Get Mystery Box with random crypto!

ድምጽ አልባ እና ናፍጣም ሆነ ቤንዚን የማይጠቀም ጄኔሬተር የሰራው ኢትዮጵያዊ ወጣት . . . ፈዴ | TIKVAH-MAGAZINE

ድምጽ አልባ እና ናፍጣም ሆነ ቤንዚን የማይጠቀም ጄኔሬተር የሰራው ኢትዮጵያዊ ወጣት . . .

ፈዴሳ ሹማ ይባላል። ተወልዶ ያደገው በቄለም ወለጋ ሲሆን በከተማው ውስጥ በኤሌክትሪክ ጥገና ሙያውም ብዙዎች ያውቁታል፡፡ ሥራው ጥገና እንደመሆኑ የመብራት መጥፋትና መቆራረጥ ሥራውን ብዙ ጊዜ ያስተጓጉልበታል።

ችግር ብልሃትን ይወልዳል እንዲሉ ወጣቱ መላ በመዘየድ ከብዙ ጥረት በኋላ አንድ ግዜ ቻርጅ ተደርጎ እስከ አንድ ዓመት ድረስ አገልግሎት መስጠት የሚችል ቴክኖሎጂ እውን አደረገ። ቴክኖሎጂውንም ይበልጥ አዘምኖ መስራት ችሏል።

ቴክኖሎጂው የመብራት አገልግሎት ከመስጠቱ ባለፈ ሞባይል፣ ለቴሌቭዥን፣ ፍሪጅና የትኛውንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መጠቀሚያዎችን ቻርጅ የሚያደርግ፣ የሚያንቀሳቅስና በገመድና ገመድ አልባ ቴክኖሎጂ መጠቀም እንዲቻል ተደርጎ የተሰራ ነው።

አንዴ የያዘውን ሀይል ሪሳይክል እያደረገ ራሱን ቻርጅ ከማድረግ አልፎ ለረዥም ጊዜ ሀይል ማመንጨት የሚችለው ይህ ቴክኖሎጂ በሀገራችን የሀይል አማራጭ ሊሆን እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል።

ከ300 ዋት ጀምሮ እንደ ተጠቃሚው አቅምና ፍላጎት የሚዘጋጀው ይህ ድምፅ አልባ ጄኔሬተር አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ነው ወጣቱ የገለፀው።

በዚህም ወጣቱ ፌዴሳ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በሀገራችን በቤቱ መብራት የማይጠፋበት ብቸኛው ሰው ነው ተብሏል። ወጣቱ ቴክኖሎጂው በስፋት ተመርቶ ለህብረተሰቡ እንዲደርስ እየሰራ ሲሆን በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና እገዛ እየተደረገለት እንደሆነም ተነግሯል።

@TikvahethMagazine