Get Mystery Box with random crypto!

በግብርና ምርቶች ብክነት በዓመት ከ474 ቢሊዮን ብር በላይ እየታጣ መሆኑ ተነገረ የግብርና ሚኒስ | TIKVAH-MAGAZINE

በግብርና ምርቶች ብክነት በዓመት ከ474 ቢሊዮን ብር በላይ እየታጣ መሆኑ ተነገረ

የግብርና ሚኒስቴር አዲስ ያስተዋወቀው የግብርና ምርቶች አስተዳደርና አመራር ስትራቴጂ፣ በኢትዮጵያ በየዓመቱ 474.67 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ የምርቶች ብክነት መኖሩን አመልክቷል በማለት ሪፖርተር አስነብቧል።

እያጋጠመ ያለው ብክነት የምርት ሒደት የሚያቀላጥፉ ምርጥ ዘር፣ ውኃ፣ የአፈር ማዳበሪያ፣ የግብርና ኬሚካሎች፣ መሬት፣ የእንስሳት መኖ፣ እንዲሁም የእንስሳት መድኃኒቶችን በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል ካለመቻል እንደሆነ ተጠቅሷል። 

በመሆኑም በየዓመቱ 161.74 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ የሥጋና ወተት ምርቶች እንዲሁም 312.93 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ የቅባት እህሎች፣ ጥራጥሬዎች፣ ፍራፍሬዎችና አትክልቶች እየባከኑ መሆኑም ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine