Get Mystery Box with random crypto!

በምስራቅ ወለጋ ተፈናቅለው ለሚገኙ ሰዎች እርዳታ እንዲደረግ ተጠየቀ የኢትዮጵያ ሲቭል ማህብረሰብ | TIKVAH-MAGAZINE

በምስራቅ ወለጋ ተፈናቅለው ለሚገኙ ሰዎች እርዳታ እንዲደረግ ተጠየቀ

የኢትዮጵያ ሲቭል ማህብረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ለሚገኙ ሰዎች እርዳታ እንዲደረግ መጠየቁን ሸገር ኤፍኤም ዘግቧል።

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ፤ 2,500 ሰዎች በዲጋ ወረዳ ተጠልለው ይገኛሉ ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቭል ማህብረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን፤ ጄፕሮ ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር ለእነዚህ ተፈናቃዮች ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በአካባቢው በነበረው የጸጥታ ስጋት ምክንያት ረጂ ድርጅቶች ወደ ቦታው ገብተው እርዳታ ለማድረስ ፈርተው መቆየታቸው ተገልጿል።

በአሁን ሰዓት በአንፃራዊነትም ቢሆን በአካባቢው እርዳታ ለማድረስ አስቻይ ሁኔታ እንዳለ ሲነገር ስለዚህም በብዙ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ተፈናቃዮች፤ ረጂ በምስራቅ ወለጋ ተፈናቅለው ለሚገኙ ሰዎች እርዳታ እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል።

@TikvahethMagazine