Get Mystery Box with random crypto!

ስለ ፅዮን ዝም አንልም

የቴሌግራም ቻናል አርማ tsiyon1621 — ስለ ፅዮን ዝም አንልም
የቴሌግራም ቻናል አርማ tsiyon1621 — ስለ ፅዮን ዝም አንልም
የሰርጥ አድራሻ: @tsiyon1621
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 448
የሰርጥ መግለጫ

“ደጋግመህ ኃጢአት ብትሠራም ደጋግመህ ንስሐ ግባ፡፡ ቤተክርስቲያን ሐኪም ቤት እንጂ ፍርድ ቤት አይደለችምና፡፡”
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
በዚህ ቻናል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ህግና ስርአት ዶግማ ፣ ቀኖና እና ትውፊትን የጠበቁ መንፈሳዊ ትምህርቶች እና መንፈሳዊ ይዘት ያላቸው የአበው ብሂሎች ይቀርባሉ።
ለአስተያየትዎ @mahberetsiyon_16 /0901255078 ያናግሩን

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-07 06:49:13
63 viewsኢሳይያስ, 03:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 15:26:02
አሁኑኑ በመደወል ቦታ ያስመዝግቡ
ቻናላችንን # join እና # follow መልእክታችንን # share ያድርጉ

"የአባቶቻችን ድል የማትነሳ እምነታቸው
ጥርጥር የሌለባት ሃይማኖታቸው
ህፀጽ የሌለባት ትምህርታቸው
አደፍ ጉድፍ የሌለባት ንጽህናቸው እንዲሁም ፀሎት እና በረከታቸው ከኛ ከህዝበ ክርስቲያኑጋር ጸንታ ለዘለዓለም ትኑር"
አሜን!!!
የቴሌግራም ቻናላችን ከታች ባለው ሊንክን በመስፈንጠር ቤተሰብ ይሁኑን፤ አብረው ያገልግሉ።
https://t.me/tsiyon1621
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
1.1K viewsEsayas Tekle, 12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 15:25:29
901 viewsEsayas Tekle, 12:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 08:05:07 https://www.tiktok.com/@esutekle1988/video/7100782089666039046?_r=1&u_code=dj059c7e67258d&preview_pb=0&language=en&_d=dj059ddhh55477&share_item_id=7100782089666039046&source=h5_m×tamp=1653282284&user_id=6969074877991191558&sec_user_id=MS4wLjABAAAAkIS1ABVS-DOW2G3s-KRLalLYCBM-4hOwukLsqdkcgihXQxVmvDodv3kLpcD2VlEc&utm_source=more&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7100777323516151558&share_link_id=058681bb-7970-4a0f-acfb-fdc7db8d38dd&share_app_id=1233&ugbiz_name=Main
244 viewsኢሳይያስ, 05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 06:49:08 ሚያዝያ 15/2014 ዓ.ም


ቅዳሜ፡–ቀዳም ሥዑር ይባላል፡፡ በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡

የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር  ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡

 

ለምለም ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡

በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡  

የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡

ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡

ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡፡ ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡

ቻናላችንን # join እና # follow መልእክታችንን # share ያድርጉ

"የአባቶቻችን ድል የማትነሳ እምነታቸው
ጥርጥር የሌለባት ሃይማኖታቸው
ህፀጽ የሌለባት ትምህርታቸው
አደፍ ጉድፍ የሌለባት ንጽህናቸው እንዲሁም ፀሎት እና በረከታቸው ከኛ ከህዝበ ክርስቲያኑጋር ጸንታ ለዘለዓለም ትኑር"
አሜን!!!
የቴሌግራም ቻናላችን ከታች ባለው ሊንክን በመስፈንጠር ቤተሰብ ይሁኑን፤ አብረው ያገልግሉ።
https://t.me/tsiyon1621
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
1.4K viewsኢሳይያስ, edited  03:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 10:21:50 አቤት የዛሬ ቀን አቤት ይችህ ዕለት
ዕለተ አርብ በዓለ ስቅለት

