Get Mystery Box with random crypto!

ትርጉም አለው

የቴሌግራም ቻናል አርማ tirgum_alew — ትርጉም አለው
የቴሌግራም ቻናል አርማ tirgum_alew — ትርጉም አለው
የሰርጥ አድራሻ: @tirgum_alew
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 845

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-02-23 21:41:32
በቦረና ካሉት የቀንድ ከብቶች 10 በመቶውን ለመታደግ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ያስፈልጋል ተባለ

On Feb 23, 2023 156
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)

በቦረና ዞን ካሉት የቀንድ ከብቶች ውስጥ 10 በመቶውን ለመታደግ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር እንደሚያስፈልግ የዞኑ አስተዳደር ገለጸ፡፡

በድርቁ ምክንያት በዞኑ ከ3 ሚሊየን በላይ እንስሳት የሞቱ ሲሆን ፥ ከዚህ ውስጥ 85 በመቶዎቹ የቀንድ ከብቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የቀሩትን 230 ሺህ የቀንድ ከብቶች ለመታደግ እየተሰራ ሲሆን ፥ ለ3 ወር የቀንድ ከብቶቹን ለመታደግ ቢያንስ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ማቅረብ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም 135 ሺህ ኩንታል መኖ የሚያስፈልግ ቢሆንም ማቅረብ የተቻለው አንድ በመቶ ብቻ መሆኑን ነው የዞኑ አስተዳደሪ ጃርሶ ቦሩ የገለጹት።

እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ የታሰበውን ያህል ችግር ውስጥ የሚገኙ ከብቶችን መታደግ ከባድ ሊሆን እንደሚችል አስገንዝበዋል፡፡

እስካሁን ዞኑ በቀንድ ከብቶች ሞት ምክንያት33 ቢሊየን የሚገመት ብር ማጣቱንም አስተዳዳሪው ተናግረዋል፡፡

በታሪኩ ለገሰ


Source: Fana Broadcasting
37 views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 21:38:56 በቦረና ለተጎጂዎች የሚቀርበው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ተጨማሪ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ
On Feb 23, 2023 26
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)

በቦረና ዞን ለተጎጂዎች የሚቀርበው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ተጨማሪ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የተከሰተው ድርቅ በሰው እና እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ነው፡፡

የዞኑ አስተዳደር በበኩሉ ከ 3ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ እንስሳት በድርቁ መሞታቸውን የገለጸ ሲሆን ፥ በአሁኑ ወቅት ለተጎጂዎች ዕርዳታዎች እየቀረቡ ቢሆንም በቂ አለመሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡

ባለፉት 3 ዓመታት ዝናብ ባለመኖሩ ምክንያት ከ 800 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍል ለከፋ ችግር መጋለጡም ነው የተነገረው፡፡

የሚጠበቀው ዝናብ በወቅቱ ካልጣለ ችግሩ ከዚህ የከፋ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት እንዳለውም ዞኑ በሰጠው መግለጫ ገልጿል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በድቡልቅ የድርቅ ተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያ ያገኛቸው የህብረተሰብ ክፍሎችም በአካባቢው በተከሰተው አስከፊ ድርቅ የደረሰባቸውን ጉዳት መታዘብ ችሏል፡፡

በዞኑ አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል አርብቶ አደር መሆኑና ከእንስሳት ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያለው በመሆኑ ድርቁ ባስከተለው ችግር ለከፋ ጉዳት መዳረጉን የገለጹት የቦረና ዞን አስተዳዳሪ አቶ ጃርሶ ቦሩ ናቸው፡፡

የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ ተቋም ምክትል ሀላፊ ዶ/ር መሊቻ ሎጂ እንዳሉት ፥ በቂ ባይሆንም እንኳን የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የተወሰኑ እንስሳትን ለማዳን የእንስሳት መኖን እያቀረበ ነው፡፡

አቶ ጃርሶ ፥ ድርቁ አሁን ላይ እያደረሰ ካለው ጉዳት አንጻር ዕርዳታ እየቀረበ ቢሆንም ጉዳት ከደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍል ቁጥር አንጻር በቂ አለመሆኑን ነው የገለጹት፡፡

በቦረና ዞን ብቻ በ3 ዙር ከ 375 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በፌዴራልና በክልሉ ቡሳ ጎኖፋ አማካኝነት የምግብ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እየቀረበ ነው ያሉት ዶክተር መሊቻ ፥ የክልሉ የመንግስት ተቋማትና የልማት ድርጅቶች በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ እየተሰራ ነውም ብለዋል፡፡

