት አቅም የማዳከም አደጋን የመቀነስ እና ጠንካራ የኢኮኖሚ እድገትን የመፍጠር ነበር፡፡ ዋናዎቹ የስምምነቱ ተዋናዮች አሜሪካ፤ ካናዳ፤ የምዕራብ አውሮፓ ሀገራት፤ አውስትራሊያ እና ጃፓንን የያዘ ነበር፡፡


ወርቅን እንደ ጠንካራ የዓለም የምንዛሬ ተመን የመጠቀም ስምምነት ሁለት ጠንካራ የዓለም ተቋማትን ፈጠረ እነሱም ምንዛሬን ለመቆጣጠር እና ገንዘብ ነክ የአስተዳደር ድጋፎችን ለማድረግ የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የልማት ብድር እና ድጋፍ ለማድረግ የዓለም ባንክ (World Bank) ናቸው (ሁለቱ ዓለም አቀፍ ተቋማት እስከ አሁን ድረስ 190 አባል ሃገራትን ይዘው ቀጥለዋል)፡፡


የዚህ ስምምነት የረጅም ዓመታት አጠንጣኞች ታዋቂው እንግሊዛዊው ኢኮኖሚስት ጆን ሜይራንድ ኬይነስ ከአሜሪካዊው ኢኮኖሚስት ሃሪ ዲክሰር ጋር በመሆን ነበር፡፡


የጆን ሜይራንድ ኬይነስ ዓላማ ለዓለም ጠንካራ ማዕከላዊ ባንክ (የታሰበው መጠሪያ Clearing Union ነበር) ለመፍጠር እና ጠንካራ የዓለም መገበያያ ገንዘብ (የታሰበው መጠሪያ Bancor ነበር) ለመፍጠር ነበር፡፡ ነገር ግን አሜሪካዊው ኢኮኖሚስት በወቅቱ ጠንካራ የነበረው የአሜሪካ ዶላር እንዲመረጥ ሃሳብ በማቅረቡ አዲሱ ብር ሳይሳካ ቀረ፡፡


ወርቅን መገበያያ ምንዛሬ አድርጎ የመጠቀሙ ስምምነት በተግባር ከባድ ስለነበር እስከ 1958 በአግባቡ ለመተግበር አልቻለም! ነገር ግን 28 ግራም ወርቅ የ35 ዶላር ዋጋ እዲኖረው ወስነው ሲመነዝሩ ነበር፡፡ አካሄዱ ሌሎች ሃገራት ዶላር ለማግኘት ወርቅ የመሰብሰብ ግዴታ ውስጥ ሲገቡ አሜሪካ በዶላሯ ወርቅ የመሰብሰብ እድል አግኝታ ነበር፡፡


ሁኔታው የተለወጠው በ1971 በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ኒክሰን አሜሪካ ዶላርን በወርቅ መተመን እንደማትፈልግ በመግለጻቸው ወርቅን መገበያያ ምንዛሬ አድርጎ የመጠቀሙ ስምምነት ከተቋቋመ ከ20ዓመታት በኋላ ፈረሰ፡፡ በወቅቱ ሀገራት ጠንካራ ዓለም አቀፍ ገንዘብ ለመፍጠር የነበራቸው ህልም በመክሸፉ በወቅቱ ጠንካራ የነበረውን የአሜሪካ ዶላር እንደ ዓለም አቀፍ መገበያያ ተመን አድርገው መውሰድ ጀመሩ፡፡ እስካሁንም ዶላር ዓለምን ዘዋሪ ሆኖ ዘልቋል፡፡
5.6K viewsWasyhun Belay, 16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 18:34:27 28 ግራም ወርቅ 35 ዶላር የሚመነዘርበት ወቅት! በዓለም ላይ የወርቅ ክምችት እንደምንዛሬ የሚቆጠርበት ጊዜ እና ወርቅ በዶላር የመቀየር ልምምድ| "Bancor" የተባለው ዓለም አቀፍ ገንዘብ በዶላር የመሸነፍ ሚስጥር| ዶላርን የዓለም ዘዋሪ ገንዘብ ያደረገው አጋጣሚ!


ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን

ትንታኔ ይመልከቱ! ለሌሎችም እንዲማሩበት አጋሩት!
5.8K viewsWasyhun Belay, 15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 07:20:12 ኢድ ሙባረክ!

እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አል አድሀ(አረፋ) በዓል አደረሳችሁ!
5.4K viewsWasyhun Belay, 04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 20:41:19 28 ግራም ወርቅ 35 ዶላር የሚመነዘርበት ወቅት! በዓለም ላይ የወርቅ ክምችት እንደምንዛሬ የሚቆጠርበት ጊዜ እና ወርቅ በዶላር የመቀየር ልምምድ| "Bancor" የተባለው ዓለም አቀፍ ገንዘብ በዶላር የመሸነፍ ሚስጥር| ዶላርን የዓለም ዘዋሪ ገንዘብ ያደረገው አጋጣሚ!


ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን

ትንታኔ ይመልከቱ! ለሌሎችም እንዲማሩበት አጋሩት!
5.7K viewsWasyhun Belay, edited  17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-26 19:26:09 የንብረት ታክስ በመንግስት፤ በንብረቱ ባለቤት እና በተከራይ እይታ ሊኖረው የሚችለው ኢኮኖሚያዊ ተቃርኖ! #ለምሳሌ፡- መንደር ውስጥ ገባ ብሎ ያለ አንድ ህንጻ (የመሸጫም ሆነ የኪራይ ዋጋው ገባ ከማለቱ ጋር ቀጥተኛ ይገናኛል!) በህንጻው አጠገብ የአስፓልት መንገድ ቢወጣ ህንጻው መንገድ ዳር በመሆኑ ብቻ Land Value መጨመሩ አይቀርም! (የመሸጫም ሆነ የኪራይ ዋጋው መንገድ ዳር ከመሆኑ ጋር ቀጥተኛ ይገናኛል!)፡፡


ህንጻው መንገድ ዳር በመሆኑ ብቻ የሽያጭም ሆነ የኪራይ ዋጋው ለመጨመሩ የህንጻው ባለቤት ሚና ዜሮ ሲሆን (ግብር ከፋይ ከሆነ የተመጠነ አስተዋጾ ሊኖረው ይችላል!) ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ እና ፕሮጀክቱን ያሰራው መንግስት ብቻ ነው ዋና ሚና የሚኖራቸው!፡፡


የንብረት ታክስ ሰብሳቢው አካል ህንጻውን ከመንገድ ገባ ብሎ በነበረበት ወቅት ከሚያስከፍለው፡ መንገድ ዳር መሆኑን ተከትሎ የደረጃ ለውጥ በማምጣቱ ብቻ ተጨማሪ የክፍያ መጠን ማስቀመጡ አይቀርም (የንብረት ታክስ ህንጻው ያለበትን ቦታ፤ ህንጻው እየሰጠ ያለውን አገልግሎት፤ የህንጻው ይዞታ ስፋት፤ ወዘተ ከግምት ይከታል)፡፡


ጉዳዩ መንግስት ለተለያዩ አገልግሎቶች በሚል በዘረጋው የአስፓልት መንገድ በአካባቢው ያሉ ህንጻዎችን ተፈላጊነት ያሳድጋል! የህንጻው ባለቤቶች ከነሱ ቁጥጥር ውጪ በሆነ ምክንያት ህንጻቸው ዋጋው አድጓል፡፡ መንግስት በሚያለማው መሰረተ ልማት እና የህግ ማሻሻያ ምክንያት በመሬት እና መሬት ነክ ንብረቶች እሴታቸው (Value) ሊጨምር ይችላል!


