Get Mystery Box with random crypto!

​​ መልካሙ ዶክተር ክፍል አንድ ➊ ስሜ ሀረግ ነው፣ ሀረግ የሚለውን ስ | ፍቅርና ተስፋ

​​ መልካሙ ዶክተር

ክፍል አንድ ➊



ስሜ ሀረግ ነው፣ ሀረግ የሚለውን ስም ማን እንዳወጣልኝ እንኳን አላውቅም ሀረግ የሚለው ስም ለኔ ብዙ ትርጉም ይሰጠኛል አንድ አንድ ጊዜ የሆነ ሰው ጥሎኝ ልሄድ ተክሎኝ የሄደ ዛፍ እንደሆንኩ ይሰማኛል ፍሬ የሌላ ዛፍ! የብቸኝነት ህይወት እንደዚህ ከባድ ነው ብሎ ለሌላ ሰው ለማስረዳት እንደዚህ ነው ብሎ ምሳሌ የሚሰጡት ነገር እንኳን ሊኖር አይችልም። ሁሉ ሰው ወደዚህች አለም ሲመጣ ተመሳሳይ ነገር ነው ይዞ የሚመጣው ከዚህ አለም ሲሄድም ተመሳሳይ ነገር ነው ይዞ የሚሄደው ነገር ግን በዚህች አለም ላይ ሁሉም ሰው የተለየያ ህይወት ይኖራል አንዱ የአንዱን ህይወት መኖር በፍጹም አይችልም ምክንያቱም የዚህች አለም ኑሮ መሪዋ እድል በምንለው ነገር የተያዘች ናትና፣ እሱ ወደፈለገበት እንጂ እኛ መሄድ የምንፈልግበትን ቦታ መሄድ አንችልም። ማንም ሰው ከእናቱ/ከአባቱ ተለይቶ መኖር አይፈልግም ግን ብቸኛ ሆኖ ይኖራል፣ ማንም ሰው አካለ ስንኩል ሆኖ መኖር አይፈልግም ግን በግድ ሆኖ ይኖራል፣ ማንም ሰው ድሃ ሆኖ መኖር አይፈልግም ግን ድሃ ሆኖ ይኖራል፣ ማንም ሰው በህመም እየተሰቃየ መኖርን አይፈልግም ግን ብዙ ሰዎች በህመም እየተሰቃዩ ይኖራሉ ፣ ለዚህም ነው ህይወት የምርጫ ጉዳይ ሳትሆን እድል ላይ የተሰራች ቤት ነው ያልኩት በዚህ አለም ላይ አብዛኛው ነገር ለሰዎች በተናጥል ተሰጥቷል ለሁሉም ሰው እኩል የተሰጠ ነገር ቢኖር " ፍቅር " ብቻ ነው! በዚህ ምድር ላይ ለሁሉም እኩል የተሰጠ ስጦታ ፍቅር ብቻ ነው ህጻን ይሁን ሽማግሌ፥ ሴት ይሁን ወንድ፥ ቆንጆ ይሁን አስጠሊታ ፥ሁሉም ሰው የፍቅር ስጦታውን ተቀብሏል፣ ምንም እንኳን ስጦታውን በአግበቡ የሚጠቀሙ ሰዎች በጣም ጥቂቶች ቢሆኑም ቅድም እንዳልኩት ሁሉም ሰው የፍቅር ስጦታን ከፈጣሪ ዘንድ ተቀብሏል።
የኔ የፍቅር ታሪክ የሚጀምረው በአንድ መጥፎ አጋጣሚ ቢሆንም አጋጣሚው ግን በድንገት ህይወቴን ቀይሮ አየሁት
ፈጣሪ ህይወትህን ለመቀየር ሲፈልግ ሰው ይልካል እንጂ እሱ አይመጣም ሰይጣንም ቢሆን ህይወትህን ለማበላሸት ሲፈልግ ሰው ይልካል እንጂ እሱ በተግባር አይመጣም ልዩነቱ ፈጣሪ መልካም ሰው ይልካል ሰይጣን ደግሞ ክፉ ሰው ይልካል እንደ አጋጣሚ ሆኖ ለኔ የተላከው ሰው መልካም ሰው ነበረ እዩኤል እኔ እንደዚህ ነው ብዬ ከምነግራችው በላይ መልካም ልጅ ነው ከምንም በላይ ለኔ ለብቸኛዋ ምስኪን ልጅ ወንድም እናት አባትም ጭምር ነው እዩኤልን የተዋወኩት ድሮ ድሮ የጎዳና ልጅ እያለሁ ነበረ አንድ ቀን መንገድ ላይ መሬት ላይ ወድቆ ሰው ሁሉ ዝም ብሎት እያለፈ አይቼ ኪሴ ውስጥ ለምሳ ሰርቄ በያዝኩት ብር ሃኪም ቤት ወሰድኩት ሃኪም ቤት ውስጥ የካርድ ብር አጥቼ ወዲህ ወዲያ ስል............