በመሳፍንት እያዩ


Source: Fana Broadcasting
33 views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 21:44:01
በስንዴ እጥረት ምክንያት የዱቄት ፋብሪካዎች ስራ እያቆሙ ነው ተባለ

(Via Ethio FM)

የፓስታና መኮሮኒ አምራች ፋብሪካዎች የስንዴ ምርት እጥረት ገጥሞናል፤ በዚህም ስራ ለማቆም ተገደናል እያሉ እንደሚገኙ ኢትዮ ኤፍኤም ዛሬ ዘግቧል።

የዱቄትና የዱቄት ውጤቶች አምራቾች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉነህ ለማ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ስንዴ በአሁኑ ወቅት ኮንትሮባንድ ሆኗል፤ ማንም እንደፈለገ መግዛትም ሆነ መሸጥ አይችልም ብለዋል፡፡

መንግስት ለኤክስፖርት የሚሆን ስንዴን ለማግኘት ሲል ዩኒዮኖች ብቻ እንዲገዙ ፈቀደ፣ ለዱቄት አምራቾችም በዩኒዮኖች በኩል ታገኛላችሁ ተባሉ፣ በኋላም 12 ባለሃብቶች ተመርጠው ወደ ስራ ገቡ፣ ዱቄት አምራቾች ግን ስንዴ ሊያገኙ አልቻሉም ብለዋል፡፡

ይህ ችግር ከተፈጠረ 2 ወራትን አስቆጥሯል የሚሉት አቶ ሙሉነህ አምራቾች በእጃቸው ያለችውን ስንዴ እየቆጠቡ ሲጠቀሙ ቆይተው አሁን ላይ ስራ ማቆም ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚህም በዳቦ ላይ የሚስተዋለው ጭማሬ እንዳለ ሆኖ የ1 ኪሎ መኮሮኒ ዋጋ ከ40 ብር ወደ 80 ብር ከፍ እንዲል አድርጎታል ነው የተባለው፡፡

እንደ አቶ ሙሉነህ ገለጻ በአሁኑ ወቅት ስንዴ እንደ ኮንትሮባንድ ተቆጥሮ በየኬላዎች በፍተሻ እየተያዘ ነው፡፡ በዚህም አምራቾች ገዝተው መተቀም አይችሉም፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች መጋዘን ላይ ስንዴ የተገኘባቸው ዱቄት ፋብሪካዎችም ሆነ ነጋዴዎች በህገ ወጥ መንገድ ግብይት ፈጽማችኋል በሚል ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡

በመሆኑም ከሁሉም በፊት የሃገር ውስጥ ፍላጎትን ማሟላት ይቀድማልና ችግሩን ለመፍታት መንግስት ትኩረት እንዲሰጥ አቶ ሙሉነህ ጠይቀዋል፡፡
58 views18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 22:45:13 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንግስት ህገወጥ ድርጊቱን እስከ የካቲት 5 የማያስቆም ከሆነ ሰላማዊ ሰልፍ እንደምታደርግ መግለጿ ይታወሳል፣ የተወገዘው አካል በበኩሉ በዛው ቀን (የካቲት 5) ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል።

ለምን እንደሆነ ግልፅ ነው?

ሁለቱንም አካላት በአንድ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳያረጉ ከልክሎ በቤተክርስቲያኗ ቀድሞ የታሰበውን ሰልፍ ለማስቆም የተደረገ አካሄድ ነው። ከዛ "የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት" ምናምን የሚሉ መግለጫዎችን እንሰማለን።

#MarkMyWord

@EliasMeseret
60 views19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 23:20:10
83 views20:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 20:52:42
#Update የ ' ፌደራሉ መንግሥት ' በሻሸመኔ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ለሚደረገው ግድያ ኃላፊነቱን ሊወጣና ሊያስቆም ይገባል ስትል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ አቀረበች። ቤተክርስቲያኗ በሻሸመኔ ከተማ አንድ ሰው በፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት መገደሉን ገለፃለች። ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጉዳዩን በተመለከተ ፤ " እየሞተ ያለው ሕዝብ ነው ቅጠል…
76 views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 20:52:42 #Update

የ ' ፌደራሉ መንግሥት ' በሻሸመኔ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ለሚደረገው ግድያ ኃላፊነቱን ሊወጣና ሊያስቆም ይገባል ስትል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ አቀረበች።

ቤተክርስቲያኗ በሻሸመኔ ከተማ አንድ ሰው በፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት መገደሉን ገለፃለች።

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጉዳዩን በተመለከተ ፤ " እየሞተ ያለው ሕዝብ ነው ቅጠል አይደለም እየተበጠሰ የሚወድቀው ፤ #ይሄ_ፖለቲካ ነው። የፌደራል መንግሥት በሻሸመኔ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ለሚደረገው ግድያ ኃላፊነቱን ሊወጣና ሊያስቆም ይገባል። " ብለዋል።

በሻሸመኔ ምንድነው የሆነ ?

