Get Mystery Box with random crypto!

ትዕግስተኛ ሰው ውሃን በወንፊት መያዝ ይችላል ፡፡ ዋናው ነገር ውሃው ወደ በረዶ እሲኪቀየር መታገሱ | 🇹 🇴 🇲 t҈ u҈ b҈ e҈ 

ትዕግስተኛ ሰው ውሃን በወንፊት መያዝ ይችላል ፡፡ ዋናው ነገር ውሃው ወደ በረዶ እሲኪቀየር መታገሱ ላይ ነው ፡፡

አንተም ህይወቴ አሁን ተቦክቶ ፤ አሁን ኩፍ ብሎ ፤ አሁን ተጋግር ፤ አሁን ካልቆረስኩት ሙቼ እገኛለው አትበል ፡፡ ሁሉም ነገር የሂደትና የትዕግስት (የመጠበቅ) ጉዳይ ነው ፡፡

ከእንቁላል ጫጬት እንደሚገኝ የታወቀ ነው ፡፡ ነገር ግን ጫጬቱ እንቁላሉን ሰብሮ ሳይወጣ ተቻኩለክ አንተ ብትሰብረው የምታገኘው ሁለት እግር ያለው ጫጬት ሳይሆን ፈሰሽ አስኳልን ነው ፡፡

የአብዛኞቻችን ችግር ምን እንደሆነ ታውቃለክ ወዳጄ ? መጠበቅ ሚባል ነገር አንወድም! አዎ ትዕግስት ብሎ ነገር አልፈጠረብንም ፡፡ ለማንኛውም መልካምና ታጋሽ ሁናችሁ ዋሉ ፡፡ የረጋ ወተት ቅቤ ይወጠዋል ይላሉ አበው ሲተርቱ እኔም ቀበል አድርጌ ረጋ እንበል እላለሁ ፡፡

በመረጋጋት ውስጥ ልምድ መውሰድ ፣ በመረጋጋት ውስጥ ያሉንን አማራጮች ማየት ፣ በመረጋጋት ውስጥ መብሰል አለና እንረጋጋ እላለሁ ፡፡

@tom_be