#ጥያቄው፡- የተሰራው አስፓልት መንገድ እንደ ታክስ መጨመሪያ ምክንያት ወይስ የተሰራው አስፓልት እንደ የቋሚ ንብረቶች ተፈላጊነት ደረጃ ወይም የመሸጫ እና የማከራያ ዋጋ ጭማሪ ይቆጥሩታል የሚለው ነው? (ከመሬት ፖሊሲው ጋር ቆይቶም ቢሆን መዛመዱ አይቀርም)፡፡


መሬት የግለሰብ በሆነባቸው ሃገራት የመንግስት መሰረተ ልማት በአካባቢው ሲሰራ በቋሚ ንብረት ሽያጭ ወቅት በሚኖራቸው የዋጋ ድርድር ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚያገኙ በማሰብ ደስተኛ ይሆናሉ! በሀገራችን የመሰረተ ልማት መኖር የቋሚ ንብረቶችን ዋጋ በተዘዋዋሪ ስለሚጨምር እና የንብረት ታክስን አብሮ መጨመሩ ስለሚጠበቅ መሰረተ ልማቱን በቀጣይ ወቅቶች አንዴት እያዩት የሚሄዱ ይመስላችኋል? (በኢትዮጲያ ለልማት የተፈለገ የግል ይዞታ በባለቤት በኩል ያለው የዋጋ ድርድር አቅም የተገደበ ነው!)፡፡


የመንግስት መከራከሪያ ከግብር ከሰበሰብኩት ገቢ ወጪ አውጥቼ የሰራውት አስፓልት መንገድ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከህንጻው ታገኙ የነበረውን ገቢ በማሳደጉ ልካስ ይገባል አይነት ነው፡፡


ህንጻው ገባ ብሎ በነበረበት ወቅት ተከራይቶ የነበረ የህንጻ ተከራይ ህንጻው በአስፓልቱ መንገድ ምክንያት ዋጋው (Land Value) በመጨመሩ ወደ ንግድ ተቋሙ በርካታ ሸማች ሊመጣ መቻሉን እና በአስፓልቱ መንገዱ ምክንያት የጨመረበትን የቤት ኪራይ ዋጋ እንዴት ያወዳድራል?


በመንግስት መሰረተ ልማት እና የንብረት ባለቤቶች መካከል፤ በንብረት ባለቤቶች እና ተከራዮች መካከል እዲሁም በተከራዮች እና በመጨረሻ ሸማቾች መካከል የመሰረተ ልማት መሰራት የሚፈጥረውን ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ መተላለፍን እንዴት ማስታመም ይቻላል?
6.4K viewsWasyhun Belay, 16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-24 18:09:25 በዋጋ ንረት (Inflation) እና በዋጋ ዝቅጠት (Deflation) መካከል ያለ የአደጋ ልዩነት! የዓለም ልምድ እና የማቃለያ መላዎች!

ዋጋ ንረት (Inflation)፡- በተከታታይ የአገልግሎት እና የቁሳቁስ ዋጋ መጨመር ሲሆን ምክንያቱ የምርት እጥረት እና የፍላጎት መጠን መጨመር ናቸው፡፡

ለምሳሌ በታሪክ ከፍተኛው የዋጋ ንረት…..

ሀንጋሪ፦ 1946 የዋጋ ንረቱ በወር 41.9 ኳድሪሊየን ከመቶ።

ዝምባዋብዌ፦ 2008 የዋጋ ንረቱ በወር 79 ቢሊየን ከመቶ።

ይጎዝላቪያ፦ 1994 የዋጋ ንረቱ በወር 313 ሚሊየን ከመቶ።

ጀርመን፦ 1923 የዋጋ ንረቱ በወር 29ሺ ከመቶ፡፡

ግሪክ፦ 1944 የዋጋ ንረቱ በወር 14ሺ% ከመቶ።

የዋጋ ዝቅጠት (Deflation)፡- በተከታታይ የአገልግሎት እና የቁሳቁስ ዋጋ መቀነስ ወይም ዋጋ ንረት ከዜሮ በታች ሲሆን ማለት ሆኖ ምክንያቱ የምርት መጠን ከፍተኛ መሆን እና የፍላጎት መጠን ማነስ፡፡ በተጨማሪም ከፍተኛ ስራ አጥነት፤ የገንዘብ እጥረት እና የውጪ ምርት ጥገኝነት ሲኖር ነው፡፡

ለምሳሌ በታሪክ ከፍተኛው የዋጋ ዝቅተት…..

