Get Mystery Box with random crypto!

​​ መልካሙ ዶክተር ክፍል ሁለት ምግቡን ጨርሼ እማማ አመሰግናለሁ ብዬ ልሄድ ስል.. ልጄ | ፍቅርና ተስፋ

​​ መልካሙ ዶክተር

ክፍል ሁለት


ምግቡን ጨርሼ እማማ አመሰግናለሁ ብዬ ልሄድ ስል.. ልጄ የበሉበትን እቃ ማጠብ የጨዋ ሰው ተግባር ነው እቃውን ብታጥቢ ደስ ይለኛል አሉ እማማ ኧረ ችግር የለም እርስዎ ምግብ ሰጥተውኝ እኔ እቃ ማጠብ እንዴት ያቅተኛል እንደውም ቤት ውስጥ ያሉትን በሙሉ አምጡ አልኳቸው ተባረኪ ልጄ ብለው ትንሽ እቃ አምጥተው ሰጡኝ እኔም እቃውን ማጠብ ጀመርኩኝ...
እቃውን ጨርሼ ልሄድ ስል ልጄ አሁን ፀሐዩ በጣም ከባድ ነው ፀሐይ ትንሽ በረድ እስኪል ቁጭ ብለሽ ቴሌቭዥን መመልከት ትችያለሽ አሉኝ የዚህች መልካም እናት ሁኔታ ትንሽ ቢገርመኝም ቁጭ ብዬ ቴሌቭዥን ማየት ጀመርኩኝ በዚህ መሃል ከተቀመጡበት ተነስተው ቡና ማፍላት ጀመሩ...
ይህ ሁሉ ክብር ለኔ? ምን የሚሉት ነገር ነው? ቡናው ተፈልቶ ደረሰ በዚህ ሁሉ ሰዓታት ተጫወቺ ከማለት ውጭ ምንም ጥያቄ እየጠየቁኝ አይደለም እኔ ደግሞ ጥያቄ የማይጠይቅ ሰው ስወድ! በቃ ቤተሰብ ቤት ምናምን ስለሌለኝ ስለ ኑሮ ስለ ቤተሰብ ታሪክ ምናምን የሚጠይቁኝ ሰዎች ያስጠሉኛል፣ ነገር ግን እሳቸውን ለመጠየቅ ምክንያት የሆነኝ ነገር ቡናው ነበረ... እማማ ለምን ቤተሰብ እስኪመጣ ትንሽ አንጠብቅም አልኳቸው ትንሽ ከሳቁ በኋላ ቤተሰብ ነው ያልሽው? ብለው ጠየቁኝ እኔም አዎ ቤተሰብ ባይኖረኝም ቡና ከቤተሰብ ጋር ሲሆን ደስ ይላል ብዬ ነው አልኳቸው አይይይይ ልጄ የሉም አሉኝ አይመጡም ለማለት መስሎኝ ዝም አልኩኝ አብረን ቡናውን ጠጥተን በድጋሚ ለመሄድ ተነሳሁ ትልቅ ቀጠሮ ያለኝ ሰው አልመስልም? ልጄ ገበያ ለመሄድ አስቤ ነበረ ግን አቅም አጣሁ ብለው ዝም አሉ ታዲያ የሚልኩት ሰው የለም? በዚህ ጊዜ ሰው ከየት ይመጣል ብለሽ ነው የምትሄጅበት ከሌለ ለምን አንቺ ሮጥ ብለሽ አትመጪም አሉኝ ማን? እኔ ገበያ? እኔ እቃውን እንዴት ገዝቼ እንደሚመጣ እንኩዋን አላውቅም አልኳቸው በልቤ ደግሞ ለኔ ብር ሰጥቶ መላክ ውሻ ላይ አጥንት እንደመላክ ነው እስከአሁን ዝም ያልኩት ራሱ ምስኪን ስለሆንሽ ነው እንጂ ሌላ ሰው ቤት ገብቼ ቢሆን ኖሮ መቼ ምን ይዤ እንደወጣሁ ማወቅ አትችይም እያልኩ ሴትዮዋን በአግርሞት ማየቱን ቀጠልኩኝ... ቀላል እኮ ነው ልጄ ሮጥ ብለሽ ደርሰሽ ነይ ብለው 300ብር ሰጡኝ እኔም ብሩን ይዤ ከቤት ወጣሁኝ.... ልክ ከቤት