Get Mystery Box with random crypto!

• ​𝙪𝙛𝙤 || Part - 2 ዶክተር ጄ አለን ሀይኒክ የተባሉ የ UFO ተመራማሪ እንደሚሉት | አዳዲስ ወቅታዊ ድብቅ ነገሮች 🌍🌍

• ​𝙪𝙛𝙤 || Part - 2

ዶክተር ጄ አለን ሀይኒክ የተባሉ የ UFO ተመራማሪ እንደሚሉት " UFO አየን የሚሉ የብዙ ሰዎች የአእምሮ ብስለት መሃከለኛ የጥቂቶች ደግሞ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው ! እነዚህ አካላት በተለያየ የጥራት መጠን ፈቶ ተነስተዋል ! ከአውሮፕላኖች ጎን ሲበሩ መታየታቸውም ተወስቷል ! በርካታ የምርምር ዘገባዎች እነዚህን ነገሮች ከብዙ ሁነታዎች ጋር አያይዘዋቸዋል ! ለምሳሌ ከጨረቃ ፣ ተወርዋሪ ኮከብ ፣ ፊኛዎች ፣ ብሩህ መብራቶች ፣ የሰሜን ብርሃኖች ፣ የእሳት ኳሶችና የመሳሰሉት ሊሆኑ ይችላሉ እሚል ግምት አለ ! ሌሎች በርካታ መላምቶች ቢኖሩም ሁሉንም የሚያስማማ መላ ምት አለ ማለት ግን አዳጋች ነው ! በምድር ላይ ያሉ ሃያላን መንግስታት የሰሯቸው የሚስጥር መሳሪያዎች ሊሆኑ ይችላሉ የሚለው መላ ምት ግን በሁሉም ዘንድ ተቀባይነትን አጥቷል !

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት እነዚህ ከተዋጊ አውሮፕላኖች አካባቢ ያንዣብቡ የነበሩ ብርሃናማ አካላት ተፋላሚ ወገኖች አንዱ የሌላውን ሚስጥር መሳሪያዎች ናቸው የሚል ጥርጣሬ ነበራቸው ! ግን እነኚህ UFO የሚስጥር መሳሪያዎች ቢሆኑ ኖሮ ሁኔታው በመገናኛ መሳሪያዎችና በመሳሰሉት መጋለጡ አይቀርም ነበር ! የአሜሪካ አየር ሃይል "UFO ማብራሪያ ሊገግኝላቸው አይችልም ! ስለዚህም የሉም" እሚል አቋም አለው ! የሚገርመው ግን የአየር ሀይሉ የውስጥ ህግ አንዱ ክፍል አውሮፕላን አብራሪዎች UFO ቢገጥማቸው መውሰድ የሚገባቸውን እርምጃዎች ይጠቅሳል !

ክፍል 3 ይቀጥላል ........

@Tofunjoinit