እንግሊዝ፡- 1921 (ከዜሮ በታች 10 ከመቶ)፣ 1922 (ከዜሮ በታች 14ከመቶ)፣1930 (ከዜሮ በታች 5 ከመቶ)፤

አሜሪካ፡- 1930-1933 (ከዜሮ በታች 7 ከመቶ)፤

ግሪክ፡- (2013-2015)፤

ኦንግ ኮንግ፡- (1997-2004)፤

ጃፓን፡- (1999-2009)፤

አይርላንድ፡- (1933) 0.1ከመቶ፤

ደቡብ ሱዳን (2022) 12.7ከመቶ (የገንዘብ እጥረት እና የውጪ ምርት ጥገኝነት)

የአንድ ሃገር ኢኮኖሚ ግዴታ ከሆነ ከዋጋ ዝቅጠት ይልቅ የዋጋ መጋሸብን ሊመርጥ ይችላል! ምክንያቱም ለማስታመም ግሽበት የዝቅጠት የተሻለ እድል ስላለው ነው፡፡

እንዴት?

በዋጋ ግሽበት ወቅት አምራቾች በግብዓት እጥረት ሲፈተኑ፤ ሸማቾች በመሸመቻ ዋጋ ይፈተናሉ! ጠቅላላ ኢኮኖሚው በሸመታ መቀዛቀዝ እና በምርት መቀነስ ወደ ፈተና ይገባል! (የሸማች ቁጥር እና መጠን መቀነስን ተከትሎ የምርት መጠን መቀነሱ አይቀርም! ምርት መጠንን በመቀነስ ሰበብ ሰራተኛ መበተን ወይም ግሽበትን ተከትሎ ክፍያን ማሳደግ ተፈጥሮ ዋጋ ንረቱ እንዲደጋገም ሊያደርግ ይችላል!)፡፡

በዋጋ መዝቀጥ ወቅት አምራቾች ያመረቱበትን ወጪ መተካት በመቸገር ሰራተኛ የመበተን ችግር እንዲሁም ሰራተኛ በመበተን ከጠቅላላ ምርት መጠናቸው ሲወርዱ የሃገር ውስጥ ግብር መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡

ሁለቱም ችግሮች ገንዘብን ወደ ገበያ በመልቀቅ ሊፈቱ ቢችሉም ገንዘብን ወደ ገበያ መልቀቅ ጥናት ከሌለው ሁለቱንም ችግሮች ይበልጥ ሊያባብሳቸው ይችላል፡፡



የኢኮኖሚ ግንዛቤዎን ለመጨመር

6.6K viewsWasyhun Belay, 15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-23 20:28:35 በዋጋ ንረት (Inflation) እና በዋጋ ዝቅጠት (Deflation) መካከል ያለ የአደጋ ልዩነት! የዓለም ልምድ እና የማቃለያ መላዎች!


የኢኮኖሚ ግንዛቤዎን ለመጨመር

6.3K viewsWasyhun Belay, 17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-23 13:54:05 የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ታሪክ ለመረመረ ኢትዮጵያ ሶስቱንም የኢኮኖሚ አማራጮች (ከፊል ነፃ ገበያ፤ ኮሚኒስት እና ጣልቃ ገብ አስተዳደር) በተለያየ ጊዚያት ተጠቅማለች አሁንም እያፈራረቀች በመጠቀም ላይ ነች!  ታዲያ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሶስቱም ርዕዮቶች ድህነትን የሚያስተናግደው ለምን ይመስላችኋል?


የርዕዮቱን ልዩነት ትንታኔ ለማየት ለምትፈልጉ

6.6K viewsWasyhun Belay, 10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