እንደወጣሁ አእምሮዬ ላይ ብዙ ሃሳቦች መምጣት ጀምሩ፣ አንዴ ብሩን ይዤ ዛሬ ዘና ማለት አለብኝ የሚል ሃሳብ ነው ሌላኛው ልቤ ደግሞ ከዚህች ምስኪን እናት ብር ይዞ መጥፋት ከክህደት ሁሉ ትልቁ ክህደት ነው እያለ መውቀስ ጀመረ ቆይ እሺ በዚህ 300ብር እቃ ገዝቼ ስሄድ ትንሽ ብር ብቻ ብሰጠኝስ ብዬም ሐሳብ ውስጥ ገባሁ ልቤ ግን አሁንም ምንም ባይሰጡሽ እንኩዋን እቃውን ገዝተሽ መሄድ አለብሽ ብሎ ትእዛዝ ሰጠኝ እኔም የልቤን ትእዛዝ ተቀብዬ እቃውን ገዝቼ ወደ ቤታቸው ተመለስኩኝ ተመልሼ በመምጣቴ ደስታ ብቻ ሳይሆን ግራ የተጋቡ የሚመስሉት እናት እንዴት መጣሽ? እእእእ ማለቴ ቶሎ መጣሽ ቤት ገብተሽ ቁጭ በይ አሉኝ አይይይ አሁን እሄዳለሁ አልኳቸው ለምን? የት? ብለው ተጣድፈው ከተናገሩ በኋላ ግን አንድ ሁለት ቀን እዚህ ብትቀመጪ ደስ ይለኛል ብለው በትህትና ተናገሩ ኧረ ማዙካ አግኝቼ ነው ሲጀመር እኔ ምን መሄጃ አለኝ በደስታ ነው ቁጭ የምለው ብዬ ቁጭ አልኩኝ ለምሳ ብዬ የገባሁት ቤት የአራት ወር መኖርያ ቤት ሆኖ አገኘሁት። ከአራት ወር በኃላ ሱቅ ተልኬ ስሄድ በአጋጣሚ የሆነ ልጅ መጥቶ ሀይ ሀረግ ብሎ ሰላም አለኝ ሀረግ? እዚህ ሰፈር የኔን ስም ማንም አያውቅም እሱ እንዴት አወቀ እያልኩ ትንሽ በዝምታ ተዋጥኩኝ ምነው ሀረግ አላስታወሽኝም እንዴ? እዩኤል እኮ ነኝ ከጥቂት ወራት በፊት ከመንገድ ላይ አንስተሽ ሃኪም ቤት የወሰድሺኝ ልጅ ብሎ በድጋሚ ሰላም አለኝ ይቅርታ ወንድም ልቤ ሌላ ቦታ ስለነበረ ነው ታዲያ አሁን እንዴት ነህ አልኩት እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ደህና ነኝ፣ ሻይ ቡና ማለት እንችላለን ብሎ ጠየቀኝ አሁን አልችልም ተልኬ ነው የመጣውት አልኩት እና እዚህ ሰፈር ነሽ ማለት ነዋ አለኝ አዎ እዚህ ሰፈር ነኝ አልኩት እኔም እኮ እዚሁ ሰፈር ነኝ አለኝ በቃ ቻው ብዬ ወደ ቤት መጣሁኝ ገበያ ተልኬ ታማኝ በመሆኔ አራት ወር በሙሉ ቁርስ ምሳ እራት ጠግቤ መብላት ጀመርኩኝ ጥሩ አልጋ ላይ ተኝቼ ማደር ጀመርኩኝ ጥሩ ልብስ መልበስ ጀመርኩኝ እነዚህ አሁን ያልኩት ነገሮች ታማኝ በመሆኔ ካገኘውት ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው። ከቀኑ ስድስት ሰአት አካባቢ የግቢው በር ተንኳኳ... እኔ እዚህ ቤት ከገባሁበት ቀን እስከዛሬ እዚህ ቤት ሰው መጥቶ አያውቅም ምስኪኗ እናት ደግሞ ቤት ውስጥ ናት ማነው ብዬ በር ለመክፈት ሄድኩኝ በሩን ስከፍት.

