Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ የፓኪስታን ባንኮች በአዲስ አበባ ቅርንጫፎቻቸውን እንዲከፍቱ ጥሪ አቀረበች የኢፌዲሪ አም | TIKVAH-MAGAZINE

ኢትዮጵያ የፓኪስታን ባንኮች በአዲስ አበባ ቅርንጫፎቻቸውን እንዲከፍቱ ጥሪ አቀረበች

የኢፌዲሪ አምባሳደር ጀማል በከር አብዱላ የፓኪስታን ባንኮች ከንግድ ጋር የተያያዙ ግብይቶችን ለማካሄድ ቅርንጫፎቻቸውን በአዲስ አበባ እንዲከፍቱ መጠየቃቸውን የሀገሪቱ የዜና ምንጭ ዘግቧል።

አምባሳደሩ ጥሪውን ያቀረቡት በፋይሳላባድ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት (FCCI) ጋር በነበራቸው ንግግር ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስትም የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለማደላደል እና የሁለትዮሽ ንግድን ለማቀላጠፍ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የባንክ ቅርንጫፎችን መክፈት ትልቅ ፈተና እንዳለው የተናገሩት አምባሳደሩ ከተሳካ ግን የሁለትዮሽ ንግድን ለማጠናከር እና የፓኪስታን ላኪዎች ሰፊውን የአፍሪካ ገበያ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ብለዋል።

@TikvahethMagazine