Get Mystery Box with random crypto!

ስለ NIKE ጫማ ማወቅ ያለብን ነገሮች Nike በአለማችን ተወዳጅ የሆነው Brand ጫማ ስያ | አዳዲስ ወቅታዊ ድብቅ ነገሮች 🌍🌍

ስለ NIKE ጫማ ማወቅ ያለብን ነገሮች

Nike በአለማችን ተወዳጅ የሆነው Brand ጫማ ስያሜውን ያገኘው ከጥንት የግሪክ አማልክት የ Pallas(Titan) እና የStyx ልጅ ከሆነችው Nike ነው ! Styx መሬትንና የሲዖልን መግቢያ የሚከፍል ወንዝ ነው ብለው ግሪኮች ያምኑ ነበር ! Nike የጥንታዊ ግሪኮች ጣዖት የነበረች ሲሆን የፍጥነት የጥንካሬና የድል አምላክ ብለው ያመልኳት ነበር ! መመለኳም አሁን ድረስ ቀጥሏል !

Nike በ Zeus(የጥንት ግሪክ ዋና አምላክ) የፍጥነት የጥንካሬና የድል አምላክ ለዘላለም እንደሆነች ቃል ስለተገባላት አምላክነቷ አሁንም ድረስ ቀጥሎ በእሷ ስም የተሰየሙት ምርቶች የሚከተሉት ናቸው !

1.Honda motor cycles የ Nike'ን ምልክት እንደ አርማ/logo ይጠቀማል !

2.በአሜሪካ anti aircraft missile system የ nike'ን ምልክት ይጠቀማል !

3.በዋነኛነት የ nike ጫማ አምራች የ nike'ን ምልክት ይጠቀማል !

ስለዚህ አብዛኞቻችን የምንጠቀመው Nike ጫማ ሰይጣንን የሚወክል ስለሆነ ልንጠነቀቅ ይገባል ! ብዙ ሰወች "ካላመለኩት ምን ችግር አለው" ይሉ ይሆናል ነገር ግን እኛ የእግዚአብሔር ተከታዮች እንጂ የሰይጣን አደለንም ! ሰይጣን አምላኪዎቹ ኢሉሚናቲዎች ብዙ በጀት መድበው ይህንን ሁሉ የሚከውኑት የሚያመልኩትን ሰይጣን ከፍ ከፍ ለማረግና የዓለም ህዝብን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሱ አቀንቃኝ ለማረግ ነው !

አሁን አሁን ላይ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ጊዜው ከባድና በፈተናዎች የተሞላ ነው ! እያንዳንዷን እርምጃችን ቆም ብለን ማሰብ ይገባናል ! ምክንያቱም እኛ ግሎባላይዜሽን በሚባል በዘመናዊ ባርነት የታጠርን ሰወች አብዛኛው እንቅስቃሴያችን በእኛ ሳይሆን የሰይጣን ጭፍራ በሆኑ ሀገሮች የተወሰነ ስለሆነ ነው ! የሚሰጡንን ቀጥታ እንቀበላለን ለምን ብለን አንጠይቅም ! የእነሱን እንቀበላለን የእኛን እንንቃለን የእነሱ የሆነው ሁሉ ይጥመናል ! ነገር ግን ምን ያህል ስለምንከተላቸው ሰወች ፣ ስለ አለባበሳቸው ፣ ስለምንመገበው ምግብ ፣ ስለምንጠቀመው ቴክኖሎጂ እናውቃለን?

አሁንም ለመንቃትና ለማስተዋል ጊዜው አረፈደም !

@Tofunjoinit