ጌታችን አማላካችን ሐሙስ ማታ 3 ሰዓት በይሁዳ አመልካችነት ስሞ አሳልፎ ሰጠው
ጠዋት 12 ሰዓት የዓለም ቤዛ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክረስቶስ ጲላጦስ ፊት የቆመበት ሰዓት ጲላጦስ በጥያቄ ጌታችን ይጠይቀው ነበር ጌታ ግን ከዝምታ ውጭ ምን አልመለሰም " ወዲያውም ማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎችና ከጻፎች ከሸንጎውም ሁሉ ጋር ከተማከሩ በኋላ፥ ኢየሱስን አሳስረው ወሰዱትና ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት።"
(የማርቆስ ወንጌል 15:1)
ጠዋት ሶስት ሰዓት ጌታችን ጲላጦስ ገረፈው በሰሰለት አስሮ ገረፈው ለአይሁድ አሳልፎ ሰጠው እኔ ከእርሱ ምንም በደል አላገኘሁበትም ዕያለ አሳልፎ ሰጠው አይሁድ እየተሳለቁ 6666ግራፋት ገረፉት ምራቅ ተፉበት በጥፊ ማን መታህ በዱላ መን ገጨኸ እያሉ ተዘባበቱበት
" ራሱንም በመቃ መቱት ተፉበትም፥ ተንበርክከውም ሰገዱለት።"
(የማርቆስ ወንጌል 15:19)

ቀን 6 ሰዓት የዓለም ጌታ በወንጀለኛ መቅጫ ጎለጎታ /የራስ ቅል በተባለ ስፍራ በመስቀል ሰቀሉት ሳዱር አላዶር ዳናት አዴራ ሮዳስ በተባሉ ቀነዋተ መስቀል ቸነከሩት የሾክ አክሊል ደፉበት
" ቀይ ልብስም አለበሱት፥ የእሾህ አክሊልም ጎንጉነው ደፉበት፤"
(የማርቆስ ወንጌል 15:17)

ቀን 9 ሰዓት ጌታችን ነፍሱ ከሥጋው በገዛ ስልጣኑ እና ፍቃዱ የለየበት ሰዓት ነው ሰባቱ የመስቀሉ ቃለት የተናገረበት
" ከስድስት ሰዓትም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 27:45)
ጌታችን በተአምራቱ !እያዩ እንኳን ልባቸው ሊመለስ አልቻለም

(የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 27)
----------
50፤ ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።

51፤ እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤

52፤ መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤
አንድም ሁለቱ አብረውት የተሰቀሉ የነበሩት ጥጦስና ዳርክስ ወይም
ፊያታዊ ዜማ እና ፊያታዊ ዘፀጋ እየተነጋገሩ ሳለ ጥጦስ እኛስ በወንጀላችን ነው የተሰቀልነው እርሱ ግን ምን አላደረገም አለ ዳርክስም አምላክ ከሆነ እራስህን አድን አለ ፊያታዊ ዜማ ግን አቤቱ በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለ ጌታም ሲመልስለት

(የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 23)
----------
41፤ ስለ አደረግነውም የሚገባንን እንቀበላለንና በእኛስ እውነተኛ ፍርድ ነው፤ ይህ ግን ምንም ክፋት አላደረገም ብሎ ገሠጸው።

42፤ ኢየሱስንም። ጌታ ሆይ፥ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው።

43፤ ኢየሱስም። እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው።

ሰርክ 11 ሰዓት ጌታችን በአዲስ መቃብር ኒቆዲሞስና አርማታዊ ዮሴፍ ገንዘው ቀበሩት

ቅዳሜ ለሊት 6 ሰዓት ሞትን በሞቱ ሽሮ የተነሳበት ሰዓት
" እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 53:5)
እንበለ ደዊ ወሕማም እንበለ ጻዕማ ወድካም ያብጽሀኒ ያብጽያክሙ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሠላም
ሰሙነ ሕማማቱ በሠላም አስፈፅሞ ለብርሃን ትንሳኤው ያድርሰን የትንሳኤው ብርሃን ያሳየን

https://t.me/tsiyon1621
3.0K viewsኢሳይያስ, 07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 20:07:59 https://t.me/tsiyon1621
236 viewsኢሳይያስ, 17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-27 16:46:59 † ቤተክርስቲያናንን ከዘመኑ ፈተና ለመታደግ የራሻ ኦርቶዶክስን መንገድ እንከተል።†


ሩሲያ እንዴት ኦርቶዶክሳዊና ኃያል ሃገር ሆነች?

