Get Mystery Box with random crypto!

*ሀገሬ የት ገባሽ ኧረ ምኑ ዋጠሽ ለምንስ እድህ ሆንሽ ''' ኦሮሞ ጉራጌ ሙስሊም ክርስቲያኑ | ፍቅርና ተስፋ

*ሀገሬ የት ገባሽ
ኧረ ምኑ ዋጠሽ
ለምንስ እድህ ሆንሽ '''

ኦሮሞ ጉራጌ ሙስሊም ክርስቲያኑ
አማራ ሶማሌ ህዝብ ና ዙፋኑ
የተከባበሩ በፍቅር የኖሩ
ሌላው መፍትሄ እጂ ያልሆነ ችግሩ
ሸሆች ሲናገሩ ቃላቸው ሲጣፍጥ
ቄሶች ሲጸብሉ ያለዘር ያለጎጥ
ኦሮሞው ሲያገባት ያማራን ውብ ቆንጆ
አፋር ከሶማሌ ሲመሰርት ጎጆ
ለሙስሊም በኣላት የሚጠራሩበት
የተቃለዱ የሚያሳልፍበት

በጣም የሚከበር የሚፈራ መቅደስ
አብሮ የሚበላ ተካፍሎ የሚቆርስ
ፈጣሪ ሳያዘው ማንንም ሳናጣ
ሀዘንታ ነበረን አስክሬን ሲመጣ
እንባችን አይደርቅም ከልብ ሲወጣ
ያኔ ድሮ ዶሮ እደዚህ ነበርን
..........ተከባብረን የኖርን
ሀገሬ የት ገባሽ
ኧረ ምኑ ዋጠሽ
ለምንስ እድህ ሆንሽ
አንድ ሰው ስናጣ ታሪክ የሚያስጠናን
ያኔ እዛጋ ቀረን ዛሬ ላይ እድህ ሆን

ዛሬ ተለውጠን በተቃርኖ ሁነን
ሠርቀን የምናድር ኑሮን የምለምን
ቆሶችን ሳንፈራ ሰይጣንን ያነገስን
በየወዛወዙ ሸህን የቀበርን
አምላክን ሳንፈራ ሰይጣን የምናምን
ሰውን አርደን የጣልን
.... አዘኔታን ያጣን
ከሰውነት ወርደን ስጋን እየበላን
ምንም የማያውቅን ህጻን ያቃጠልን።

ሰው ሜዳ ወርቆ ኪሱን የምዳብስ
እናት ልጇን አታ በመንታ ስታለቅስ
አሞራ አስበላነው አምላክ የሰራውን
ፈጣሪስ አስችሎት እደትስ አቆመን ።


ሀገሪቷ ጠባንን ድበር ስንገፋ
ዙሪያችንን ከቦት ደም እየተስፋፋ
ሁሉም እየሞተ ሁሉም ዘሩ ጠፋ።

#ሀሰን አለባቸው (hashuya)

መልካም በኣል