ሰላም ዋላችሁ? ብዙዎቻቹ እንደጠየቃችሁኝ የዛሬው ቅዳሴ ይለያል ወይ ላላችሁት ምነው ተለየብኝ ላላችሁት ለመመለስ መጥቻለሁ መልካም ቆይታ። የዛሬው ቅዳሴ ተለይቶ ሳይሆን በቤተክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሁላችሁም እንደምታውቁት 14 የቅዳሴ አይነት አለ ። ሁሉም አንድ ሆነው ልዩነትም አላቸው ። ለምሳሌ ቅዳሴ ሐዋርያት ሐዋርያትን የሚነካ ቅዳሴ ማርያም ደሞ ማርያምን የሚገልፅ ቅዳሴ እግዚእ ደሞ የጌታ ቅዳሴ ነው። እናም ዛሬ መጋቢት 10 በዓል ስለሆነ መስቀልን የሚነካ መሆን አለበት ። ስለዚህ ስለ መስቀል በብዛት የተረከው ወይም የደረሰው በቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ ነው ስለዚህ ። የዮሐንስ አፈወርቅን ቅዳሴ ዛሬ ይቀደሳል ማለት ነው። እንጂ ሌላ የተጨመረ ወይም የተቀነሰ አዲስ ነገር የለም። 2 ተኛ ጥያቄያቹ ደሞ የ የ የ ይላሉ ምን ማለት ነው በቅዳሴው ላይ ብላቹህኛል። ተሳስታቹሀል የ ሳይሆን ዬ ነው የሚሉት ትርጉሙም ወየው (ወይኔ) እንደማለት ነው። 3 ተኛ ጥያቄያቹ ደሞ ሠራዊቱስ የለያል ወይ ? አዎ ይለያል የዮሐንስ አፈወርቅ ሰራዊት አለ እሱ ነው የሚባለው። ስለጠየቃችሁኝ አመሠግናለሁ ዲ/ን ፍቅረ አብ መለስኩላቹ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል ውስጥ ሌላም ጥያቄ ካላቹ በዚህ ጠይቁን @serate_bte_krstian @serate_bte_krstian @serate_bte_krstian 1.7K views10:36