ሩሲያ አሁን ላለችበት የሃይማኖትና የሥልጣኔ ደረጃ ያደረሳት በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት በአሁኗ ሩሲያ የነበረው መንግስታዊ አስተዳደር(ፖለቲካ) ይከተል የነበረው ሶሻሊስት ርዕዮተ ዓለም ፀረ ቤተክርስቲያን ፀረ ኦርቶዶክስ ነበር። በእዚህ የተነሳ በሃገሪቱ የነበሩ አብያተ ክርስቲያናት ገዳማት ተዘጉ ምዕመናን ሃይማኖታቸውን ዘነጉ ወደ ኢአማኒነት ተለወጡ። በእዚህ ሰዓት ሩሲያ አሁን ያለችበትን ደረጃ ሊያደርስ የሚችል ስብሰባ በሰንበት ት/ት ቤት ወጣቶች ተካሄደ።
❆የስብሰባው ተሳታፊዎች:-
የአሁኑ የሩሲያ ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ክሪል እና የአሁኑ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ሌሎችም የሰ/ት ት/ቤት ወጣቶች ነበሩ።
❋የስብሰባው አጀንዳ:-
"አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት እየተዘጉ ነው፣ ምዕመናን ሃይማኖታቸውን እየዘነጉ ነው ምን እናድርግ?" ነበር።
❆የተነሱ ሃሳቦች:-
በመጨረሻም ሁለት መሠረታዊ ሃሳቦች በስብሰባው ተሳታፊዎች መካከል በሁለት ቡድን ተከፍለው ሰፊ ክርክርና ውይይት ተደረገ።
☞የመጀመሪያው: "ለምን ወደ ገዳም ገብተን ቄስ መምህር መነኩሴ ቆሞስ ጳጳስ ሁነን ምዕመናን አናስተምርም አብያተ ክርስቲያናትን ገዳማትን አንከፍትም" ሲሆን
☞ሁለተኛው: "በዓለማዊ ትምህርት ተምረን በፖለቲካ ተሳትፈን የመንግስትን የሥልጣን ቦታ በመያዝ ጠንካራ መንግስት መመስረት አለብን" የሚሉ ነበሩ።
➻የስብሰባው ውሳኔ:-
በሁለቱም ቡድን የቀረበው ሃሳብ እንተግብር የእነ አቡነ ክሪል ቡድን ወደ ገዳም እንሂድ የነ ቭላድሚር ፑቲን ቡድን ወደ ፓለቲካው ገብተን እንሳተፍ በሚል ተወሰነ።
➻በመጨረሻም:-
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ክሪል የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ በመሆን ቤተክህነቱን ሲይዙ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያ ፕሬዝዳንት ሆነው ተገናኙ።
ሩሲያ በአሁኑ ሰዓት ከመላው ህዝቧ ውስጥ 99% የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነው።
ሩሲያ በአሁኑ ሰዓት በዓለም ላይ ካሉ ሰባት ሃያላን ሃገራት አንዷ ናት።

ሼር ያድርጉ

https://t.me/tsiyon1621
2.3K viewsEisu Tekle, 13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-27 16:46:54
2.1K viewsEisu Tekle, 13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-26 21:23:00 † ምን ብዬ ልጥራችሁ? †
በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

… ከሌሎች ከማያምኑት ብልጫ ኖሯችሁ እንዳየው በምፈልገው ሕይወት፥ በኹሉም ረገድ ተቃራኒ ኾናችሁ አያችኋለሁ፡፡ ለምሳሌ ከቦታ አንጻር፥ ቀኑን ኹሉ የፈረስ እሽቅድምድምንና ተውኔትን፣ ነውርን የተሞሉ ትርኢቶችንና የክፉዎችን ማኅበር፣ ርኵሰትንም የተሞሉ ሰዎችን ስትመለከቱ እንደምትውሉ አያችኋለሁ፡፡ ከፊታችሁ አንጻር፥ ዘወትር ያለ ልክና እንደ አመንዝራ ሴት ስትስቁ እመለከታችኋለሁ፡፡ ከአለባበሳችሁ አንጻር፥ ከተዋንያንና ጠቢባን ነን ከሚሉ ሰዎች ምንም እንደማትለዩ አስተውላችኋለሁ፡፡ ከሚከተሉአችሁ ሰዎች አንጻር፥ ብዙ ውዳሴ ከንቱን እንደምትሹ አያችኋለሁ፡፡ ከንግግራችሁ አንጻር፥ ምንም ደኅና ነገር፣ በቁዔት ያለው ቃል፣ ለሕይወታችን የሚረባ ንግግር እንደሌለባችሁ እገነዘባለሁ፡፡ ከማዕዳችሁ አንጻርም ከዚያ ጽኑዕ የኾነ ወቀሳ የሚያመጣባችሁ እንደ ኾነ አያለሁ፡፡

