Get Mystery Box with random crypto!

ጠቃሚ የህይወት መርሆዎች! * ❖ ደግ ሁን፡፡ የምትችል ከሆነ ከማንም የበለጠ ደግ | ፍቅርና ተስፋ

ጠቃሚ የህይወት መርሆዎች!
*

❖ ደግ ሁን፡፡
የምትችል ከሆነ ከማንም የበለጠ ደግ ሁን፤ ቢሆንም ደግነትህን አትናገር፡፡ ስለተረፈህ ሳይሆን ሰብአዊነት ኖሮህ ላንተ ከሚያስፈልግህ ሳትሰስት ለሌሎች አካፍለህ ኑር፡፡ "መስጠት የማያውቁ ሰዎች ሌሎች ሲሰጡ ይታመማሉ!!"

❖ ቀና ብለህ ተጓዝ፡፡
ዘወትር ቀና ብለህ ተጓዝ ምክንያቱም ራሱን ያጎበጠ ሰው መቼም ሌሎችን አቅንቶ አያውቅምና፡፡ ችግሮችህን አስብ፡፡ የገጠሙህን ችግሮች ችላ አትበላቸው ምክንያቱም ችግርን በጥቅም ላይ እንደማዋል ጣፋጭ ነገር የለምና፡፡

❖ እውቀትን የምትሻ ሁን፡፡
ከሌሎች ሰዎች ለማወቅ የተዘጋጀህ ሁን ምክንያቱም የእብደት የመጀመሪያ ምልክት እራስን አዋቂ አድርጎ ማሰብ ነውና፡፡

❖ መልካም አሳቢ ሁን፡፡
ሁሉም ሰው ራሱን የሚያገኘው በየእለቱ በሚፈጥረው አስተሳሰብ መሠረት ነው፡፡ መጥፎ ቀን የምንለው መጥፎ ሃሳብ ያሰብንበት ቀን ነው፡፡ ስለሆነም ሁሌም መልካም ነገር እንዲገጥምህ መልካም የሆነውን ብቻ ተመልከት፡፡

❖ የቁሳዊ ድህነትን አትፈርበት፡፡
የቁሳዊ ድህነትን አትፈርበት ምክንያቱም ምድር ላይ እጅግ የሚያሳፍረው ነገር ቢኖር የአዕምሮ ድህነት ነውና፡፡

❖ ለገባኸው ቃል ታመን፡፡
ቃል ለመግባት የዘገየህ፤ ከገባህ ደግሞ የፈጠንክ ሁን፡፡ ራስህን አሻሽል፡፡ "የአንተን ውድቀት ለሚመኙ ስትል ራስህን አሻሽል" መጀመሪያ ራስህን እወቅ፡፡ ጠንካራ ጎኖችህን ይበልጥ አጠንክርህ በድክመትህ ላይ
ፈጥነህ ዝመትባቸው፡፡

❖ ህሊናህን አድምጥ፡፡
የተፃፈውን ሁሉ አንብበህ በህሊና መዝገብህ ከመፃፍህ በፊት በህሊናህ ሚዛንህ አብጠርጥር፡፡ ሁሌም ለሕሊናህ እንጂ ለሰው አትገዛ ምክንያቱም የሰው ልጅ ዛሬ ወዳጅ
መስሎ ቀርቦ ነገ ሊሸሽህ ይችላል ህሊናህ ግን በፀፀት እየወቀሰህ ዘወትር አብሮህ ይኖራልና፡፡

❖ አንደበተ ርቱህ ሁን፡፡
"ምላስህን ካልጠበካት እስዋ አትጠብቅህም" ጨዋ አንደበት የተዘጉ በሮችን ይከፍታል፡፡

❖ ብልህ ሁን፡፡
መከራን እና የተወረወረ ድንጋይን ዝቅ ብሎ ማለፍ ብልህነት ነው፡፡ ምክንያቱም ምድር ላይ ስትኖር ለመኖር መፈተን ለማለፍ መታገስ ግድ ነውና፡፡

❖ ሁልጊዜ ራስህን ሁን፡፡
ራሱን ያወቀ ሰው ሁልጊዜ በኑሮው ደስተኛ ነው፡፡ ሌላውን ለመምሰል ስትሞክር ማንነትህን ታጣና ህይወት ጣእሟን ታጣለች፡፡

❖ ሞራል ይኑርህ፡፡
የማይዋዥቅ የህይወት ሞራል ይኑርህ ምክንያቱም ጠንካራ ሞራል የህይወት ተስፋ ነውና፡፡

❖ ባለህ ነገር ተደሰት፡፡
ዛሬን ስለነገ በመጨነቅ ካሳለፍከው ዛሬን በቅጡ መኖር ይሳንሃል፡፡ ስላለህ ነገር እንጂ ስለሌለህ ነገር አታስብ ምክንያቱም ነገ የፈጣሪህ ነውና፡፡

❖ እውነታን ተቀበል፡፡
ተፈጥሮ የቸረችህን ማንነትህን አምነህ መቀበልን ትተህ ለማማረር ወይም ለመሸማቀቅ አትሞክር ምክንያቱም በተሰጠህ ተፈጥሮሯዊ ማንነትህ ላይ ያንተ ሚና የለበትምና፡፡ በማይለወጥ አንተነትህ ተደሰት ምክንያቱም
ቁርጡን ያወቀ ሰው ምርጫ ይኖረዋልና፡፡
ትክክለኛና ፍጹም ቀናውን መንገድ አግኝተን እንኖር ዘንድ ፈጣሪ ይርዳን!

መልካም ቀን!



@tloveandhope