ተ/ሚ/ማ የተባለው የቤተክርስቲያኗ ሚዲያ " በዛሬው ዕለት ሕገ ወጡ ቡድን ወደ ሻሸመኔ ይመጣል መባሉን ተከትሎ ጠዋት ሁለት (2:00) ሰዓት ላይ ሥርዓተ ቅዳሴ እንደተፈጸመ ሕዝቡን ለመጥራት በከተማዋ ያሉ አድባራት ደወል ደውለዋል " ሲል ገልጿል።

" ጥሪው ሰምቶ ሁሉም ምእመን ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ ይጀምል ፤ በዚህ ጊዜ ወደ ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሔዱ ምእመናን የቤተክርስቲያኑ በር በመዘጋቱ ከውጪ ቆመው ነበር።

በእንዲህ ሁኔታ ውስጥ እያለ የከተማው ፖሊስ ሕዝቡን ለመበተን ተኩስ ከፍያል ፤ እስካሁን ድረስ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት ሰማዕትነትን ተቀብሏል፤ በውል ያልታወቀ ሰውም በጥይት ተመቷል " ሲል የነበረውን ሁኔታ አስረድቷል።

በሌላ በኩል ቤተክርስቲያኗ ፤ " ትናንትና ሌሊት ሊቀ ጳጳሷን አስሮ ከከተማ ያባረረው ኃይል   በአርሲ ሀገረ ስብከት መናገሻ አሰላ ኦርቶዶክሳውያንን እያሠረ  ይገኛል " ብላለች።

በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ውስጥ ያሉትም እንዲወጡ እየተነገራቸውና ያ የማይሆን ከሆነ የኃይል እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ተዝቶባቸዋል ብላለች።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ያሉት ሁኔታዎች እየከረሩ መጥተው ለሰው ህይወት #መጥፋት ምክንያት እስከመሆን የደረሱ ቢሆንም መንግስት እስካሁን ስለጉዳዩ ምንም ያለው ነገር የለም።

ቤተክርስቲያን በበኩሏ ለዚህ ሁሉ መሆን ህገወጥ ሲመት አከናውነዋል ፤ ተቀብለዋል ባለቻቸው ግለሰቦች እና የመንግስት ተቋማት ላይ ክስ ለመመስረት በሂደት ላይ ነች።

@tikvahethiopia
69 views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 19:42:14
ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ መንግስት የቤተ ክርስቲያኒቱን መብት የማያስከብር ከሆነ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ መላው ኦርቶዶክሳውያን የሚሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ በመጥራት በደሉን ለዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ እንደሚገልጽ አስታወቀ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ያሳወቀው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው።

" መንግሥታችን በሕገ መንግሥቱ የተጣለበትን ኃላፊነት በመወጣት የቤተ ክርስቲያኒቱን ተቋማዊ ልዕልና፣ በሕግ የተሰጣትን መብትና ጥቅም ያስከብር " ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ " ሕገወጡን ድርጊት ተገቢውን እርምት በመስጠት ኃላፊነቱን ይወጣ " ሲል አሳስቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን " ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ ብፁዓን አበው ሊቃነጳጳሳት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋይ ካህናትና ምእመናን ጭምር የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ በደላችንን ለዓለም ሕዝብ ችግሩ ተፈቶ የቤተ ክርስቲያኒቱ መብት እስኪረጋገጥ ድረስ ያለማቋረጥ እስከ ሕይወት መስዋዕትን ድረስ በመክፈል የምናሳውቅ ይሆናል " ብሏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬ መግለጫ ሰሞኑን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በተመለከተ የተናገሩትንና በመገናኛ ብዙሃን የተሰራጨውን ንግግራቸውን በማንሳት እንዲታረም አሳስቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተይይዟል)

@tikvahethiopia
63 views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-12 12:38:44
Training Opportunity for 2023 Graduates of AAiT

If you are graduating this year from Addis Ababa University Institute of Technology then you are in luck!!

Dereja is bringing you employability skills and job readiness training that is set to help join the workforce equipped and ready!! The training will prepare you in;

Understanding the job market,
The job searching process,
Applying for a Job application,
CV and interview preparation, and many more

Time: 3:00-6:00 Local Time
Venue: AAiT, Auditorium
Date: Saturday, January 14,2023

@awaqiethiopia
111 views09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 20:42:35
አዲሷ ፀሐይ
The Fresh Sun

photo by #


Join Godana Challenge 2 @godanachallenge_bot
161 views17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