ታዲያ እስኪ ንገሩኝ! ክርስቲያንን ክርስቲያን ከሚያስብሉት ነገሮች እጅግ የራቃችሁ ኾናችሁ እያለ፥ ክርስቲያኖች መኾናችሁን መለየት የምችለው በምንድን ነው? ክርስቲያኖች መባላችሁስ ይቅርና፥ ሰዎች ብዬ ልጠራችሁ የምችለው እንዴት ነው? ምክንያቱም እንደ አህያ ትራገጣላችሁ፡፡ እንደ ኮርማ ትሴስናላችሁ፡፡ እንደ ፈረስ ከሴቶች ኋላ ኾናችሁ ታሽካካላችሁ፡፡ እንደ ድብ ሆዳሞች ናችሁ፡፡ ሥጋችሁን እንደ በቅሎ ሥጋ ትሰገስጋላችሁ፡፡ እንደ ግመልም ቂም ትይዛላችሁ፡፡ እንደ ተኵላ ትነጥቃላችሁ፡፡ እንደ እባብ ትቈጣላችሁ፡፡ እንደ ጊንጥ ትናደፋላችሁ፡፡ እንደ ቀበሮ ተንኰለኞች ናችሁ፡፡ እንደ እባብ ወይም እንደ እፉኝት በጕረሮአችሁ መርዝ አለ፡፡ እንደ ክፉ ጋኔን ከወንድማችሁ ጋር ትጣላላችሁ፡፡ ታዲያ ክርስቲያኖች የሚለውስ ይቅርና፥ በምናችሁ ሰዎች ብዬ ልጥራችሁ? ሰው የሚያስብል ምልክት ሳይኖራችሁ እንዴት ብዬ ከሰው ዘንድ ልቊጠራችሁ? የንኡሰ ክርስቲያኖችና የክርስቲያኖች ልዩነት ባሰብኩ ጊዜ ልዩነቱ የሰውና የበረኻ አውሬ ያህል ይኾንብኛል፡፡ ታዲያ ምን ብዬ ልጥራችሁ? የበረኻ አውሬ ብዬ ልጥራችሁን? እንዲህስ አልላችሁም፤ የበረኻ አውሬዎች እንደዚያ የኾኑት ከተፈጥሮአቸው የተነሣ እንጂ እንደ እናንተ ወደውና ፈቅደው አይደለምና፡፡ ታዲያ ምን ብዬ ልጥራችሁ? አጋንንት ልበላችሁን? እንዲህስ አልላችሁም፤ አጋንንት የሆድ ባሪያዎች አይደሉምና፤ ፍቅረ ንዋይም የለባቸውምና፡፡ ታዲያ ከበረኻ አውሬዎችም ከአጋንንትም የሚብስ ክፉ ግብር ከያዛችሁ፥ ንገሩኝ - ሰዎች ብዬ እጠራችሁ ዘንድ ይገባኛልን? ሰዎች ለመባል እንኳን የሚበቃ ምግባር ከሌላችሁስ፥ ክርስቲያኖች ብዬ ልጠራችሁ የምችለው እንዴት ነው?

ቻናላችንን # join እና # follow መልእክታችንን # share ያድርጉ

"የአባቶቻችን ድል የማትነሳ እምነታቸው
ጥርጥር የሌለባት ሃይማኖታቸው
ህፀጽ የሌለባት ትምህርታቸው
አደፍ ጉድፍ የሌለባት ንጽህናቸው እንዲሁም ፀሎት እና በረከታቸው ከኛ ከህዝበ ክርስቲያኑጋር ጸንታ ለዘለዓለም ትኑር"
አሜን!!!
የቴሌግራም ቻናላችን ከታች ባለው ሊንክን በመስፈንጠር ቤተሰብ ይሁኑን፤ አብረው ያገልግሉ።
https://t.me/tsiyon1621
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
3.4K viewsሱላማጢስ ፩, 18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