Get Mystery Box with random crypto!

10 ዋና ዋና የእንቁላል ጥቅሞች እንቁላል ለሰው ልጅ በጣም ተስማሚ ከሆኑ የምግብ አይነቶች ውስ | 🇹 🇴 🇲 t҈ u҈ b҈ e҈ 

10 ዋና ዋና የእንቁላል ጥቅሞች

እንቁላል ለሰው ልጅ በጣም ተስማሚ ከሆኑ የምግብ አይነቶች ውስጥ ዋነኛዉ ነው ። ሰዎች በቀን 3 እንቁላል እንዲመገቡ ይመከራል። እንቁላል ለአዘገጃጀት ቀላልና ከማንኛውም ምግብ ጋር አብሮ ሊዘጋጅ የሚችል ነው ። በጣእሙም ከማንኛውም ምግብ ጋር ሊወዳደር የሚችል ነው ።

እንቁላል ለሰው ልጅ ብዙ ጥቅም አለው። 10 የእንቁላል ዋና ዋና ጥቅሞች እንደሚከተለው ቀርበዋል ።

ለወዳጅዎ ያጋሩ። እንቁላልን አዘውትረው ይመገቡ ።

1.እንቁላል የአልሚ ምግብ ምንጭ ነው

እንቁላል የሰው ልጅ የሚያስፈልገውን አልሚ ምግብ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ይዟል።

2.እንቁላል ጤናማ የኮሌስትሮል ምንጭ ነው

እንቁላል በውስጡ የበዛ ኮሌስትሮል የያዘ ቢሆንም በደም ውስጥ የሚኖረውን የኮሌስትሮል መጠን ለአብዛኛው ሰው አይጨምርም።

3.እንቁላል የልብ ህመምንና ስትሮክን ይከላከላል

HDL(High Density Lipo Protein) የተባለውን የኮሌስትሮል መጠን በመጨመር ሰዎችን ከልብ በሽታ ይከላከላል ። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት 2 እንቁላል በየቀኑ ለ6 ሳምንታት መጠቀም የHDL መጠንን በ10% ይጨምራል ።

4. እንቁላል የኮሊን(Choline)ንጥረ ምግብ ምንጭ ነው

ኮሊን የሴል ሜምብሬን ለመስራት የሚያገለግል ንጥረ ነገር ነው።

ኮሊን ከቪ ቫይታሚን ምንጭ ውስጥ ይመደባል።ከእንቁላል ውጭ በሌሎች የምግብ አይነቶች ውስጥ በብዛት አይገኝም።

5.እንቁላል የአይን ህመምን ይከላከላል

እንቁላል Lutein እና Zeaxanthin የተባሉ ንጥረ ነገሮችን ይዟል ። በተለይም የእንቁላል አስኳል በሁለቱ ንጥረ ነገሮች የበለፀገ ነው። ለእንቁላልን መጠቀም ከአይን ህመም እራሳችንን ለመጠበቅ ያግዘናል ።

6.እንቁላል የቫይታሚን ኤ ምንጭ ነው

በአለም ላይ ለአይነ መታወር ከሚዳርጉ ዋነኛ ምክንያቶች አንዱ የቫይታሚን ኤ እጥረት ነው ። እንቁላል በበቂ መጠን የቫይታሚን ኤ ምንጭ ነው ።

7.እንቁላል የኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ ምንጭ ነው

ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ በደም ውስጥ የሚገኝ Triglyrcerides የተባለ ንጥረነገር በመቀነስ የልብ ህመምን ይከላከላል ።

8. እንቁላል የፕሮቲን ምንጭ ነው

የሰው ልጅ የተሰራው ገንቢ ምግብ (ፕሮቲን ) ከተባለ ነገር ነው ። እንቁላል በውስጡ ለሰው ልጅ አስፈላጊ የተባሉትን አሚኖ አሲድ በሙሉ የያዘ ነው ። ፕሮቲን የሰውን ሴልና ቲሹን ለመስራት ይጠቅማል።

9.እንቁላል ክብደት ለመቀነስ ይጠቅማል

እንቁላል በትንሹ በመመገብ ከሚያጠግቡን ምግቦች መካከል አንዱ ነው። ይህም ክብደት ለመቀነስ ይጠቁማል።

10.እንቁላል የአጥንትንና ፀጉርን ጤና ለመጠበቅ ይጠቀማል


ለወዳጅዎ ያጋሩ። እንቁላልን አዘውትረው ይመገቡ ምንጭ- healthline

@tom_abe