ማነው ብዬ ሄጄ በሩን ስከፍት.. እዩኤል? እንዴት መጣህ አልኩት እእእእእእ ታምራት የለም አለኝ ታምራት ታምራት? ማነው ደግሞ ታምራት አልኩት ኦኦኦኦኦ ለካ ቤት ተሳስቼ ነው የመጣሁት ብሎ በተረፈ እንዴት ነሽ አለኝ ደህና ነኝ አልኩት እንዲህ እንዲህ እያለን ከእዩኤል ጋር ጥሩ ጓደኛሞች ሆንን.. ቤት ተሳስቼ ነው የመጣውት ያለኝ ቀን ለካ ውሸቱን ነው ሱቅ የተገናኘን ቀን ተከትሎኝ መጥቶ ነው ቤቱን አይቶ ተመልሶ የሄደው እዩኤል በጣም የዋሀ መልካም ልጅ ነው በጓደኝነት ብዙ መቆየት አልቻልንም ጓደኝታችን ቶሎ ወደ ፍቅር ተቀየረ... የእዩኤል እናት በህመም መሰቃየት ከጀመሩ ብዙ አመታትን አስቆጥረዋሉ የእናቱን ሙሉ ኃላፊነት ከልጅነቱ ጀምሮ በእጁ ላይ ይዞ ያደገ ምስኪን ልጅ ነው ህይወቱ ከእኔ ህይወት ጋር ብዙ ተመሳሳይ ነገሮች ያሉት እዩኤል ከራሱ እድገት አንጻር ለኔ ያለው ክብር እጅግ በጣም ደስ ይለኛል አንድአንድ ጊዜ የልቤን ሃሳብ ሁሉ የሚያውቅ ይመስለኛል እኔም ህይወቴን ከመንገድ ላይ አንስተው ዛሬ እንደዚህ በደስታ እንድኖር ካደረጉኝ እናቴ ጋር አብሬ በደስታ እየኖርኩኝ ነው ለዚህች ምስኪን እናት ልጅ ይሁን ዘመድ የሚባል ነገር የላቸውም አሁን ግን እሳቸውም ልጅ እኔም እናት አግኝተን በደስታ እየኖርን ነው። እዩኤል አልፎ አልፎ ልክ እንደ እናቱ ሁሉ በህመም እየተሰቃየ ነው ጥሩ ሃኪም ቤት ሄደው ጥሩ ህክምና የማግኘት እድል ግን አልነበረውም፣ አንድ ቀን ቤት ውስጥ ቁጭ ብዬ ቴሌቭዥን በማየት ላይ እያለሁ ስልክ ተደወለልኝ የእዩኤል ስልክ ነው እኔም በደስታ ሀይ ፍቅር አልኩት እዩኤል አይደለም እናቱ ነኝ ቶሎ ብለሽ ድረሽ ታውቂያለሽ እኔ እንደሆንኩ አቅም የለኝም አሉኝ እማማ እዩኤል ምን ሆነ ስላቸው አሁን ጥያቄው ምንም አያደርግም ቶሎ ብለሽ ቤት ነይ አሉኝ እኔም በፍጥነት ቤታቸው ሄድኩኝ፣ እዩኤል እራሱን ስቶ ወድቆ ነበረ.... ቶሎ ብዬ ታክሲ ጠርቼ ወደ ሃኪም ቤት ወሰድኩት ከብዙ የፀጥታ ሰአታት በኋላ እዩኤል በድጋሚ ማውራት ጀመረ... እዚህ አለም ላይ አለኝ የምለው እዩኤል እንደዚህ ሆኖ ከማየት በላይ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር ምን አለ? ሀረግ አሁን እኮ ደህና ነኝ ይላል የሆዱን በሆዱ ይዞት ሁሉም ሰው የፍቅረኛውን ደስታ ይፈልጋል አይደል እሱም ለኔ ደስታ ብሎ ህመሙን ቀላል ለማድረግ እየሞከረ ነው ህመሙ በጣም ከባድ እንደሆነ ግን ሃኪሙ ነግሮኛል ዛሬ መልካሙን ዶክተር የተገናኘውበት ቀን ናት ለህክምናው የጠየቀኝ ብር በጣም ብዙ ብር ነው በኪሴ ውስጥ የነበረኝ ብር ደግሞ በጣም ጥቂት ብር ነው ይቅርታ አድርግልኝ ለጊዜው ሙሉ ብር የለኝም ልጁ እዚሁ ይቀመጥ እኔ ብሩን ይዤ እመጣለሁ አልኩት አይይይይ ችግር የለም ባይሆን ልጁ ክትትል ይፈልጋል ክትትል

ይቀጥላል ...