ሃኪም ቤት የካርድ ብር አጥቼ ወዲህ ወዲያ ስል አንዲት
መልካም እናት ልጄ ሰው ጠፍቶብሽ ነው ወይ ብለው ጠየቁኝ እኔም የሆነውን ነገር ሁሉ በትህትና ነገርኳቸው፣ እርሳቸውም አይዞሽ ልጄ አንቺ መልካም ልጅ ነሽ የካርዱን ብር እኔ እሰጣችኋለሁ ግን የህክምና ብር አለሽ ወይ ብለው ጠየቁኝ
ማዘር እኔጋ ምንም ብር የለም ምናልባትም ልጁ ቀድሞ
እራሱን ቢያውቅ ስልክ ቁጥር ተቀብለን ለቤተሰቦቹ መደወል
እንችል ነበረ አልኳቸው
መልካም ብለው እርሳቸውም ከእኔ ጋር አብረው የልጁን ሁኔታ
ለማየት ቁጭ አሉ
ዶክተሩ የመጀመሪያ እርዳታ ከሰጠ በኋላ ለጊዜው ብዙ
አሳሳቢ ችግር እንደሌለበት ነገር ግን እራሱን ከጭንቀት ነጻ
ማድረግ እንዳለበት ነግሮት አንድአንድ መድሃኒቶችን ሰጥቶ
ትንሽ ብር ሲጠይቅ እኔ ቶሎ ብዬ ቤተሰብ ጋር ልደውል ስልክ
ቁጥር ስጠኝ አልኩት
ከዝምታ ሌላ ምንም መልስ መስጠት አልቻለም
በዚህን ጊዜ ከልጁ ዝምታ የሆነ ነገር መረዳት የቻሉት እናት
ከቦርሳ ውስጥ አውጥተው ሃኪሙ የጠየቀውን ብር ሰጡ
በጣም ደስ አለኝ ግን ምን አይነት መልካም እናት ናቸው?
ከዛም ልጄ እኔ አሁን ወደ ቤት ልሄድ ነው እናንተም ወደ
ቤታችሁ ተመለሱ ይሄ የታክሲ ብር ነው ብለው ብዙ ብር ሊሰጡ
ሲሉ እማማ እኔ ምን ቤት አለኝ ብለው ነው ለኔ የሄድኩበት ሁሉ
ቤቴ ነው የትም ሰፈር ብሄድ መኖር እችላለሁ ብሩን ለሱ
ስጡት አልኳቸው ልጄ ምን እያልሽ ነው ቤት የለኝም ማለት ምን ማለት ነው?
ቤተሰብ አለሽ አይደል ብሎ ጠየቁኝ እማማ ለካ እርስዎም ቀልደኛ ኖት ቤተሰብ ቢኖረኝ ይሄን
እመስላለሁ ብዬ ጥዬ ልሄድ ሲል ታዲያ ወዴት ነሽ ብለው ጠየቁኝ
ወዴት ነኝ? እኔን ከየት ነሽ ብሎ እንጂ ወዴት ነሽ ብሎ ሰው
ጠይቆ አያውቅም ምክንያቱም እኔ እግሬ ወደ መራኝ መሄድ
እንጂ እዛ እሄዳለሁ ብዬ መንገድ አልጀምርም አልኳቸው
ታዲያ ለምን ዛሬ ከእኔ ጋር አትሄጅም አሉኝ ቡሌ ይስጡኝ እንጂ የትም እሄዳለሁ አልኳቸው
ቡሌ ደግሞ ምንድነው ሲሉኝ
እማማ ምሳ አልበላሁም አልኳቸው
ልጁን አንተስ አትሄድም አሉት
እማማ እርሶ በጣም መልካም እናት ኖት ስለ ሁሉም ነገር
በጣም አመሰግናለሁ እግዚአብሔር ያክብሮት እኔ አሁን ቤት መሄድ እፈልጋለሁ እናቴ ትጠብቀኛለች ብሎ ልሄድ ሲል
ታዲያ ምስጋናው እኮ ከእኔ በላይ አጠገብህ ለቆመች ልጅቷ
ነው መሆን ያለበት እሷ እኮ ናት ከመንገድ ላይ አንስታ ሃኪም
ቤት የወሰደችህ አሉት
እሱም ወደ እኔ መጥቶ በመጀመሪያ ይቅርታ አድርግልኝ
ሃኪም ቤት የወሰድሽኝ አንቺ እንደሆንሽ አላወኩም ነበረ
በመቀጠል ደግሞ በጣም አመሰግናለሁ ስሜ እዩኤል ነው
ብሎ እጄን ጨበጠ
እኔም ሀረግ አልኩትና ለትንሽ ሴኬንዶች ሁለታችንም ፍዝዝ
ብለን ቀረን
በዚህ መሃል በይ አሁን እንሂድ እሱም ወደቤት ይሂድ ብሎ
እኔን ወደቤታቸው ይዘውኝ ሄዱ
ቤታቸው ደረስን፣ ቤት ውስጥ ለጊዜው ሌላ ሰው አልነበረም
ልክ ቤት እንደገባን የእጅ ውሃ ሰጥተውኝ ተሰርቶ ከተቀመጠው ምግብ አምጥተው ሰጡኝ
እኔም ተገኘ ብዬ ልጀምር ስል ቆይ ልጄ ምግብ ከመብላትሽ በፊት የሰጠሽን አምላክ ማመስገን አለብሽ ብለው አመስግነው
ሰጡኝ ምግቡን ግማሽ ካደረኩ በኋላ የእሳቸው ነገር ትዝ አለኝ
እማማ እርስዎ አይበሉም አልኳቸው እሺ መጣሁ አሉና ሌላ ምግብ አምጥተው ጨምረው ከእኔጋ አብሮ መብላት ጀመሩ
ይህች ቀን በህይወቴ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ ሰዎች ክብር
የሰጡኝ ቀን ነበራች
ምግቡን ጨርሼ እማማ አመሰግናለሁ ብዬ ልሄድ ስል......

ይቀጥላል!


​​​​​​​@tloveandhope