Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን የዞን አምስት ውድድርን እንድታዘጋጅ ተመረጠች ኢትዮጵ | TIKVAH-MAGAZINE

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን የዞን አምስት ውድድርን እንድታዘጋጅ ተመረጠች

ኢትዮጵያ ከ10 ሃገራት እና ከ350 በላይ ልዑካን ቡድን የሚሳተፉበት በዓለም አቀፍ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን የሚዘጋጀው ዞን አምስት የምስራቅ አፍሪካ እጅ ኳስ ዋንጫ እንድታዘጋጅ መመረጧን የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል።

የምስራቅ አፍሪካ ዞን አምስት ሃገራት ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ጂቡቲ እና ቡሩንዲ ሲሆኑ ውድድሩ ከግንቦት 03 - 11/2016 ዓ.ም ከ18 ዓመት በታች እና ከ20 ዓመት በታች የብሄራዊ ቡድን የሚሳተፉበት የእጅ ኳስ ውድድር መሆኑ ተገልጿል።

@TikvahethMagazine